የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g04 2/8 ገጽ 17
  • ወደ ቀዝቃዛው ዓለም ሲመጡ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደ ቀዝቃዛው ዓለም ሲመጡ!
  • ንቁ!—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ልጅ መውለድ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ሕፃናት የሚያስፈልጋቸውና የሚፈልጉት
    ንቁ!—2004
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ውርጃ ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2004
g04 2/8 ገጽ 17

ወደ ቀዝቃዛው ዓለም ሲመጡ!

አንድ ሕፃን ልጅ የሚወለደው በጭንቀት በተሞላ፣ ለሰው ስሜት ደንታ ቢስና ቀዝቃዛ በሆነ ዓለም ውስጥ ነው። አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት እንደሚያምኑት አንድ ሕፃን ስሜቱን በቃላት መግለጽ ባይችልም እንኳ ከመወለዱ አስቀድሞ ገና በማሕፀን ውስጥ እያለ በአካባቢው የሚፈጸመውን ነገር ያውቃል።

ዘ ሴክሬት ላይፍ ኦቭ ዚ አንቦርን ቻይልድ (ምስጢራዊው የሽል ሕይወት) የተሰኘው መጽሐፍ “ገና ያልተወለደ ልጅ ከተጸነሰ ከስድስት ወር ጀምሮ (ምናልባትም ከዚህ ቀደም ብሎ) አንዳንድ ነገሮችን ተረድቶ ምላሽ የሚሰጥ ስሜት ያለው ሰብዓዊ ፍጡር ነው” ብሏል። ሕፃኑ ላያስታውሰው ቢችልም በሚወለድበት ሰዓት የሚኖረው አስጨናቂ ሁኔታ የወደፊት ሕይወቱን ይነካው ይሆናል የሚለው ጉዳይ በአንዳንድ ሳይንቲስቶች ላይ ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል።

ከተወለደ በኋላ ጭንቀቱ ይቀጥላል። ሕፃኑ ከእናቱ ማሕፀን ከወጣ በኋላ በቀጥታ ከእናቱ የሚመጣለት ምግብ ይቋረጣል። አየርና ምግብ ያደርስለት የነበረው እትብት አገልግሎቱን አብቅቷል። በሕይወት ለመቀጠል መተንፈስ መጀመርና የሚያስፈልገውን ምግብ ራሱ መውሰድ አለበት። የሚመግበውና ሌሎች ፍላጎቶቹን የሚያሟላለት ሰው ያስፈልገዋል።

ይህ ሕፃን በአእምሮ፣ በስሜትና በመንፈሳዊ ሁኔታ ማደግ አለበት። ስለዚህ ይህን ጨቅላ ሕፃን የሚንከባከብ ሰው የግድ ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግ ከሁሉ የተሻለ ብቃት ያለው ማን ነው? ሕፃኑ ከወላጆቹ የሚፈልገው ምንድን ነው? እነዚህ ፍላጎቶች ሊሟሉለት የሚችሉት እንዴት ነው? የሚቀጥሉት ርዕሶች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ