የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/09 ገጽ 24
  • የበራሪ ፍጥረታት ክንፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የበራሪ ፍጥረታት ክንፍ
  • ንቁ!—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በምድር ወገብ አካባቢ የሚገኘው ደን በራሪ አትክልተኞች
    ንቁ!—2014
  • በጆሮዋ “የምታየው” የሌሊት ወፍ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • አስገራሚው የሦስት አፅቄዎች ዓለም
    ንቁ!—2000
ንቁ!—2009
g 2/09 ገጽ 24

ንድፍ አውጪ አለው?

የበራሪ ፍጥረታት ክንፍ

◼ ከአውሮፕላንና እንደ ሌሊት ወፍ፣ ነፍሳትና ወፍ ካሉት ፍጥረታት በበረራ ላይ ይበልጥ እንደልብ መንቀሳቀስ የሚችለው የትኛው ይመስልሃል? ብታምንም ባታምንም፣ አውሮፕላን ከእነዚህ አስደናቂ ፍጥረታት ጋር ፈጽሞ የማይወዳደር ሲሆን እነዚህ ፍጥረታት “ኃይለኛ ነፋስ፣ ዝናብና በረዶ ባለበት ጊዜም እንኳን ሳይቀር እየበረሩ የመቆየት አስደናቂ ችሎታ ያላቸው” መሆኑን በሚሺጋን ዩኒቨርሲቲ የበረራ መሣሪያ ምሕንድስና ፕሮፌሰር የሆኑት ዌይ ሸ የተባሉ ሰው ተናግረዋል።a ለዚህ ሚስጥሩ ምንድን ነው? ሚስጥሩ ያለው በሚርገበገቡት ክንፎቻቸው ላይ ነው፤ ይህም የሰው ልጅ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አብራሪዎች ሲቀኑበት የነበረ ጉዳይ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አንዳንድ ወፎችና ነፍሳት በሚበሩበት ወቅት ከአካባቢው ሁኔታ ጋር ለመስማማት የክንፎቻቸውን ቅርጽ ያለማቋረጥ ይለዋውጣሉ። ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ተንሳፈው ለመቆየትና በቅጽበት አቅጣጫቸውን ለመቀየር ያስችላቸዋል። ሳይንስ ኒውስ የተሰኘው መጽሔት በሌሊት ወፎች ላይ የተስተዋለውን ሁኔታ እንዲህ በማለት ዘግቧል፦ “የሌሊት ወፎች በሴኮንድ 1.5 ሜትር በሆነ ዝቅተኛ ፍጥነት በሚበሩበት ጊዜ ወደ ላይ ለመወንጨፍ የክንፎቻቸውን ጫፎች ገልብጠውና ወደኋላ አድርገው በፍጥነት ያርገበግቧቸዋል። ወፎችን ለመንሳፈፍና ወደፊት ለመብረር የሚያስችላቸው . . . ይህ ዘዴ ሳይሆን እንደማይቀር የሳይንስ ሊቃውንት ይገምታሉ።”

እርግጥ ነው፣ ስለ በራሪ ፍጥረታት ገና ብዙ ያልታወቁ ነገሮች አሉ። በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካልና የበረራ መሣሪያ ምሕንድስና ፕሮፌሰር የሆኑት ፒተር ኢፍዩ “እንዲህ በአየር ላይ ሊንሳፈፉ የሚችሉት አየሩን ምን ቢያደርጉት ነው?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። አክለውም እንዲህ ብለዋል፦ “ከመብረር ችሎታ ጋር የተያያዙ ፈጽሞ ያልተረዳናቸው ብዙ ዓይነት የፊዚክስ ሕጎች አሉ። [ወፎችና ነፍሳት] ሲበሩ ማየት ብንችልም እንቅስቃሴያቸው ከከባቢው አየር ጋር ያለውን ግንኙነት መረዳት ግን አልቻልንም።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? በራሪ ፍጥረታት ያላቸው እንደልብ የሚታዘዝላቸው ክንፍ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ክንፍ ያላቸው በርካታ ፍጥረታት በዝናብ ውስጥ መብረር ቢችሉም አብዛኞቹ ግን የሚጠለሉበት ቦታ ይፈልጋሉ።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጠፍጣፋ መንቆር ያላት ሃሚንግበርድ

[ምንጭ]

Laurie Excell/Fogstock/ age fotostock

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የአይጥ ዓይነት ጆሮ ያላት የሌሊት ወፍ

[ምንጭ]

© Delpho, M/age fotostock

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ