የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/13 ገጽ 10-11
  • የበረሃዋን ድመት ተዋወቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የበረሃዋን ድመት ተዋወቁ
  • ንቁ!—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • የድመት ምላስ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • ወዳጅነትህን ጠብቀህ ለማቆየት አንተ ራስህ ወዳጅ መሆን አለብህ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • የድመት ጺም ያለው ጥቅም
    ንቁ!—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2013
g 7/13 ገጽ 10-11

የበረሃዋን ድመት ተዋወቁ

የዚህች ድመት የእርግዝና ጊዜ ሁለት ወር ገደማ ሲሆን በአማካይ ሦስት ግልገሎችን ትወልዳለች

የበረሃዋ ድመት (ሳንድ ካት) ጭው ባለው በረሃ ጨለማውን ተገን አድርጋ ከጉድጓዷ ትወጣና ቆም ብላ ዙሪያ ገባውን ትቃኛለች። እንዲሁም ጆሮዋን ቀስራ ታዳምጣለች። ከዚያም ድምጿን አጥፍታ እያደባች በአሸዋማው መሬት ላይ በቀስታ መሄድ ትጀምራለች።

በድንገት ድመቷ ዘለለችና አደጋ ይመጣል ብላ ያልጠረጠረችውን የአይጥ ዝርያ እንቅ አደረገቻት። አደኑ በዚህ አያቆምም፤ ሌሊቱን ሙሉ በዚሁ መንገድ ስታድን ታድራለች። በልታ ልትጨርሰው ከምትችለው በላይ ካደነች የተረፋትን አሸዋ ውስጥ ትቀብራለች። የበረሃዋ ድመት ወደ ጉድጓዷ የምትመለሰው ሊነጋጋ ሲል ነው፤ ቀን ላይ ጨርሶ ብቅ አትልም ማለት ይቻላል። ስለዚህች በቀላሉ የማትታይ እንስሳ አንዳንድ አስደናቂ መረጃዎችን እስቲ እንመልከት።

  • ጆሯቸው ከሩቅ ስለሚሰማ የሚያድኑት እንስሳ ከመሬት በታች ቢሆንም እንኳ ሊያገኙት ይችላሉ

  • ተባዕቱ ድመት ተጓዳኝ ለማግኘት ቀጭን የሆነ ኃይለኛ ጩኸት ያሰማል። እንስቷም ይህንን ድምፅ ከረጅም ርቀት መስማት ትችላለች

  • መዳፎቻቸው በፀጉር የተሸፈኑ ናቸው፤ ይህም በሚሄዱበት ጊዜ አሸዋ ውስጥ እንዳይሰምጡ የሚረዳቸው ከመሆኑም ሌላ መዳፋቸውን ቅዝቃዜም ሆነ ሙቀት እንዳይጎዳው ይከላከልላቸዋል

  • የጆሮዎቻቸው ውስጠኛ ክፍል ጥቅጥቅ ባለ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ መሆኑ ነፋስ በሚኖርበት ጊዜ አሸዋ ጆሯቸው ውስጥ እንዳይገባ ይከላከልላቸዋል

  • የእነዚህ ድመቶች መዳፍ ጥቅጥቅ ባለ ፀጉር የተሸፈነ በመሆኑ ዱካቸውን ተከታትሎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው

  • እነዚህ ድመቶች ከሚበሉት እንስሳ በሚያገኙት ውኃ ብቻ መኖር ይችላሉ

  • የካራኩም በረሃ አሸዋ እስከ 80 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ሙቀት ሊኖረው ይችላል። በሌሎች ጊዜያት ደግሞ የሙቀቱ መጠን ከዜሮ በታች እስከ 25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊወርድ ይችላል

አጭር መረጃ

  • የምትገኝበት አካባቢ፦ በሰሃራ በረሃ መካከለኛ አካባቢ፣ በዓረብ አገሮች በሙሉና በማዕከላዊ እስያ አንዳንድ ክፍሎች

  • ክብደት፦ ተባዕቱ ከ2 እስከ 3 ኪሎ ግራም

  • ርዝመት (ጅራትን አይጨምርም)፦ ከ40 እስከ 57 ሴንቲ ሜትር

  • ጅራት፦ ከ20 እስከ 30 ሴንቲ ሜትር

  • ባሕርይ፦ ቁጡና አስፈሪ ከሆኑት ሌሎች የዱር የድመት ዝርያዎች ጋር ስትወዳደር ገራም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ