የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/10 ገጽ 31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2010
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ውሳኔ ነበር?
  • ስለ ንጉሥ ሳኦል ምን የምታውቀው ነገር አለ?
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • ከዚህ እትም
  • በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 1/10 ገጽ 31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ጥሩ ውሳኔ ነበር?

ዘፍጥረት 39:1-23ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. በዚህ ሥዕል ላይ የምትታየው ሴት ማን ነች?

․․․․․

2. ሰውየውስ ማን ነው?

․․․․․

3. ሰውየው ምን ዓይነት ውሳኔ አደረገ?

․․․․․

ለውይይት፦

ሰውየው ይህን ውሳኔ ያደረገው ለምንድን ነው? በዚህ ምክንያትስ የደረሰበት ችግር ነበር? ትክክለኛ ውሳኔ ያደረገ ይመስልሃል? አድርጓል ካልክ ለምን? ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ በመወሰንህ ችግር ሊያጋጥምህ የሚችለው መቼ ሊሆን ይችላል?

ስለ ንጉሥ ሳኦል ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. ሳኦል ምን ዓይነት የሰውነት አቋም ነበረው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 9:1, 2ን አንብብ።

․․․․․

5. ይሖዋ ሳኦልን የተወው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 13:13, 14ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ከአንድ ሰው አካላዊ ቁመና ይበልጥ አምላክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምኑ ነው? ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 16:6, 7ን አንብብ። ይህን ሐቅ ማወቅህ ስለ አካላዊ ቁመናህ ሚዛናዊ አመለካከት እንድትይዝ የረዳህ እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 1 ጢሞቴዎስ 4:8ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን በተመለከተ ምን ማበረታቻ ይዟል? መክብብ 3:․․․

ገጽ 7 የምንሠራው ለምን መሆን አለበት? ዮሐንስ 6:․․․

ገጽ 10 አምላክ ምን ለማድረግ ቀን ወስኗል? የሐዋርያት ሥራ 17:․․․

ገጽ 28 አንድ ወንድና ሴት ሲጋቡ ምን ይሆናሉ? ዘፍጥረት 2:․․․

● መልሱ በገጽ 14 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. የጲጥፋራ ሚስት።

2. ዮሴፍ።

3. ከጲጥፋራ ሚስት ጋር ላለመተኛት።

4. ሳኦል ቁመቱ ረጅምና መልከ ቀና ነበር።

5. ሳኦል አምላክን አልታዘዘም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ