የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/11 ገጽ 26
  • ሳንድካስል የተባለው ትል ሙጫ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሳንድካስል የተባለው ትል ሙጫ
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
  • ዛጎል አልባ ቀንድ አውጣ የሚያመነጨው የሚያጣብቅ ዝልግልግ ፈሳሽ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • የባርናክሎች ሙጫ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • ዕጹብ ድንቅ የሆነው ባሕረ ሰላጤ
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 4/11 ገጽ 26

ንድፍ አውጪ አለው?

ሳንድካስል የተባለው ትል ሙጫ

● የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች የተሰበሩ አጥንቶችን የሚያያይዙት በስፒሎች፣ በብሎኖችና በቀጭን ብረቶች ነው፤ ይሁንና እነዚህ መሣሪያዎች የተሰበሩ ትንንሽ አጥንቶችን ለማያያዝ በጣም ስለሚተልቁ አይመቹም። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተመራማሪዎች እርጥበት ባለው የሰው ልጅ አካል ውስጥ ሊደርቅ የሚችል ሙጫ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ግራ ተጋብተው ነበር። ሳንድካስል የተባለውን ትል በማጥናት መፍትሔ ሊሆን የሚችል ነገር አግኝተዋል!

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሳንድካስል የተባለው ትል፣ የቱቦ ቅርጽ ያለውን ቤቱን ውኃ ውስጥ የሚሠራው ከአሸዋና ከባሕር እንስሳት ቅርፊት ወይም ዛጎል ቅንጣቶች ነው። እያንዳንዱ ቅንጣት ከሌላው ቅንጣት ጋር የሚጣበቀው ትሉ በሚያመነጨው ሙጫ ሲሆን ትሉ ሙጫውን የሚሠራው በደረቱ አካባቢ በሚገኝ እጢ ነው። ይህ ሙጫ በአሁኑ ጊዜ ካሉት ሰው ሠራሽ ማጣበቂያዎች ሁሉ የላቀ ነው። ትሉ የሚሠራው ሙጫ ለየት ያሉ ፕሮቲኖችን የያዘ ሲሆን እነዚህ ፕሮቲኖች ሲቀላቀሉ ሙጫው ውኃ ውስጥ ቶሎ እንዲደርቅ ያደርጉታል። በእርግጥም ሳንድካስል የተባለው ትል፣ የተዋጣለት ግንበኛ ተብሎ መጠራቱ ተገቢ ነው። የዩታ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ራስል ስቱዋርት ይህ ትንሽ ፍጥረት “ነገሮችን ከማጣበቅ ጋር በተያያዘ በጣም ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን” ለመፍታት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ተመራማሪዎች ሳንድካስል የተባለው ትል ሙጫ የሚሠራበትን መንገድ በመኮረጅ ትሉ ከሚያመነጨው ሙጫ እንኳ ይበልጥ ጥንካሬ ያለው ሰው ሠራሽ ማጣበቂያ መሥራት ችለዋል። በቀዶ ጥገና ክፍሎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ሙጫ የተሰበረው አጥንት ከተጠገነ በኋላ ሟሙቶ ሊጠፋ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ይህ ሙጫ በሰው ልጆች ላይ ተሞክሮ ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ አንድ ትልቅ የሕክምና ግኝት ይሆናል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ሳንድካስል የተባለው ትል የሚያመነጨው ልዩ የሆነ ሙጫ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ተመራማሪዎች የተሰበሩ አጥንቶችን የብረት ማያያዣ ሳያስፈልጋቸው መጠገን እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Sandcastle worm: © Peter J. Bryant, University of California, Irvine

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ