የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/11 ገጽ 15
  • የተገለበጠ ሬቲና

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተገለበጠ ሬቲና
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከዓይንህ ፊት የሚንቀሳቀሱ ጉድፍ መሳይ ነገሮች አሉን?
    ንቁ!—2000
  • የሮቦት ንድፍ አውጪ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?
    ንቁ!—2013
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
  • ፍጥረት ቀድሟቸዋል
    ንቁ!—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 1/11 ገጽ 15

ንድፍ አውጪ አለው?

የተገለበጠ ሬቲና

● በሰው ዓይን ውስጥ ሬቲና የሚባል ክፍል አለ፤ ሬቲና በግምት 120 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴሎች ያሉት ሲሆን ፎቶሪሰፕተር የሚባሉት እነዚህ ሴሎች የብርሃን ጨረሮችን ተቀብለው ወደ ኤሌክትሪክ መልእክት ይለውጣሉ። አንጎልህ እነዚህን መልእክቶች ወደ ምስል ይቀይራቸዋል። የዝግመተ ለውጥ አማኞች፣ የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ሬቲና በዓይናቸው ውስጥ የተቀመጠበት ቦታ ዓይን ንድፍ አውጪ እንደሌለው ያረጋግጣል የሚል የመከራከሪያ ሐሳብ ያቀርባሉ።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ሬቲና አቀማመጥ የተገለበጠ ነው፤ ይህም ሲባል ፎቶሪሰፕተር የሚባሉት ሴሎች የሚገኙት በሬቲናው የፊተኛ ሳይሆን የኋለኛ ክፍል ነው ማለት ነው። በመሆኑም ብርሃን እነዚህ ሴሎች ላይ ለመድረስ በርካታ የሴሎች ንጣፎችን ማለፍ ይኖርበታል። የዝግመተ ለውጥ የባዮሎጂ ባለሙያ የሆኑት ኬነት ሚለር እንደሚሉት ከሆነ ፎቶሪሰፕተር የተባሉት ሴሎች “በዚህ መንገድ መቀመጣቸው ብርሃን እንዲበታተን ስለሚያደርግ ሊኖረን የሚችለውን ያህል ጥርት ያለ እይታ እንዳይኖረን አስተዋጽኦ አድርጓል።”

በመሆኑም የዝግመተ ለውጥ አማኞች የሬቲና አቀማመጥ የተገለበጠ መሆኑ ጥሩ ንድፍ እንደሌለው እንዲያውም እስከ ጭራሹ ንድፍ እንደሌለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንደሆነ ይገልጻሉ። እንዲያውም አንድ ሳይንቲስት፣ የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ሬቲና “አሠራሩ ግራ የሚያጋባ ፊቱ ወደኋላ የዞረ አቀማመጥ” እንዳለው እስከ መናገር ደርሰዋል። ይሁን እንጂ ፎቶሪሰፕተር የተባሉት ሴሎች በሬቲናው ውስጥ የተቀመጡበት ቦታ በጣም ተስማሚ መሆኑን ተጨማሪ ጥናቶች አሳይተዋል፤ እነዚህ ሴሎች ለጥሩ የማየት ችሎታ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችንና ኦክስጅንን ከሚያቀርበው ፒግመንት ኤፒተልየም ከተባለው የሴሎች ንጣፍ አጠገብ ናቸው። ጄሪ በርግመን የተባሉ የባዮሎጂ ባለሙያ እና ጆሴፍ ካልኪንስ የተባሉ የዓይን ሐኪም “የፒግመንት ኤፒተልየም ሕዋሶች ከሬቲና ፊት ቢሆኑ ኖሮ የማየት ችሎታችን በእጅጉ ይቀንስ ነበር” በማለት ጽፈዋል።

የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ሬቲና የተገለበጠ መሆኑ በተለይ ትናንሽ ዓይኖች ላሏቸው በጣም ጠቃሚ ነው። በስዊድን የለንድ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሮናልድ ክሮገ እንዲህ ብለዋል፦ “ጥርት ያለ እይታ እንዲኖር በዓይን ሌንስና ፎቶሪሰፕተር በተባሉት ሴሎች መካከል የተወሰነ ርቀት መኖር አለበት። ይህ ቦታ በነርቭ ሴሎች መሞላቱ የጀርባ አጥንት ላላቸው እንስሳት ቦታ ይቆጥብላቸዋል።”

በተጨማሪም የሬቲና ነርቭ ሴሎች አንድ ላይ መታመቃቸውና ፎቶሪሰፕተር ከተባሉት ሴሎች አጠገብ መሆናቸው በዓይናችን የሚገባውን መረጃ በፍጥነትና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስተላለፍ ያስችላል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የተገለበጠ ሬቲና አሠራር ጥራት የሌለው ነው? ደግሞስ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ፎቶሪሰፕተር ሴሎች

ብርሃን

ፒግመንት ኤፒተልየም

ብርሃን

ሬቲና

ኦፕቲክ ነርቭ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ