የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/11 ገጽ 25
  • የግንደ ቆርቁር ተርብ ኦቪፖዚተር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የግንደ ቆርቁር ተርብ ኦቪፖዚተር
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
  • የወረቀት ሠሪ ተርብ በደመነፍስ የተገኘ የምሕንድስና ችሎታ
    ንቁ!—2012
  • ጥርስህን የማፋጨት ልማድ አለህን?
    ንቁ!—1998
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
ንቁ!—2011
g 3/11 ገጽ 25

ንድፍ አውጪ አለው?

የግንደ ቆርቁር ተርብ ኦቪፖዚተር

● እንስቷ ግንደ ቆርቁር ተርብ እንቁላሎቿን በአርዘ ሊባኖስ ዛፍ ግንድ ውስጥ ታስቀምጣለች፤ ይህን ለማድረግ የምትጠቀምበት ዘዴ ሳይንቲስቶችን በጣም ቀልጣፋና ብዙም ጉዳት የማያስከትል የቀዶ ጥገና መሣሪያ ለመፈልሰፍ አነሳስቷቸዋል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ግንደ ቆርቁር ተርብ የአርዘ ሊባኖስን ግንድ የምትቦረቡረው ኦቪፖዚተር (ማንቋለያ) በሚባለው የሰውነቷ ክፍል በመጠቀም ነው፤ ኦቪፖዚተር እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት ዘንጎች ያሉት እንደ መርፌ ያለ ቱቦ ሲሆን እያንዳንዱ ዘንግ ወደኋላ የዞሩ ጥርሶች አሉት። በአንደኛው ዘንግ ላይ ያሉት ጥርሶች እንጨቱን ቆንጥጠው ሲይዙ ሌላኛው ዘንግ በተወሰነ መጠን ወደፊት ይንሸራተታል። ከዚያም የዚህኛው ዘንግ ጥርሶች ግንዱን ቆንጥጠው ሲይዙ የመጀመሪያው ዘንግ ወደፊት ይሄዳል። ዘንጎቹ በዚህ መንገድ በየተራ እንጨቱን መቆንጠጣቸውና ወደፊት መንሸራተታቸው ኦቪፖዚተሩ ብዙም ኃይል ሳያባክን እንዲሁም የመታጠፍም ሆነ የመሰበር አደጋ ሳያጋጥመው እንጨቱን እስከ 20 ሚሊ ሜትር በሚደርስ ጥልቀት እንዲቦረቡር ያስችለዋል።

ሳይንቲስቶች የእንስቷን ግንደ ቆርቁር ተርብ ኦቪፖዚተር በመመልከት በተመሳሳይ መንገድ የሚሠራ በነርቭ ሥርዓት ላይ ቀዶ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ለሙከራ ሠርተዋል። ከሲሊከን የተሠራው የዚህ መሣሪያ መርፌ እየተፈራረቁ የሚሠሩ ሁለት ዘንጎች ሲኖሩት እያንዳንዱ ዘንግ ይህ ነው የሚባል ጉዳት ሳያደርሱ አንጎል ውስጥ ጠልቀው መግባት የሚችሉ ጥቃቅን ጥርሶች አሉት። ይኸው መሣሪያ ተጨማሪ ገጽታዎችም ይኖሩታል። ኒው ሳይንቲስት መጽሔት እንደሚለው “መሣሪያው በአሁኑ ጊዜ እንዳሉት የቀዶ ጥገና መሣሪያዎች ግትር ያለ ሳይሆን እንደ ልብ የሚተጣጠፍ በመሆኑ በቀዶ ጥገና ወቅት በቀላሉ ጉዳት ሊደርስባቸው የሚችሉ የአንጎል ክፍሎችን ትቶ ብዙም በማይጎዱ ክፍሎች በኩል ማለፍ ይችላል።” እንዲህ ያለው መሣሪያ በቀላሉ የማይደረስባቸውን የአካል ክፍሎች ለማግኘት ሲባል ሰውነትን ብዙ ቦታ ከመቅደድ ያድናል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የእንስት ግንደ ቆርቁር ተርብ ኦቪፖዚተር እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

አንደኛው ዘንግ ወደ ታች በመንሸራተት እንጨቱን ሲቦረቡር ሌላኛው ዘንግ በጥርሶቹ እንጨቱን ቆንጥጦ ይይዛል

እንጨት

በየተራ የሚንቀሳቀሱት ዘንጎች

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል ምንጭ]

Wasp: David R. Lance, USDA APHIS PPQ, Bugwood.org; diagram: J. F. V. Vincent and M. J. King, (1996). The mechanism of drilling by wood wasp ovipositors. Biomimetics, 3: 187-201

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ