የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 6/12 ገጽ 4
  • 1. በጥንቃቄ ሸምቱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1. በጥንቃቄ ሸምቱ
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለምግብ ደህንነትና ለጤናማ አመጋገብ ወሳኝ የሆኑ ሰባት ነገሮች
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • በቅርቡ ሁሉም ሰው ጤናማ ምግብ ያገኛል!
    ንቁ!—2012
  • 3. ምግብ ስታዘጋጁም ሆነ ስታስቀምጡ ተጠንቀቁ
    ንቁ!—2012
  • በመንፈሳዊ በደንብ ትመገባለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 6/12 ገጽ 4

1. በጥንቃቄ ሸምቱ

የራሳችሁ እርሻ ወይም የጓሮ አትክልት ከሌላችሁ ምግባችሁን ከገበያ መሸመት ይኖርባችኋል። ታዲያ ገበያ ምግብ በምትሸምቱበት ጊዜ ምን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይኖርባችኋል?

● አስቀድማችሁ አስቡ

ስለ ምግብ ደኅንነት መረጃ የሚሰጥ በአውስትራሊያ የሚገኝ ተቋም እንዲህ ብሏል፦ “ምግብ ስትሸምት፣ ቶሎ የማይበላሹትን አስቀድም። ማቀዝቀዣ እና በረዶ ቤት ውስጥ መቀመጥ የሚያስፈልጋቸውን ምግቦች መጨረሻ ላይ መግዛቱ የተሻለ ነው።” በተጨማሪም ትኩስ ምግብ መግዛት የምትፈልጉ ከሆነ ወደ ቤት ልትሄዱ ስትሉ ብትሸምቱት ጥሩ ይሆናል።

● ከተመረቱ ያልቆዩ ምግቦችን ግዙ

በተቻለ መጠን ከተመረቱ ያልቆዩ ምግቦችን ለመግዛት ሞክሩ።a በናይጄሪያ የምትኖር ሩት የምትባል የሁለት ልጆች እናት “ምግቡን ወደ ገበያ እንደመጣ ለማግኘት ስል አብዛኛውን ጊዜ ለመሸመት የምሄደው በማለዳ ነው” ትላለች። በሜክሲኮ የምትኖረው ኤልዛቤትም የምግብ ሸቀጦችን የምትገዛዛው እንደ ጉሊት ባለ ከቤት ውጭ የሚገኝ የገበያ ቦታ ነው። “በዚያ፣ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ከተመረቱበት ቦታ እንደመጡ ማግኘት የምችል ከመሆኑም ሌላ የምፈልገውን ነገር ራሴ መርጬ መግዛት እችላለሁ” ትላለች። “ያደረ ሥጋ ፈጽሞ አልገዛም። የተረፈኝን ሥጋ በረዶ ቤት አስቀምጠዋለሁ።”

● ምግቡን አገላብጣችሁ ተመልከቱት

ራሳችሁን እንደሚከተለው እያላችሁ ጠይቁ፦ ‘የምገዛው ፍራፍሬና አትክልት ቆዳው ላይ የመበላሸት ምልክት ይታይበታል? ሥጋው መጥፎ ጠረን አምጥቷል?’ የምትገዙት የምግብ ሸቀጥ የታሸገ ከሆነ አስተሻሸጉን አገላብጣችሁ ተመልከቱት። ማሸጊያው ከተቀደደ ምግቡን የሚመርዙ ባክቴሪያዎች ሊገቡ ይችላሉ።

በሆንግ ኮንግ የሚኖረው ቼንግ ፋይ የምግብ ሸቀጦችን የሚገዛው ከሱፐርማርኬት ነው፤ እንዲህ ይላል፦ “የታሸገው ምግብ ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከመቼ እንደሆነ ለማወቅ በማሸጊያው ላይ የታተሙትን ቀኖች መመልከትም አስፈላጊ ነው።” ለምን? ምክንያቱም “ጊዜው ያለፈበት” ምግብ መልኩ፣ ሽታውና ጣዕሙ ደህና ቢሆንም እንኳ የጤና መታወክ ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

● ንጹሕ መያዣ ተጠቀሙ

የገዛችሁትን ምግብ የምትይዙበትን የፕላስቲክ ዘንቢል ወይም መያዣ በተደጋጋሚ የምትጠቀሙበት ከሆነ አዘውትራችሁ በሞቀ ውኃና በሳሙና እጠቡት። ሥጋና ዓሣ ከሌሎች የምግብ ሸቀጦች ጋር ከተነካኩ ሊያበላሿቸው ስለሚችሉ ለብቻ ለይታችሁ ያዟቸው።

በጣሊያን የሚኖሩ ኤንሪኮና ሎሬዳና የሚባሉ ባልና ሚስት የምግብ ሸቀጦችን የሚገዙት በአካባቢያቸው ከሚገኝ ገበያ ነው። “ምግቡን ከገዛን በኋላ ረጅም ርቀት ስለማንጓዝ አይበላሽብንም” ይላሉ። የምግብ ሸቀጦችን ከገዛችሁ በኋላ ወደ ቤት ለመመለስ ከ30 ደቂቃ በላይ የሚፈጅባችሁ ከሆነ ከበረዶ ቤት የወጡ ወይም ማቀዝቀዣ ውስጥ የነበሩ ምግቦችን፣ እንደቀዘቀዙ ለማቆየት በሚረዱ ዕቃዎች ለመያዝ ወይም ሙቀት እንዳያገኛቸው ለማድረግ ሞክሩ።

በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ደግሞ የገዛችሁት የምግብ ሸቀጥ ቤታችሁ ከገባ በኋላ እንዳይበከል ጥንቃቄ ማድረግ የምትችሉት እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በመጋቢት 2011 ንቁ! ላይ የወጣውን “1ኛው ቁልፍ​—ጥሩ አመጋገብ ይኑርህ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ልጆቻችሁን አሠልጥኑ፦ “ልጆቼን [እንደ ብስኩት ያለ] ማንኛውንም የታሸገ ምግብ ከመግዛታቸው በፊት በማሸጊያው ላይ ያለውን ቀን እንዲመለከቱ አስተምሬያቸዋለሁ።”​—ሩት፣ ናይጄሪያ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ