የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 10/14 ገጽ 7
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዩናይትድ ስቴትስ
  • ሕንድ
  • ስዊዘርላንድ
  • የአፍሪካ ቀንድ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • ንቁ! ላይ የወጡ “የወጣቶች ጥያቄ” ርዕሶች
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 10/14 ገጽ 7

ከዓለም አካባቢ

ዩናይትድ ስቴትስ

በመኪኖች ላይ የሚገጠም አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ

ፖሊሶች አንድን መኪና አባርረው ለመያዝ በሚሞክሩበት ጊዜ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ላይ ናቸው። ለምሳሌ፣ የፖሊስ መኪናዎቹ በታመቀ አየር በሚሠራ ማስወንጨፊያ በመጠቀም በሚከታተሉት መኪና ላይ የአቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ ያጣብቃሉ። ይህም አደጋ በማያስከትል ፍጥነት እየነዱ ተጠርጣሪውን ለመከታተል ያስችላቸዋል።

ሕንድ

አንዲት ሕንዳዊት ሴት

በጥሎሽ ምክንያት በሚፈጠር ግጭት የተነሳ በየሰዓቱ አንዲት ሴት እንደምትገደል ይገመታል። ጥሎሽ መስጠትም ሆነ መቀበል በሕግ የታገደ ቢሆንም በ2012 ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ8200 የሚበልጡ ሴቶች ተገድለዋል፤ ይህ የሆነው ሙሽራው ወይም ቤተሰቦቹ ሙሽሪት ያመጣችው ጥሎሽ በቂ እንዳልሆነ ስለተሰማቸው ነው።

ስዊዘርላንድ

አልፓይን ስዊፍት

አልፓይን ስዊፍት የሚባሉት ወፎች ወደ አፍሪካ በሚፈልሱበት ወቅት ከ200 ለሚበልጡ ቀናት ያለማቋረጥ እንደበረሩ ታውቋል፤ ይህን ማወቅ የተቻለው እነዚህ ወፎች በሚፈለፈሉበት ቦታ ላይ በነበሩ ሦስት ወፎች ላይ በተገጠመው እንቅስቃሴ ጠቋሚ መሣሪያ አማካኝነት ነው። ከዚህ በፊት ያለምንም ማቋረጥ እንዲህ ዓይነት ረጅም ጉዞ እንደሚያደርጉ የሚታወቀው የባሕር እንስሳት ብቻ ነበሩ።

የአፍሪካ ቀንድ

የመርከብ ጠለፋንና ለዚያ የሚከፈለውን የማስለቀቂያ ክፍያ የሚያሳይ ግራፍ

ከሚያዝያ 2005 እስከ ታኅሣሥ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ የባሕር ላይ ወንበዴዎች በአፍሪካ ቀንድ የባሕር ዳርቻዎች 179 መርከቦችን ጠልፈዋል። የዓለም ባንክ ያካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ወንበዴዎቹ እስከ 413 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የማስለቀቂያ ገንዘብ ተከፍሏቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ