የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g01 12/8 ገጽ 29
  • አስደናቂ የሆነው ቱሌ ዛፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስደናቂ የሆነው ቱሌ ዛፍ
  • ንቁ!—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ችግር ቢኖርም በሙሉ ነፍስ ማገልገል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የዘመናችን አዝቴኮች እውነተኛ ክርስትናን ተቀበሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ንቁ!—2001
g01 12/8 ገጽ 29

አስደናቂ የሆነው ቱሌ ዛፍ

ሜክሲኮ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

በዓለማችን ካሉት የዛፍ ዓይነቶች ሁሉ ረጅሙ 110 ሜትር ወይም ከዚያ በላይ ቁመት ያለው በካሊፎርኒያ የሚገኘው ሬድውድ የተባለው ዛፍ ነው። ይሁን እንጂ በጎን ስፋት ክብረ ወሰኑን የያዘው የዚሁ የሴኮያ ዝርያ የሆነው በሜክሲኮ የሚገኘው የጥድ ዓይነት ነው። በጣም የታወቀው የዚህ ዛፍ ምሳይ (specimen) በሜክሲኮ ከዋሃካ ከተማ 13 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው መንደር በሳንታ ማሪያ ደል ቱሌ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ቱሌ ዛፍ ተብሎ ይጠራል። የታችኛው የግንዱ ዙሪያ 46 ሜትር ነው። ውፍረቱን ለመገመት እንዲያስችላችሁ ዙሪያውን ለመሙላት በትንሹ 30 ሰዎች እጅ ለእጅ መያያዝ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ከ500 በላይ ሰዎችን በሥሩ ማስጠለል ይችላል።

ይህ የቱሌ ዛፍ ከ2,000 ዓመት በላይ እድሜ እንዳለው ይገመታል። በ1996 ቅርንጫፎቹ ሲከረከሙ አስር ቶን የሚመዝን ጭራሮ ተለቅሟል። የአካባቢው ሰዎች ኤል ሂጋንቴ (ግዙፉ ዛፍ) እያሉ ይጠሩታል። በሜክሲኮ ይህ የዛፍ ዝርያ አዌዌቴ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህም በናዋተል ቋንቋ “የውኃው ዳር አዛውንት” ማለት ነው። በአብዛኛው በውኃ አቅራቢያ ወይም ረግረጋማ በሆኑ ስፍራዎች ስለሚበቅል ይህን ስያሜ ማግኘቱ ተገቢ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ