የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/07 ገጽ 9
  • ምሳሌ በመሆን አስተምሯቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምሳሌ በመሆን አስተምሯቸው
  • ንቁ!—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልጆችን ስለ አምላክ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? ከሁሉ የተሻለው ዘዴ የትኛው ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • እናንት ወላጆች፣ ልጆቻችሁን በፍቅር አሠልጥኗቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ልጆቻችን ውድ ስጦታ ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ አስተምሯቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2007
g 8/07 ገጽ 9

7

ምሳሌ በመሆን አስተምሯቸው

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የአንድ ሰው ተግባር ትምህርት ሊሰጥ ይችላል። ብዙውን ጊዜ ቃላት መረጃ ከማስተላለፍ ያለፈ ነገር አያከናውኑም። ለምሳሌ ያህል፣ ወላጆች ልጆቻቸው ሰው አክባሪዎች እንዲሆኑና እውነት እንዲናገሩ ያስተምሯቸው ይሆናል። ይሁን እንጂ እነዚሁ ወላጆች አንዳቸው በሌላው ላይ ወይም በልጆቻቸው ላይ የሚጮኹ ከሆነ እንዲሁም የማይፈልጉትን ኃላፊነት ላለመወጣት ሲሉ የሚዋሹ ከሆነ አዋቂዎች እንዲህ ማድረግ እንዳለባቸው ለልጆቹ እያስተማሯቸው ነው። ወላጆችን መኮረጅ “ልጆች ከሚማሩባቸው በጣም ጉልህ መንገዶች አንዱ ነው” በማለት ደራሲው ዶክተር ሳል ሰቪር ይናገራሉ።

ተፈታታኝ የሚሆነው ለምንድን ነው? ወላጆች ፍጹማን አይደሉም። ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል” በማለት ጽፏል። (ሮሜ 3:23) አንደበትን መቆጣጠርን በሚመለከት ደግሞ ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ምላስን መግራት የሚችል ማንም ሰው የለም” በማለት ጽፏል። (ያዕቆብ 3:8) ከዚህም በላይ ብዙውን ጊዜ ልጆች የወላጆቻቸውን ትዕግሥት የሚያስጨርስ ነገር ያደርጋሉ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ላሪ፣ ለወትሮው ረጋ ያለና ራሱን መግዛት የሚችል ሰው ቢሆንም “ልጆቼ ምን ያህል በቀላሉ እንደሚያስቆጡኝ ሳስበው ይገርመኝ ነበር” ብሏል።

መፍትሔው ምንድን ነው? ፍጹም ለመሆን ሳይሆን ጥሩ ምሳሌ ለመሆን ጥረት አድርጉ። ደግሞም አልፎ አልፎ የምትሠሯቸውን ስህተቶች ጠቃሚ ትምህርት ለማስተማር ተጠቀሙባቸው። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ክሪስ እንዲህ ብሏል:- “ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ ልጆቼን በጣም ከተቆጣኋቸው ወይም እነሱን የሚጎዳ መጥፎ ውሳኔ ካደረግሁ ስህተቴን አምኜ ይቅርታ እጠይቃለሁ። እንዲህ ማድረጌ ወላጆችም ጭምር ስህተት እንደሚሠሩና ሁላችንም ጠባያችንን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልገን ለልጆቼ አስተምሯቸዋል።” ቀደም ሲል የተጠቀሰው ኮስታስ “በጣም በምቆጣበት ጊዜ ይቅርታ ስለምጠይቅ ሴት ልጆቼም ስህተት በሚሠሩበት ጊዜ ይቅርታ መጠየቅን እንደተማሩ ተመልክቻለሁ” ብሏል።

ይሖዋ አምላክ “ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው” ብሏል። (ኤፌሶን 6:4) ልጆች፣ ሥልጣን ያለው ሰው የሚናገረውና የሚያደርገው ነገር መለያየቱን ሲመለከቱ የአዋቂዎችን ያህል፣ ምናልባትም ከእነሱ ይበልጥ ይቆጣሉ። እንግዲያው በየምሽቱ ራሳችሁን እንደሚከተሉት ያሉትን ጥያቄዎች ብትጠይቁ ጥሩ ነው:- ቀኑን ሙሉ ምንም ነገር ሳልናገር ብውል ኖሮ ልጆቼ ከተግባሬ ምን ትምህርት ያገኙ ነበር? ከተግባሬ ያገኙት ትምህርት በቃል ላስተምራቸው ከምፈልገው ጋር ይጣጣማል?

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

“አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን?”—ሮሜ 2:21

[በገጽ 9 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ወላጅ ይቅርታ ሲጠይቅ ልጁም እንዲሁ ማድረግን ይማራል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ