የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/14 ገጽ 12-13
  • እንቆቅልሽ የሆነው እንባ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንቆቅልሽ የሆነው እንባ
  • ንቁ!—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ እንባውን ማፍሰሱ ምን ያስተምረናል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ይሖዋ እንባህን ይመለከታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • “እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 3/14 ገጽ 12-13
የሚያነባ ሰው

እንቆቅልሽ የሆነው እንባ

ማልቀስ ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ ከእኛ ጋር የሚኖር ነገር ነው። ሕፃን ሳለን ስሜታዊና አካላዊ ፍላጎቶቻችን እንዲሟሉልን የምንጠይቀው በማልቀስ ነው፤ በመሆኑም ለቅሶ “የድምፅ እትብት” ሊባል እንደሚችል አንድ ባለሙያ ገልጸዋል። ታዲያ እያደግን ስንሄድ በሌሎች መንገዶች ስሜታችንን መግለጽ ስንችል እንባችንን የምናፈስሰው ለምንድን ነው?

ከስሜት ጋር በተያያዘ እንባችንን የምናፈስስባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ስናዝን፣ ስንበሳጭ ወይም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሥቃይ ሲደርስብን ልናለቅስ እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ በጣም ስንደሰት፣ እፎይታ ሲሰማን ወይም ስኬት ስናገኝ ከስሜት ጋር ተያይዞ የሚመጣ እንባ እናነባለን፤ በዚህ ጊዜ ግን እንባችን የደስታ ነው። በተጨማሪም ማንባት ይጋባል። ማሪያ “ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሰው ሲያለቅስ ካየሁ እኔም እንባዬን መቆጣጠር ያቅተኛል” ብላለች። በፊልም ላይ የተመለከትከው ወይም በመጽሐፍ ላይ ያነበብከው ምናባዊ ታሪክ አስለቅሶህ ይሆናል።

የምታነባ ወጣት፣ የሚያለቅስ ሕፃን፣ የምታነባ ሴት

ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ማልቀስ ከፍተኛ ኃይል ያለው ንግግር አልባ ቋንቋ ነው። የአዋቂዎች ለቅሶ (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ፣ የእንባን ያህል “በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገር ለመግለጽ የሚያስችሉ ሌሎች መንገዶች” እንደሌሉ ገልጿል። እንባ፣ ሰዎች አንድ እርምጃ እንዲወስዱ ያነሳሳል። ለምሳሌ ያህል፣ አብዛኞቻችን የሐዘን እንባ አይተን ችላ ብለን ማለፍ አንችልም፤ ምክንያቱም ለቅሶው ግለሰቡ በሥቃይ ውስጥ መሆኑን ይጠቁመናል። በመሆኑም የሚያለቅሰውን ሰው ለማጽናናት ወይም ለመርዳት እንገፋፋለን።

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ማልቀስ በውስጣችን ያለውን የታመቀ ስሜት እንዲወጣልን የሚያደርግ ጠቃሚ ዘዴ ስለሆነ እንባን አምቆ የመያዝ ልማድ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ሌሎች ደግሞ ማልቀስ የሚያስገኘው አካላዊም ሆነ ሥነ ልቦናዊ ጥቅም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አልተረጋገጠም ብለው ይከራከራሉ። ያም ሆነ ይህ፣ 85 በመቶ የሚሆኑ ሴቶችና 73 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ካለቀሱ በኋላ ቀለል እንዳላቸው ጥናቶች አመልክተዋል። ኖኤሚ “ማልቀስ እንደሚያስፈልገኝ የሚሰማኝ ጊዜ አለ” ብላለች። “ከዚያም በረጅሙ ከተነፈስኩ በኋላ እውነታውን ይበልጥ አጥርቼ ማየት እችላለሁ።”

ጥናቶች እንደሚያሳዩት 85 በመቶ የሚሆኑ ሴቶችና 73 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ካለቀሱ በኋላ ቀለል ይላቸዋል

ይሁን እንጂ ይህ የእፎይታ ስሜት እንባ በማፍሰስ ብቻ የሚገኝ ላይሆን ይችላል። ሌሎች ለለቅሷችን የሚሰጡት ምላሽም በዚህ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል፣ ሰዎች እንባችንን አይተው ሲያጽናኑን ወይም ሲረዱን የእፎይታ ስሜት ይሰማናል። በምናለቅስበት ወቅት ተገቢውን ምላሽ ከሰዎች ካላገኘን የኃፍረትና የመገለል ስሜት ሊሰማን ይችላል።

ከለቅሶ ጋር በተያያዘ ብዙ እንቆቅልሽ የሆኑ ነገሮች እንዳሉ ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ አንድ የምናውቀው ነገር አለ፤ እንባን ማፍሰስ አምላክ ከሰጠን አስደናቂ የስሜት መግለጫዎች አንዱ ነው።

ይህን ታውቅ ነበር?

ሕፃናት ገና እንደተወለዱ አካባቢ ሲያለቅሱ በአብዛኛው እንባ አይፈስሳቸውም። ዓይናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል በቂ እርጥበት አላቸው፤ ይሁን እንጂ ከበርካታ ሳምንታት በኋላ የእንባ መውረጃ ቱቧቸው ሙሉ በሙሉ ሲዳብር እንባቸው መፍሰስ ይጀምራል።

ሦስት የእንባ ዓይነቶች

  • መደበኛ (ቤዘል) እንባ። የእንባ አመንጪ እጢዎች ዓይናችንን ለመጠበቅና ለማርጠብ ሲሉ ይህን የጠራ ፈሳሽ ዘወትር ያመነጫሉ። በተጨማሪም ይህ እንባ የማየት ችሎታችንን ያሻሽልልናል። ዓይናችንን በምናርገበግብበት ጊዜ ይህ ፈሳሽ በመላው ዓይናችን ይዳረሳል።

  • ድንገተኛ (ሪፍሌክስ) እንባ። የሚያስቆጣ ወይም የሚቆጠቁጥ ነገር ዓይናችን ውስጥ ሲገባ ይህ ዓይነቱ እንባ ይፈስሰናል። በተጨማሪም ስናዛጋ ወይም ስንስቅ የሚፈስሰው ይኸው የእንባ ዓይነት ነው።

  • ስሜታዊ (ኢሞሽናል) እንባ። ይህ ዓይነቱ እንባ፣ ኃይለኛ የሆነ ስሜት ውስጥ ስንሆን የምናፈስሰው በሰዎች ላይ ብቻ የሚታይ ነገር ነው። በዚህ ዓይነቱ እንባ ውስጥ የሚገኘው ፕሮቲን በድንገተኛ እንባ ውስጥ ከሚገኘው 24 በመቶ ይበልጣል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ