የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/11 ገጽ 28
  • የአእዋፍ እንቁላል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአእዋፍ እንቁላል
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተአምረኛው የሰጎን እንቁላል
    ንቁ!—2002
  • የሰው ልጅ የፈጣሪን ጥበብ ይኮርጃል
    ንቁ!—2003
  • የሰው ሕይወት የሚጀምረው መቼ ነው?
    ንቁ!—2009
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 9/11 ገጽ 28

ንድፍ አውጪ አለው?

የአእዋፍ እንቁላል

● የአእዋፍ እንቁላል “ተአምራዊ ማሸጊያ” ተብሎ ይጠራል። እንዲህ ዓይነት ስያሜ ያተረፈው ለምንድን ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ በካልሲየም የበለጸገው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ሙሉ በሙሉ ድፍን ቢመስልም በአጉሊ መነጽር ብቻ ሊታዩ የሚችሉ እስከ 8,000 የሚደርሱ ቀዳዳዎች አሉት። እነዚህ ቀዳዳዎች ኦክስጅን ወደ ውስጥ እንዲገባና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከውስጥ እንዲወጣ የሚያስችሉ ሲሆን ይህ ደግሞ በእንቁላሉ ውስጥ ያለው ሽል መተንፈስ እንዲችል በእጅጉ ይረዳዋል። ያም ቢሆን ግን ቅርፊቱና ከሥሩ ያሉት የተለያዩ ስስ ሽፋኖች ባክቴሪያዎች ሽሉን እንዳይጎዱት ይከላከላሉ። ከፍተኛ መጠን ያለው ውኃ የያዘው አልቡሚን የተባለ ዝልግልግ ፈሳሽ፣ እንቁላሉ ተንገጫግጮ አስኳሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ያደርጋል።

ተመራማሪዎች የእንቁላልን አሠራር በመኮረጅ ግጭትን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም የሚችሉ ነገሮችን እንዲሁም ፍራፍሬዎች በባክቴሪያዎችና በጥገኛ ተሕዋስያን እንዳይበከሉ የሚከላከሉ ማሸጊያዎችን የመሥራት ፍላጎት አላቸው። ይሁን እንጂ ማሪያን ቦታ ዲነ፣ ቪቫይ በተሰኘው መጽሔት ላይ እንደገለጹት “ተፈጥሮን መኮረጅ እንዲህ የዋዛ አይደለም።” እኚህ ሴት እንደገለጹት እስከ አሁን የተደረጉት ሙከራዎች በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? እንዲህ ያለው “ተአምራዊ ማሸጊያ” ማለትም የአእዋፍ እንቁላል እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

የአንድ እንቁላል ውስጣዊ ገጽታ

ቅርፊት

አስኳል

ካላዛ (የአስኳል ማሰሪያ)

ውጭኛ ሽፋን

ውስጠኛ ሽፋን

የዘር እምብርት (ሽል የሚፈጠርበት)

ስስ አልቡሚን

ወፍራም አልቡሚን

የአየር ቦታ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ