የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/08 ገጽ 30
  • ከአንባቢዎቻችን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከአንባቢዎቻችን
  • ንቁ!—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአንባቢዎቻችን
    ንቁ!—2008
  • ከአንባቢዎቻችን
    ንቁ!—2008
  • ከአንባቢዎቻችን
    ንቁ!—2008
  • እውነተኛ ፍቅርና ሰላም አገኘሁ
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2008
g 3/08 ገጽ 30

ከአንባቢዎቻችን

ወጣቶች ችግሩን እንዲቋቋሙ መርዳት (መጋቢት 2007) የ18 ዓመት ወጣት እንደመሆኔ መጠን የሞባይል ስልክንና የኢንተርኔት አጠቃቀምን አስመልክቶ የተሰጡትን አብዛኞቹን ነጥቦች ከግል ሕይወቴ ጋር ለማዛመድ ችያለሁ። ማኅበራዊ ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችሉ የተለያዩ የኢንተርኔት ድረ ገጾች አማካኝነት ከማላውቃቸው በርካታ ሰዎች ጋር ተገናኝቻለሁ። ብዙም ሳይቆይ ከመጥፎ ባልንጀራ ጋር መግጠም በሚያመጣው ወጥመድ ውስጥ እንደገባሁ ተሰማኝ። ወዲያውኑ ለማለት ይቻላል መንፈሳዊነቴ መዳከም ጀመረ። እንዲያውም ከአንዳንዶቹ ግለሰቦች ጋር በአካል ለመገናኘት እስከ መስማማት ደርሼ ነበር። የሚያሳዝነው እንዲህ ያለው አካሄድ ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት ወደ መፈጸም መርቶኛል። ይህ ርዕሰ ትምህርት ሌሎች እንደ እኔ ያለ ሥቃይና ጭንቀት እንዳይደርስባቸው ይረዳቸው ዘንድ እጸልያለሁ። እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር የማሳልፋቸው ሌሊቶችና ድንገት ትዝ የሚሉኝ ድርጊቶች እያንዳንዱን ቀን አስቸጋሪ እያደረጉብኝ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ሰይጣንን መቃወሜን እቀጥላለሁ።

ቢ. አር፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ራሴን የምስተው ለምንድን ነው? (ሚያዝያ 2007) ራስን በመሳት ችግር የምሠቃየው እኔ ብቻ አለመሆኔን ማወቄ አጽናንቶኛል። ይህ ርዕሰ ትምህርት ይሖዋ፣ “ችግርሽ ገብቶኛል፣ እስቲ አንዳንድ ማበረታቻዎችን ልስጥሽ” በማለት በቀጥታ ያነጋገረኝ ያህል እንዲሰማኝ አድርጎኛል።

አይ. አር.፣ ማዳጋስካር

ከሥነ ጥበብ ይበልጥ ዘለቄታ ያለው ነገር (ሚያዝያ 2007) ለዚህ ተሞክሮ ምን ያህል አመስጋኝ እንደሆንኩ መግለጽ ያዳግተኛል። ታዋቂ በሆኑ ሁለት የፎቶ ግራፍ ስቱዲዮዎች ውስጥ ለስድስት ዓመታት ያህል በአስተዳዳሪነት ሠርቻለሁ። የፈጠራ ችሎታዬን ለመጠቀም የሚያስችለኝን ይህን ሥራዬን እወደው ነበር። ሆኖም በሥራዬ የማገኘው ስኬትና ዝና እየጨመረ ሲመጣ ለይሖዋ የማቀርበው አገልግሎት እየቀነሰ እንደመጣ አስተዋልኩ። በሥራው እጅግ ከመዋጤ የተነሳ ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን እምብዛም ጊዜ አልነበረኝም። አንድ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈገኝ ተረዳሁ። በመሆኑም ሥራዬን በመተው ለአምልኮቴ ይበልጥ ትኩረት መስጠት ጀመርኩ። እንደ እውነቱ ከሆነ ፎቶ ግራፍ በማንሳት የማገኘው እርካታና ደስታ በክርስቲያን አገልግሎት ከማገኘው ደስታ ጋር ሊወዳደር አይችልም።

ኤ. ፒ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የወጣቶች ጥያቄ . . . ይህ ሰው ጥሩ የትዳር ጓደኛ ሊሆነኝ ይችላል? (ግንቦት 2007) በቅርቡ፣ ይሆነኛል ብዬ ካሰብኩት አንድ ሰው ጋር ፍቅር እንደያዘኝ ተገነዘብኩ። ሆኖም ይህን ርዕሰ ትምህርት ካነበብኩ በኋላ ልጁን እንድወደው ያደረጉኝ ባሕርያት ያን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆኑ ተረዳሁ። ርዕሰ ትምህርቱ፣ ከሁሉም ይበልጥ ትኩረት መስጠት የሚገባው ለመንፈሳዊ ባሕርያትና ለትዳር ያሰብነው ሰው ሌሎችን ለሚይዝበት መንገድ መሆኑን እንድገነዘብ አስችሎኛል። እኛ ወጣቶችን ከክፉ ለመጠበቅ እንዲሁም ለእኛ መመሪያ ለመስጠት ሲባል ለሚዘጋጁልን እንደዚህ ላሉ ርዕሰ ትምህርቶች ይሖዋን አመሰግነዋለሁ።

ኢ. ፒ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ከምሥራቅ ቲሞር ሕዝብ ጋር ተዋወቅ (ግንቦት 2007) ይህን ርዕሰ ትምህርት ያነበብኩት በከፍተኛ ጉጉት ነው። ስለዚህች አገር መጀመሪያ የሰማሁት በአገሪቱ ስለነበረው ብጥብጥ በዜና ሲነገር ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የምሥራቅ ቲሞር ሕዝብ ችግሩን እንዴት እንደተቋቋመና በዚያ የነበረው ብጥብጥ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ ለማወቅ በጣም እጓጓ ነበር። ጭካኔ የተሞላበት ሁኔታ ሳይበግራቸው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን የሚያከናውኑት እነዚህ ሰዎች ባላቸው ጥንካሬ ተደንቄያለሁ። የምሥራቅ ቲሞርን ሕዝብ መንፈሰ ጠንካራነት እንዲሁም የጃኮብና የቤተሰቡ ፈገግታ ከአእምሮዬ አይጠፉም።

ዋይ. ኤም.፣ ጃፓን

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ