የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g02 7/8 ገጽ 28
  • በማዳመጥ እውቀት አግኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በማዳመጥ እውቀት አግኝ
  • ንቁ!—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፍቅር እንዳለን በሚያሳይ መንገድ ማዳመጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ጥሩ አዳማጭ ሁን
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • ደቀ መዛሙርት በማድረግ ተወዳዳሪ የሌለውን ኢየሱስን ኮርጅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • “እንዴት እንደምታዳምጡ በጥንቃቄ አስቡ”
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2002
g02 7/8 ገጽ 28

በማዳመጥ እውቀት አግኝ

በቶሮንቶ ስታር ጋዜጣ ላይ የወጣ አንድ ዘገባ “ከምናውቃቸው ነገሮች ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑትን የተማርነው በማዳመጥ ነው” በማለት ገልጿል። አብዛኛውን ጊዜያችንን የምናጠፋው በማዳመጥ ቢሆንም ትኩረታችን ይሰረቃል፣ ስለ ሌሎች ነገሮች እናስባለን ወይም ከሰማነው ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነውን እንረሳዋለን። እነዚህ ትኩረት የሚስቡ አኃዛዊ መረጃዎች የማዳመጥ ችሎታችንን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን የሚያጎሉ ናቸው።

በዘገባው መሠረት “በኅብረተሰብ ውስጥ ለሚታዩት ብዙ ችግሮች መንስኤው ደካማ የሆነ የማዳመጥ ልማድ ነው።” ስለ ሰው የንግግር ችሎታ የሚያጠኑትና የሐሳብ ልውውጥ ባለሙያ የሆኑት ሪቤካ ሻፈር ደካማ የሆነ የማዳመጥ ልማድ በአብዛኛው ራስን መግደልን፣ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚፈጸም ዓመፅን፣ የቤተሰብ መፈራረስንና አደገኛ ዕፅ መውሰድን ለመሳሰሉት ችግሮች አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያምናሉ።

ስለ ማኅበራዊ ሕይወት የሚያጠኑ ሳይንቲስቶች ሰዎች የተለያየ ዓይነት የማዳመጥ ዘይቤ እንዳላቸው አስተውለዋል። አንዳንዶች ከባለ ታሪኩ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መስማት የሚያስደስታቸው ሲሆን በሚነገረው ነገር ዙሪያ ያሉትን ዝርዝር ሁኔታዎች በሙሉ ማወቅ ይፈልጋሉ። ሌሎች ደግሞ መስማት የሚፈልጉት ስለተከናወነው ነገር ብቻ ስለሆነ ተናጋሪው በቀጥታ ወደ ነጥቡ እንዲሄድ ይሻሉ። መጽሔቱ “እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እርስ በርስ ሲነጋገሩ በቀላሉ መግባባት ይቸግራቸዋል” ብሏል።

ኢየሱስ “እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ” በማለት የጉዳዩን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርጎ የገለጸው ያለ ምክንያት አልነበረም። (ሉቃስ 8:18፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) ጥሩ አድማጭ መሆን መልካም ምግባር ነው። ውጤታማ የሆነ ውይይት ለማድረግም ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በውይይት ወቅት እንዴት ማዳመጥ እንደሚቻል ከቀረቡት ተግባራዊ ሐሳቦች መካከል ትኩረትን ከሚሰርቁ ነገሮች መቆጠብ፣ በመጠኑ ወደፊት ዘመም ብሎ ማዳመጥ እንዲሁም የሚናገረውን ሰው ትኩር ብሎ በመመልከትና ጭንቅላትን በመነቅነቅ ምላሽ መስጠት ይገኙበታል። እውቀት መቅሰማችን በአብዛኛው የተመካው ውጤታማ በሆነ መንገድ በማዳመጣችን ላይ ስለሆነ ትኩረት ሰጥቶ የማዳመጥ ልማድ ሁላችንም እያሻሻልነው ልንሄድ የሚገባ ነገር ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ