የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/07 ገጽ 30
  • በእርግጥ ይህን ያህል ዓመት ኖረዋል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በእርግጥ ይህን ያህል ዓመት ኖረዋል?
  • ንቁ!—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት የጥንት ሰዎች በእርግጥ ረጅም ዕድሜ ኖረዋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የተፈጠርነው ለዘላለም እንድንኖር ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ኖኅ ካሰፈረው የግል ማስታወሻ ምን ትምህርት እናገኛለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የተራራው ማቱሳላ
    ንቁ!—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2007
g 7/07 ገጽ 30

በእርግጥ ይህን ያህል ዓመት ኖረዋል?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው አዳም 930 ዓመት እንዲሁም ሴት 912 ዓመት ኖረዋል። ማቱሳላ ደግሞ 969 ዓመት የኖረ ሲሆን አንድ ሺህ ሊሞላ የቀረው 31 ዓመት ብቻ ነበር! (ዘፍጥረት 5:5, 8, 27) በዚያ ዘመን የነበረው የአንድ ዓመት ርዝማኔ ከዛሬው ጋር እኩል ነው ወይስ ያንሳል? ምናልባት አንዳንዶች እንደሚሉት የዚያ ዘመን አንድ ዓመት በዛሬው ጊዜ አንድ ወር ከምንለው ጋር እኩል ይሆን?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት የዚያ ዘመን ዓመታት ርዝማኔ ከዛሬዎቹ ጋር ተመሳሳይ ነው። እስቲ የሚከተለውን ሁኔታ ልብ በል። የዚያ ዘመን አንድ ዓመት ርዝመት በዛሬው ጊዜ አንድ ወር ከምንለው ጋር እኩል ቢሆን ኖሮ ቀጥሎ የተገለጹት ሰዎች የልጅ አባት የሆኑት መውለድ በማይችሉበት ዕድሜ ላይ ይሆን ነበር። ለምሳሌ ያህል ቃይናን ልጅ የወለደው ስድስት ዓመት ሳይሞላው ሔኖክና መላልኤል ደግሞ በአምስት ዓመታቸው ነበር ማለት ነው።—ዘፍጥረት 5:12, 15, 21

ከዚህም በላይ የጥንት ሰዎች ታሪካቸው የተገለጸው ቀን፣ ወርና ዓመት እየተጠቀሰ ነው። (ዘፍጥረት 1:14-16፤ 8:13) እንዲያውም ስለ ኖኅ የሚናገረው ዝርዝር ታሪክ አንድ ወር ምን ያህል ርዝመት እንደነበረው ለይተን እንድናውቅ ይረዳናል። ዘፍጥረት 7:11, 24ን ከዘፍጥረት 8:3, 4 ጋር ስናነጻጽረው ከሁለተኛው ወር 17ኛ ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ወር 17ኛ ቀን ድረስ ያለው አምስት ወር ወደ ቀን ሲለወጥ 150 ቀን መሆኑን እንረዳለን። ከዚህ መረዳት እንደምንችለው ኖኅ አንድ ወር ያለው 30 ቀናትን ነው፤ አሥራ ሁለት ወራት ደግሞ ተደምረው አንድ ዓመት ይሆናሉ።—ዘፍጥረት 8:5-13a

ይሁን እንጂ ሰዎች 900 ዓመትና ከዚያ በላይ እንዴት ሊኖሩ ቻሉ? መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሰዎችን የፈጠረው ለዘላለም እንዲኖሩ እንደሆነና አለፍጽምናና ሞት ወደ ሰብዓዊው ቤተሰብ የገባው በአዳም ኃጢአት ምክንያት መሆኑን ይነግረናል። (ዘፍጥረት 2:17፤ 3:17-19፤ ሮሜ 5:12) ከጥፋት ውኃ በፊት ይኖሩ የነበሩት ሰዎች በዛሬው ጊዜ ከምንገኘው ይልቅ ለፍጽምና ቅርብ ስለነበሩ ረጅም ዓመት ሊኖሩ የቻሉበት ዋነኛ ምክንያት ይህ መሆኑ አያጠራጥርም። ለምሳሌ ያህል፣ ማቱሳላ የኖረው ከአዳም ሰባት ትውልድ በኋላ ነው።—ሉቃስ 3:37, 38

ይሁን እንጂ በቅርቡ ይሖዋ አምላክ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የሚያምኑ ሰዎች በአዳም ምክንያት የመጣባቸው ኃጢአት ሙሉ በሙሉ እንዲወገድላቸው ያደርጋል። “የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6:23) አዎን፣ ማቱሳላ የኖረበት 969 ዓመት በጣም አጭር የሚመስልበት ጊዜ ቀርቧል!

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ጥራዝ 2 ገጽ 1214ን ተመልከት።

[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ግራፍ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

1000

ማቱሳላ

አዳም

ሴት

900

800

700

600

500

400

300

200

100

በዛሬው ጊዜ የሰው አማካይ ዕድሜ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ