የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g04 11/8 ገጽ 18
  • ለምጽ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለምጽ ምንድን ነው?
  • ንቁ!—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በቆዳ ቀለምህ ደስተኛ ሁን
    ንቁ!—2010
  • ፀሐይ አፍቃሪዎች ለቆዳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ!
    ንቁ!—1999
  • ለረጅም ጊዜ ለፀሐይ መጋለጥህ ሊያሳስብህ ይገባል?
    ንቁ!—2009
  • የእባብ ቆዳ
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2004
g04 11/8 ገጽ 18

ለምጽ ምንድን ነው?

ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

◼ ሲቦንጊሌ አንዳንድ ጊዜ ስለ ቆዳዋ ሁኔታ እየቀለደች ትናገራለች። ፈገግ ብላ እንዲህ አለች:- “ስወለድ ጥቁር ነበርኩ፤ አሁን ግን ነጭ ነኝ፤ ስለዚህ ከየትኛው ወገን እንደምመደብ ግራ ገብቶኛል።” ሲቦንጊሌ እንዲህ የምትለው ፊቷ ላይ ለምጽ ስላለባት ነው።

የለምጽ በሽታ የሚከሰተው በቆዳ ውስጥ ያሉት ቀለም የሚያመነጩ ሕዋሳት ሲሞቱ ነው። በሽታው በቆዳ ላይ ነጣ ያሉ ነጠብጣቦች እንዲወጡ ወይም የተወሰነ የቆዳ ክፍል እንዲነጣ ያደርጋል። ይህ በሽታ በአንዳንድ ተጠቂዎች ላይ በመጀመሪያ ከነጣው የቆዳ ክፍል አልፎ የማይስፋፋ ሲሆን በሌሎች ላይ ደግሞ ወደ መላው ሰውነታቸው በፍጥነት ይሰራጫል። ለበርካታ ዓመታት ቀስ በቀስ እየተስፋፋባቸው የሚሄድ የበሽታው ተጠቂዎችም አሉ። ለምጽ የሚያስከትለው የሕመም ስሜት ካለመኖሩም በላይ በንክኪ አይተላለፍም።

የለምጽ በሽታ መጀመሪያ ላይ እንደተጠቀሰችው እንደ ሲቦንጊሌ ሁልጊዜ ግልጽ ሆኖ ላይታይ ይችላል፤ በሽታው ይበልጥ ጎልቶ የሚታየው በተለይ ጥቁር የቆዳ ቀለም ባላቸው ሰዎች ላይ ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ ብዙ ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ። ከ1 እስከ 2 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በለምጽ እንደሚያዙ አኃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ። በሽታው ዘርና ቀለም የማይለይ ከመሆኑም በላይ ሴቶችንና ወንዶችን እኩል ያጠቃል። ሆኖም የበሽታው መነሾ እስከ አሁን አልታወቀም።

ለምጽ እስከ አሁን ድረስ መድኃኒት ባይገኝለትም በተለያዩ መንገዶች ጎልቶ እንዳይታይ ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ታማሚዎች ጤነኛ የሆነውን ቆዳቸውን ፀሐይ ሲያጠቁረው ለምጹ ጎልቶ ይታያል። ስለዚህ ለፀሐይ አለመጋለጣቸው በሽታው እንዳለባቸው እንዳይታወቅ ያደርጋል። ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ደግሞ ልዩ የሆኑ የመዋቢያ ቅባቶችን በመቀባት የቆዳ ልዩነቱን መደበቅ ይችላሉ። ሪፒግመንቴሽን (እንደገና ማቅለም) የተባለው የሕክምና ዘዴ በአንዳንድ የበሽታው ተጠቂዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል። ይህ ሕክምና ለበርካታ ወራት መድኃኒት መውሰድንና ልዩ የሆኑ ጨረር አመንጪ መሣሪያዎችን መጠቀምን ይጨምራል። አንዳንድ ጊዜ ግን ይህ የሕክምና ዓይነት ጤነኛ የነበረው የቆዳ ክፍል በበሽታው እንዲጠቃ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ሌሎቹ ደግሞ ዲፒግመንቴሽን የተባለውን የሕክምና ዓይነት ይመርጣሉ። የዚህ ሕክምና ዓላማ ቀለም የሚያመርቱ ሕዋሳትን በመድኃኒት ከሰውነት ውስጥ ጨርሶ በማጥፋት በለምጽ ከተያዘው የቆዳ ቀለም ጋር ማመሳሰል ነው።

የለምጽ በሽታ በተለይ ፊት ላይ በሚወጣበት ጊዜ ተጠቂዎቹ የስሜት መረበሽ ያጋጥማቸዋል። ሲቦንጊሌ የሚያጋጥማትን ነገር እንዲህ ብላ ገልጻለች:- “በቅርቡ ሁለት ልጆች ተመለከቱኝና እየተጯጯሁ ከአጠገቤ ሮጠው ሄዱ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ በሽታው ተላላፊ ወይም በእርግማን የሚመጣ ስለሚመስላቸው ሊያናግሩኝ አይፈልጉም። ይህ በሽታ የያዛቸው ሰዎች መፈራት እንደሌለባቸው መናገር እፈልጋለሁ። ምክንያቱም በሽታው በንክኪም ሆነ በትንፋሽ አይተላለፍም።”

የይሖዋ ምሥክር የሆነችው ሲቦንጊሌ በፊቷ ላይ ያለው ለምጽ የምትወደውን መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር ሥራ እንዳትሠራ አላገዳትም። ይህን ሥራ ለመሥራት ወደ ሰዎች ቤት መሄድና ማወያየት ይኖርባታል። “የአሁኑን ማንነቴን አምኜ የተቀበልኩ ከመሆኔም በላይ ብዙም አልሳቀቅም። ስወለድ የነበረኝን መልክ መልሼ የማገኝበትን ይሖዋ አምላክ ቃል የገባልንን ገነት የሆነ ምድር በተስፋ እጠባበቃለሁ።”—ራእይ 21:3-5

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በ1967፣ በበሽታው ከመጠቃቷ በፊት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ