የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/12 ገጽ 11-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ሳሙኤል እውነተኛውን አምልኮ አስፋፍቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢኖሩም ጸንቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢያጋጥሙትም ጸንቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 2/12 ገጽ 11-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

አንደኛ ሳሙኤል 1:24-28ን እና 2:11ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

[ሰንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

የሳሙኤል ወላጆች፣ ልጃቸው ሕይወቱን እንዴት እንዲጠቀምበት ፈልገው ነበር? ይሖዋ ሳሙኤልን የባረከው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 3:19-21⁠ን አንብብ።

ይሖዋን ለማክበር ምን ዓይነት ግቦችን ማውጣት ትችላለህ?

ፍንጭ፦ መክብብ 12:13⁠ን እና 1 ጢሞቴዎስ 4:6-8, 12, 13⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦ አንድ የቤተሰባችሁ አባል ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ያደረገውን ነገር ምንም ድምፅ ሳይሰማ በእንቅስቃሴ ያሳይ። የቀሩት የቤተሰብ አባላት ደግሞ ማንን እያስመሰለ እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 14 ሳሙኤል

ጥያቄ

ሀ. የሳሙኤል ወላጆች ․․․․․ እና ․․․․․ ይባላሉ።

ለ. ይሖዋ፣ ሳሙኤልን የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንዲጽፍ ተጠቅሞበታል?

ሐ. መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ይህንን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “ብላቴናውም ሳሙኤል . . .”

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

1100ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ ሳሙኤል የኖረበት ዘመን

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

የተወለደው በራማ ሲሆን ወደ ሴሎ ተዛውሯል

ራማ

ሴሎ

ኢየሩሳሌም

ሳሙኤል

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ወላጆቹ ‘ለእግዚአብሔር የሰጡት’ ሲሆን ከልጅነቱ አንስቶ ሕይወቱን ሙሉ አምላክን እንዲያገለግል አበረታተውታል። (1 ሳሙኤል 1:24, 28) ሳሙኤል፣ ምግባረ ብልሹ የነበሩ ካህናት ሌሎችን መጠቀሚያ ሲያደርጉ ይመለከት የነበረ ቢሆንም ምንጊዜም ታማኝ፣ ሐቀኛና ደፋር ነበር።—1 ሳሙኤል 2:22-26፤ 3:18, 19፤ 12:2-5, 17, 18

መልስ

ሀ. ሕልቃና እና ሐና።—1 ሳሙኤል 1:19, 20

ለ. መሳፍንትን፣ ሩትን እና የአንደኛ ሳሙኤልን የተወሰነ ክፍል

ሐ. “. . . በእግዚአብሔር ፊት አደገ።”—1 ሳሙኤል 2:21

ሕዝቦችና አገሮች

4. ኦስካር እና ሳስኪኧ እንባላለን፤ የ10 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በኢስቶኒያ ነው። በኢስቶኒያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 2,400፣ 4,200 ወይስ 6,800?

5. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከኢስቶኒያ በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.jw.org ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 11 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. መሥዋዕት የሚሆን ወይፈን

2. ዱቄት

3. አንድ አቁማዳ ወይም እንስራ የወይን ጠጅ

4. 4,200

5. ለ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ