የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 5/09 ገጽ 24
  • የሳይፎኪለስ ጥንዚዛ ቅርፊት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሳይፎኪለስ ጥንዚዛ ቅርፊት
  • ንቁ!—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥንዚዛ ቅርፊት
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • ጥንዚዛ መርዝ የምትረጭበት መንገድ
    ንቁ!—2008
  • ጥቁር የእሳት ጥንዚዛ ያሉት ጠቋሚዎች
    ንቁ!—2012
  • እርጥበት የመሳብ ችሎታ ያለው የናሚብ ጥንዚዛ ክንፍ ሽፋን
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2009
g 5/09 ገጽ 24

ንድፍ አውጪ አለው?

የሳይፎኪለስ ጥንዚዛ ቅርፊት

◼ የሳይፎኪለስ ጥንዚዛ የላይኛው ቅርፊት የተሠራው ከሰው ፀጉር በአሥር እጥፍ ከሚሳሱና አንዱ በአንዱ ላይ ከተነባበሩ ቀጫጭን ክር መሳይ ነገሮች ነው። በብሪታንያ በኤክሴተር ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩት ዶክተር ፒት ቪኩሲች “ቅርፊቶቹን በኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ ሳያቸው ሌላ ዓለም የምመለከት መሰለኝ፤ እጅግ የሚያስደንቅ ነበር” በማለት ተናግረዋል።

እስቲ አስበው፦ ቪኩሲች ያደረጉት ምርምር፣ የጥንዚዛው ቅርፊት በጣም ነጭ እንዲሆን ያደረገው ምን እንደሆነ ለማወቅ አስችሏል። ቅርፊቱ ነጭ የሆነው ማቅለሚያ ንጥረ ነገር ስላለው ሳይሆን ቅርፊቱ የተሠራባቸው ክር መሳይ ነገሮች በጣም ቀጫጭን መሆናቸውና በመካከላቸው ያለው ክፍተት ብርሃንን አስገራሚ በሆነ መንገድ ለማንጸባረቅ የሚያስችል መሆኑ ነው። “ከፍተኛ ጥራት ባለው ወረቀትና በፕላስቲኮች ላይ እንዲሁም በአንዳንድ ቀለሞች ውስጥ እንደሚገኙት ያሉ በፋብሪካ ውስጥ ከማዕድኖች የሚዘጋጁ ቀለሞች የጥንዚዛውን ቅርፊት ያህል ንጣት እንዲኖራቸው በእጥፍ መወፈር ያስፈልጋቸዋል” በማለት ሳይንስ ዴይሊ ዘግቧል።

የሳይንስ ሊቃውንት፣ የዚህ ጥንዚዛ ቅርፊት ጥንዚዛው ብዙውን ጊዜ በሚኖርበት ሥፍራ ከሚገኘው ነጭ ፈንገስ ጋር እንዲመሳሰል እንደሚረዳው ያምናሉ። ይሁን እንጂ የባለሙያዎቹን ቀልብ ይበልጥ የሳበው ስለዚህ ትንሽ ጥንዚዛ ቀለም ያገኙት እውቀት፣ ከፍተኛ ንጣት ያለው ሰው ሠራሽ ነገር በመሥራት ረገድ ለሰዎች ሊሰጥ የሚችለው ጥቅም ነው። “ቴክኖሎጂ ከዚህ ጥንዚዛ ትምህርት ቀስሞ ንድፉን በሥራ ላይ ቢያውል” የምንጽፍበትን ወረቀትና የጥርሳችንን ንጣት የመሳሰሉ ነገሮችን፣ ሌላው ቀርቶ የብርሃንን ድምቀት እንኳ “በእጅጉ ማሻሻል እንደሚቻል” ቪኩሲች ያምናሉ።

ምን ይመስልሃል? የሳይፎኪለስ ጥንዚዛ ነጭ ቅርፊት እንዲሁ በአጋጣሚ የመጣ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

“የሳይፎኪለስ” ጥንዚዛ ከጣትህ ጫፍ አይበልጥም (ፎቶግራፉ እንዲተልቅ ተደርጓል)

[ምንጭ]

Department of Ento Department of Entomology, Kasertsart University, Bangkok

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ