የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/12 ገጽ 3
  • ቁጣ የሚያስከትለው ጉዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቁጣ የሚያስከትለው ጉዳት
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ቁጣን በተመለከተ ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ቁጡ የሆኑ ሰዎች የበዙት ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2012
  • ቁጣህን መቆጣጠር ያለብህ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—1998
  • ቁጣን መቆጣጠር
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 3/12 ገጽ 3

ቁጣ የሚያስከትለው ጉዳት

በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ሳንድዊች አዝዞ የነበረ አንድ ሰው ምግቡ እንደዘገየ ስለተሰማው በጣም ተቆጣ። ሰውየው በንዴት ገንፍሎ ከምግብ ቤቱ ሠራተኞች አንዱ ላይ አንባረቀበት፤ ይህም ሳይበቃው ሠራተኛውን በኃይል ከገፈተረው በኋላ በጥፊ አጮለው። ከዚያም ሳንድዊቹን መንጭቆ በመውሰድ ከምግብ ቤቱ ወጥቶ ሄደ።

ሁላችንም አልፎ አልፎ እንቆጣለን። ደግሞም እንደ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ጭንቀት፣ ሐዘንና ፍርሃት ሁሉ ቁጣም የሰው ልጆች ካሏቸው ተፈጥሯዊ ስሜቶች አንዱ ነው። ቁጣ ልጓም ከተበጀለት በተገቢው መንገድ ሊገለጽና ጠቃሚ ዓላማ ሊያከናውን ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ ቁጣ አንድ ሰው እንቅፋቶችን ወይም ችግሮችን ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጠናክርለት ከሆነ ጥቅም ይኖረዋል።

በሌላ በኩል ግን ከላይ የቀረበው ታሪክ እንደሚያሳየው ቁጣ ጉዳት ሊያስከትልም ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይበልጥ በቀላሉ ይበሳጩ፣ ቶሎ ቶሎ ይናደዱ እንዲሁም በጣም ይቆጡ ይሆናል። የሚያበሳጭ ነገር ሲያጋጥማቸው በንዴት ገንፍለው ሊሳደቡ አልፎ ተርፎም ሊማቱ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን መቆጣጠር ሲገባቸው እነሱ ግን ቁጣቸው እንዲቆጣጠራቸው ይፈቅዱለታል። እንዲህ ዓይነቱ ልጓም ያልተበጀለት ቁጣ አደገኛ ሲሆን በአንድ ሰው አስተሳሰብ፣ ስሜት፣ ጠባይና ከሌሎች ጋር ባለው ግንኙነት አልፎ ተርፎም በመላ ሕይወቱ ላይ ከባድ ችግሮችን ያስከትላል።

እንዲህ ባለው መንገድ ቁጣቸውን የሚገልጹ ሰዎች ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይጎዳሉ። ቁጣን የመቆጣጠር ችግር ያለባቸው ሰዎች ቀላል በሚመስሉ ጉዳዮች እንኳ በንዴት ገንፍለው አሳዛኝ ውጤት የሚያስከትል ድርጊት ሊፈጽሙ ይችላሉ። እስቲ ቀጥሎ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንመልከት፦

በሕዝብ በተጨናነቀ መንገድ ላይ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ የሚጓዝ አንድ ሰው አንገቱ ላይ በጥይት ተመታ፤ ይህ የሆነው ከጓደኞቹ አንዱ፣ ተኳሹን ሳያውቅ በቦርሳው ስለገፋው ነበር።

አንድ የ19 ዓመት ወጣት የ11 ወር ሕፃን የሆነውን የእጮኛውን ልጅ ክፉኛ መትቶ ገደለው። ወጣቱ ይህን ያደረገው ዓመፅ የሚንጸባረቅበት የቪድዮ ጨዋታ እየተጫወተ ሳለ ልጁ መጫወቻውን ነክቶበት እንዲሸነፍ ስላደረገው በቁጣ ገንፍሎ ነው።

ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ተመሳሳይ የሆኑ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሰዎች ቁጣቸውን የመቆጣጠር ችግር አለባቸው። ይሁንና ቁጡ የሆኑ ሰዎች እየበዙ ያሉት ለምንድን ነው?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ቁጣ የሰው ልጆች ካሏቸው ተፈጥሯዊ ስሜቶች አንዱ ነው። በመሆኑም ልጓም በተበጀለት መልኩ ቁጣን መግለጽ ተገቢ ሊሆን የሚችልባቸው ጊዜያት አሉ። በእነዚህ ርዕሶች ላይ ትኩረት የምናደርገው ግን በእኛም ሆነ በሌሎች ላይ ስሜታዊ፣ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጤናማ ያልሆነ ቁጣ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ