የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 6/12 ገጽ 18
  • የክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ዛጎል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ዛጎል
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የስኬሊ ፉት ቀንድ አውጣ ዛጎል
    ንቁ!—2011
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • ቢልሃርዚያን በቅርቡ ማጥፋት ይቻል ይሆን?
    ንቁ!—1998
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 6/12 ገጽ 18

ንድፍ አውጪ አለው?

የክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ዛጎል

● ብዙዎቹ የባሕር ፍጥረታት ብርሃን የማመንጨት ችሎታ አላቸው። ክላስተርዊንክ የተባለው ቀንድ አውጣ ይህን ችሎታውን የሚጠቀምበት ልዩ በሆነ መንገድ ነው። ይህ ቀንድ አውጣ፣ ሸርጣን የሚባለው እንስሳ ሲመጣበት ዛጎሉ ውስጥ ይገባና ሸርጣኑን ለማባረር ብርሃን ያበራበታል። ይሁን እንጂ ብርሃኑ የቀንድ አውጣውን ዛጎል አልፎ ሊታይ የሚችለው እንዴት ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የዚህ ቀንድ አውጣ ዛጎል ብርሃኑ እንዳይታይ ከማገድ ይልቅ በተለያየ አቅጣጫ እንዲበተን ያደርገዋል። በሳን ዲዬጎ ካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የውቅያኖስ ምርምር ተቋም የሚሠሩት ዲሚትሪ ዴሄን እና ኔሪደር ዊልሰን የተባሉት የሳይንስ ሊቃውንት፣ ከዚህ ቀንድ አውጣ የሚወጣው ብርሃን በዛጎሉ ላይ ወጥ በሆነ መልኩ እንደሚበተን እንዲሁም በዛጎሉ ላይ ብርሃን የሚበተንበት መንገድ ተመሳሳይ ውፍረት (0.5 ሚሊ ሜትር) ካለውና ብርሃን እንዲበተን ከሚያደርግ ሰው ሠራሽ መሣሪያ በአሥር እጥፍ እንደሚበልጥ ደርሰውበታል። በዚህ ላይ ደግሞ ዛጎሉ ብርሃኑን ወደ አካባቢው የማሰራጨት ችሎታው ሰው ሠራሽ ከሆኑ ብርሃን የሚያሰራጩ መሣሪያዎች በስምንት እጥፍ ይበልጣል። የሚገርመው ነገር የክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ያለው ዓይነት ብርሃንን የመበተንም ሆነ የማሰራጨት አስደናቂ ችሎታ ከእሱ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች የባሕር ቀንድ አውጣ ዝርያዎች የላቸውም። ከዚህ ቀንድ አውጣ የሚወጣው ብርሃን ላይ የሚታየው ቀለም ደግሞ ከሌሎቹ ቀለማት የበለጠ በባሕር ውስጥ ረጅም ርቀት ሊጓዝ ይችላል፤ ይህም እንዲሁ በአጋጣሚ የሆነ ነገር አይደለም።

ዶክተር ዴሄን፣ ስለ ክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ተጨማሪ እውቀት መገኘቱ “ብርሃን በማስተላለፍ ረገድ የተሻሉ መሣሪያዎችን ለመሥራት ሊጠቅም” እንደሚችል ተናግሯል። እንዲህ ያለው ምርምር፣ በብርሃን በመጠቀም በሽታዎችን የሚመረምሩና የሚያክሙ ባለሙያዎችንም ይጠቅማቸዋል። ብርሃን አመንጪ ዳዮዶች ሥራ ላይ በዋሉበት በዚህ ዘመን፣ አነስተኛ የሆነን ብርሃን አባዝተው ሊበትኑ የሚችሉ መሣሪያዎች ኃይል በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ጥርጥር የለውም።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የክላስተርዊንክ ቀንድ አውጣ ዛጎል በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ዛጎሉ በአጉሊ መነጽር ሲታይ

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ዛጎሉ ብርሃን ሲያሰራጭ (በአጉሊ መነጽር ሲታይ)

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Left: www.robastra.com; center and right: Courtesy of Dr. D. Deheyn, Scripps Institution of Oceanography, UC San Diego

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ