የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/13 ገጽ 14-15
  • የአልኮል መጠጥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአልኮል መጠጥ
  • ንቁ!—2013
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስህተት ነው?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል መጠጣት እንዳለብን ይናገራል?
  • መጠጣት ተገቢ የማይሆነው መቼ ነው?
  • የአልኮል መጠጥን በተመለከተ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስህተት ነው?
    ንቁ!—2006
  • አምላክ ለአልኮል መጠጥ ባለው አመለካከት ተመራ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ክርስቲያኖች ለአልኮል መጠጥ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2013
g 8/13 ገጽ 14-15

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የአልኮል መጠጥ

የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስህተት ነው?

“የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።”—መዝሙር 104:15

ሰዎች ምን ይላሉ?

በብዙ ቤተሰቦች ዘንድ የአልኮል መጠጦች ከምግብ ጋር ሁልጊዜ ይቀርባሉ። ሌሎች ግን አልኮል መጠጣት ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። እንዲህ ያለ የአመለካከት ልዩነት የኖረው ለምንድን ነው? እንደ ባሕል፣ ጤንነትና ሃይማኖት ያሉት ነገሮች ሰዎች በዚህ ረገድ ባላቸው አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ስካርንና ከልክ በላይ መጠጣትን እንጂ በመጠኑ መጠጣትን አይደለም። (1 ቆሮንቶስ 6:9, 10) በእርግጥም አምላክን የሚያመልኩ ወንዶችና ሴቶች ከጥንት ዘመናት ጀምሮ የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፤ የወይን ጠጅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት ተጠቅሷል። (ዘፍጥረት 27:25) መክብብ 9:7 “ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ” ይላል። የወይን ጠጅ ሰዎችን ደስ ስለሚያሰኝ እንደ ሠርግ ባሉት የደስታ ጊዜያት ላይ ይቀርብ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃውን ወደ “ወይን ጠጅ” በመለወጥ የመጀመሪያውን ተአምር የፈጸመው እንዲህ ባለው ድግስ ላይ ነው። (ዮሐንስ 2:1-11) በተጨማሪም ወይን ለሕክምና ያገለግል ነበር።—ሉቃስ 10:34፤ 1 ጢሞቴዎስ 5:23

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል መጠጣት እንዳለብን ይናገራል?

“ለብዙ ወይን ጠጅ [አትገዙ]።”—ቲቶ 2:3

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

በበርካታ ቤተሰቦች ውስጥ አንዱ ወይም ሁለቱም ወላጆች ከልክ በላይ የሚጠጡ መሆናቸው በቤተሰቡ ውስጥ ችግር እንዲፈጠር አድርጓል። በተጨማሪም አልኮል አብዝቶ መጠጣት ሰዎች የመኪና አደጋን ጨምሮ በመውደቅና በሌሎች አደጋዎች ለጉዳት እንዲዳረጉ ያደርጋል። አልኮል ከልክ በላይ መጠጣት ውሎ አድሮ ደግሞ በአንጎል፣ በልብ፣ በጉበትና በሆድ ዕቃ ላይ ጉዳት ያደርሳል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ እንድናሟላ ከሚጠብቅብን መሠረታዊ ብቃቶች አንዱ በመጠጥም ሆነ በምግብ ረገድ ልከኛ መሆን ነው። (ምሳሌ 23:20፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:2, 3, 8) ራስን መግዛት አለመቻል አምላክ እንዲያዝንብን ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ “የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም” ይላል።—ምሳሌ 20:1

የአልኮል መጠጥ ጥበበኛ ያልሆነን ሰው ከሚያስትባቸው መንገዶች አንዱ የሥነ ምግባር አቋሙን እንዲያላላ ማድረግ ነው። ሆሴዕ 4:11, 12 ላይ ‘የወይን ጠጅ ማስተዋልን እንደሚወስድ’ ይናገራል። ጆን የተባለ ሰው ይህን ሐቅ ከደረሰበት ችግር ተምሯል።a ከሚስቱ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ጆን ከቤት ወጥቶ ወደ ሆቴል ሄደና ብዙ መጠጥ ጠጣ፤ ይህም ምንዝር ወደ መፈጸም መራው። እንዲህ በማድረጉ በኋላ ላይ በጣም የጸጸተው ሲሆን ወደዚህ ዓይነት ስህተት የሚመራ ነገር ዳግመኛ ላለማድረግ ቆርጧል። ከመጠን በላይ መጠጣት በአካላችን፣ በሥነ ምግባራዊ አቋማችን እንዲሁም በመንፈሳዊነታችን ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሰካራሞች የዘላለም ሕይወት እንደማያገኙ ይናገራል።—1 ቆሮንቶስ 6:9, 10

መጠጣት ተገቢ የማይሆነው መቼ ነው?

“ብልኅ ሰው መከራ ሲመጣ አይቶ ይሸሻል፤ ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ ከገባ በኋላ እንደገና ይጸጸታል።”—ምሳሌ 22:3 የ1980 ትርጉም

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ “አልኮል በጣም ኃይለኛ ዕፅ ነው” ይላል። ስለዚህ አልኮልን በመጠኑ እንኳ መጠጣት ተገቢ የማይሆንባቸው ሁኔታዎች ወይም ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ ወቅት በመጠጣታቸው ምክንያት ‘ሰተት ብለው ወደ መከራ ይገባሉ።’ መጽሐፍ ቅዱስ “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው” ይላል፤ ይህ ከአልኮል ጋር በተያያዘም ይሠራል። (መክብብ 3:1) ለምሳሌ አንድ ሰው አልኮል መጠጣት የሚፈቀድለት ዕድሜ ላይ አልደረሰ ይሆናል፤ አሊያም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ እየታገለ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ ከአልኮል መጠጥ ጋር የሚጋጭ መድኃኒት እየወሰደ ይሆናል። አብዛኞቹ ሰዎች ደግሞ ወደ ሥራ ከመሄዳቸው በፊት ወይም ሥራ ላይ በሚሆኑበት ወቅት አልኮል መጠጣት አይኖርባቸውም፤ በተለይም አደጋ ሊያስከትል በሚችል ማሽን ላይ የሚሠሩ ከሆነ ከመጠጣት መቆጠብ አለባቸው። ጠቢብ የሆኑ ሰዎች፣ ሕይወትንና ጤንነትን ከአምላክ የተገኙ ውድ ስጦታዎች አድርገው ይመለከቷቸዋል። (መዝሙር 36:9) ስለ አልኮል ባለን አመለካከት ረገድ በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች የምንመራ ከሆነ ለእነዚህ ስጦታዎች አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።

a ስሙ ተቀይሯል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ