የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/14 ገጽ 3
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዩናይትድ ስቴትስ
  • ዓለም
  • ሚድዌይ ደሴት
  • ደቡብ አፍሪካ
  • “በምድር ላይ በትልቅነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ሕይወት ያለው በራሪ ማሽን”
    ንቁ!—2010
  • በዱር እንስሳት ላይ ሰላይ ማቆም
    ንቁ!—2002
  • የዋንደሪንግ አልባትሮስ ኃይል ቆጣቢ የበረራ ዘዴ
    ንቁ!—2013
  • በልጆች ላይ የሚታይ ጤናማ ያልሆነ ውፍረት—ምን ማድረግ ይቻላል?
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 4/14 ገጽ 3

ከዓለም አካባቢ

ዩናይትድ ስቴትስ

እርስ በርሳቸው ተቀናጅተው የሚሠሩ የመንገድ ትራፊክ መብራቶች

በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ የምትገኘው የሎስ አንጀለስ ከተማ፣ በ1,215 ካሬ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ያሉትን ወደ 4,500 የሚጠጉ የትራፊክ መብራቶች በሙሉ እርስ በርሳቸው ተቀናጅተው የሚሠሩበትን ሥርዓት ዘርግታለች። ኒው ዮርክ ታይምስ እንደገለጸው ከሆነ ሎስ አንጀለስ “ይህን ለማድረግ በዓለም የመጀመሪያዋ ትልቅ ከተማ ሆናለች።”

ዓለም

በዓለም ዙሪያ ከጤና ጋር በተያያዘ የተደረገ አንድ ግምገማ እንዳሳየው ከልክ ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከ1990 እስከ 2010 ባሉት ዓመታት ውስጥ 82 በመቶ ጨምሯል። በቂ ምግብ አለማግኘት ዛሬም ድረስ በብዙ አገሮች ችግር ማስከተሉ እንዳለ ሆኖ፣ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ግን በቂ ምግብ ባለማግኘት ከሚሞቱት በሦስት እጥፍ ይበልጣል። እንደ እውነቱ ከሆነ “ከ20 ዓመት በፊት ሰዎች በቂ ምግብ የማያገኙባት የነበረችው ዓለማችን አሁን ግን ታዳጊ በሆኑ አገሮች ሳይቀር ከበቂ በላይ የሆነ ምግብ እንዲሁም ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች የሚገኝባት መሆኗ ለበሽታ ዳርጎናል” በማለት ከዋነኞቹ ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ማጂድ ኢዛቲ ተናግረዋል።

ሚድዌይ ደሴት

ላይሳን አልባትሮስ

“በዓለማችን ላይ ካሉ የዱር አእዋፍ መካከል በዕድሜ አንጋፋ” እንደሆነች የሚነገርላት ላይሳን አልባትሮስ የተባለችው ወፍ ተጨማሪ ጫጩት ፈልፍላለች። ለመሆኑ ዕድሜዋ ምን ያህል ይሆናል? የመከታተያ ቀለበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገላት በ1956 ሲሆን በዚያ ጊዜ ቢያንስ አምስት ዓመት ይሆናት ነበር፤ በመሆኑም አሁን ዕድሜዋ ከ60 ዓመት አልፏል ማለት ነው። ይህች አልባትሮስ በሕይወት ዘመኗ ከሦስት እስከ አራት ሚሊዮን ኪሎ ሜትር እንደበረረች የሚገመት ሲሆን ይህ ርቀት ከምድር ወደ ጨረቃ ደርሶ መልስ ከአራት እስከ ስድስት ጊዜ ይሆናል።

ደቡብ አፍሪካ

አንዲት ደቡብ አፍሪካዊት ፊቷን ቆዳ የሚያነጣ ቅባት ስትቀባ

አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከደቡብ አፍሪካ ሴቶች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት የቆዳ ቀለማቸውን ለማንጣት ሲሉ ቆዳ የሚያነጡ ሳሙናዎችና ቅባቶች ይጠቀማሉ። እንደነዚህ ያሉት ቆዳን ለማንጣት የሚያገለግሉ ምርቶች አደገኛ በመሆናቸው በብዙ አገሮች ታግደዋል። ከሚያስከትሉት አደጋዎች መካከል የተለያዩ የካንሰር በሽታዎች፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ ሽፍታና የቆዳ መበላሸት ይገኙባቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ