የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/10 ገጽ 29
  • የዓሣ አመቴ ምንቃር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዓሣ አመቴ ምንቃር
  • ንቁ!—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በቀለማት ያሸበረቀው ዓሣ አመቴ
    ንቁ!—2010
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2010
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2010
  • ጎማ አልባ ባቡር
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 4/10 ገጽ 29

ንድፍ አውጪ አለው?

የዓሣ አመቴ ምንቃር

● በሰዓት 300 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚጓዘው የጃፓን የመንገደኞች ባቡር በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ፈጣን ባቡሮች አንዱ ነው። ባቡሩ ይህን ያህል ፈጣን እንዲሆን አስተዋጽኦ ካደረጉት ነገሮች መካከል ዓሣ አመቴ የምትባለው ትንሽ ወፍ ትገኝበታለች። እንዴት?

እስቲ አስበው፦ ዓሣ አመቴ፣ የምትወደውን ምግብ ለማግኘት ቁልቁል ወደ ውኃ ውስጥ የምትገባው ምንም ሳታንቦጫርቅ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ሁኔታ ፈጣኑን ባቡር የመሞከሩን ሂደት የሚመራውን ኤይጂ ናካትሱ የሚባለውን መሐንዲስ ትኩረት ሳበው። አየር ያለው የግፊት መጠን ከውኃ ያነሰ ሆኖ ሳለ ይህች ወፍ ይህን ለውጥ ግምት ውስጥ በማስገባት ውኃው ሳይረበሽ ሰንጥቃ መግባት የቻለችው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ጥረት አደረገ። ይህን ሚስጥር መረዳቱ በፈጣኑ ባቡር አሠራር ላይ የገጠመውን ለየት ያለ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ቁልፍ ነበር። ናካትሱ እንዲህ ብሏል፦ “አንድ ባቡር በከፍተኛ ፍጥነት እየበረረ ጠባብ ወደሆነ የመሬት ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲገባ በአየሩ ውስጥ ኃይለኛ ግፊት እንዲፈጥር የሚያደርግ ሲሆን ይህ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ከማዕበል ጋር የሚመሳሰሉ ሞገዶችን ይፈጥራል። እነዚህ ሞገዶች በድምፅ ፍጥነት በመጓዝ ወደ መተላለፊያው መውጫ ይደርሳሉ፤ በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ድምፅና ንዝረት ስለሚፈጠር በ400 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።”

የፈጣኑ ባቡር የፊት ክፍል ከዓሣ አመቴ ምንቃር ጋር በሚመሳሰል መንገድ እንዲሠራ ውሳኔ ተደረገ። ታዲያ ይህ ምን ውጤት አስገኘ? ፈጣኑ ባቡር በአሁኑ ጊዜ ፍጥነቱ 10 በመቶ የጨመረ ከመሆኑም በላይ የኃይል ፍጆታው 15 በመቶ ቀንሷል። በተጨማሪም ባቡሩ ወደ መሬት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲገባ የሚፈጥረው የአየር ግፊት 30 በመቶ ቀንሷል። በመሆኑም ባቡሩ በመተላለፊያው በኩል በሚያልፍበት ጊዜ ይሰማ የነበረው ኃይለኛ ድምፅ ቀርቷል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የዓሣ አመቴ ምንቃር እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Kingfisher diving: Woodfall/Photoshot; bullet train: AP Photo/Kyodo

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ