የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/14 ገጽ 3
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዓለም
  • ብሪታንያ
  • ቻይና
  • አውሮፓ
  • በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት—ዓለም አቀፍ ችግር
    ንቁ!—2008
  • ጠብ ቤተሰብን ሲያናጋ
    ንቁ!—1998
  • አምላክ የዓመፅ ድርጊቶችን እንዴት ይመለከታል?
    ንቁ!—2002
  • ዓመፅ የማይጎዳው ሰው የለም
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 9/14 ገጽ 3

ከዓለም አካባቢ

ዓለም

በትዳር አጋሯ ጥቃት የደረሰባት ሴት

የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከሆነ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት “እንደ ወረርሽኝ የተዛመተ ዓለም አቀፍ የጤና ችግር” ሆኗል። “በዓለም ላይ ካሉ ሴቶች መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት በወንድ ጓደኛቸውና በትዳር አጋራቸው አሊያም በሌላ ወንድ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል” በማለት የዓለም የጤና ድርጅት ገልጿል። “በወንድ ጓደኛ ወይም በትዳር አጋር የሚፈጸመው ጥቃት በጣም የተለመደ ሲሆን በዓለም ዙሪያ 30 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለዚህ የተጋለጡ ናቸው።”

ብሪታንያ

ቤተ ክርስቲያን

ከ64,303 ሰዎች የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው 79 በመቶ የሚሆኑት “ሃይማኖት በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ለብዙ ችግሮችና ግጭቶች መንስኤ” እንደሆነ ያስባሉ። ከዚህም በላይ በ2011 በእንግሊዝና በዌልስ የተደረገ የሕዝብ ቆጠራ እንዳመለከተው ክርስቲያን እንደሆኑ የተናገሩት ሰዎች ቁጥር በ2001 72 በመቶ ከነበረበት ቀንሶ ወደ 59 በመቶ ወርዷል። ለሃይማኖት ግድ እንደሌላቸው የተናገሩት ሰዎች ቁጥር በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከ15 በመቶ ወደ 25 በመቶ ከፍ ብሏል።

ቻይና

በዕድሜ የገፉ ቻይናዊ ወላጆች

መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት ከሆነ በቅርቡ ተሻሽሎ የወጣው ሕግ፣ ትላልቅ ልጆች አረጋውያን ወላጆቻቸውን አዘውትረው እንዲጠይቁ ብቻ ሳይሆን “ስሜታዊ ፍላጎታቸውንም” እንዲያሟሉላቸው የሚያስገድድ ነው። ሕጉ፣ ደንቡን ተግባራዊ በማያደርጉ ሰዎች ላይ “ስለሚደርሰው ቅጣት ምንም አይናገርም።”

አውሮፓ

አስመስለው የተሠሩ ሸቀጦች

የተደራጁ ወንጀለኞች በአሁኑ ጊዜ ለሕዝብ የሚቀርቡ ሸቀጦችን ለምሳሌ መዋቢያዎችን፣ የጽዳት ኬሚካሎችን አልፎ ተርፎም የምግብ ምርቶችን አስመስለው እየሠሩ ነው። ወንጀለኞቹ እነዚህን ሸቀጦች ለመሥራት የሚያገለግል “ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለውን ማንኛውንም ንጥረ ነገር አስመስሎ ከመሥራት” እንደማይመለሱ አንድ የምግብ ደኅንነት አማካሪ ድርጅት ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። አንድ ባለሙያ እንደገመተው በበለጸጉት አገሮች ለሽያጭ ከሚቀርቡት የምግብ ምርቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ተቀይጠዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ