የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 11/14 ገጽ 3
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢኳዶር
  • ጃፓን
  • ዚምባብዌ
  • አውስትራሊያ
  • የተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስከትሉትን ኪሣራ መመዘን
    ንቁ!—2000
  • በኤች አይ ቪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ ደም አስተማማኝ ነው ሊባል ይችላል?
    ንቁ!—2008
  • በላይኛው አማዞን የሚገኙ የተለያዩ አስደናቂ ፍጥረታት
    ንቁ!—2010
  • ኤድስን እንዴት መከላከል ይቻላል?
    ንቁ!—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 11/14 ገጽ 3

ከዓለም አካባቢ

ኢኳዶር

የአማዞን ደን የተወሰነ ክፍል

የኢኳዶር መንግሥት፣ 10,000 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ስፋት ባለው የአማዞን ደን ክፍል ውስጥ ነዳጅ ለማውጣት ከማስቆፈር ይልቅ የደኑን ተፈጥሯዊ ይዞታ ለማስጠበቅ የሚያስችል እቅድ ማውጣቱን በ2007 ገልጾ ነበር። ይሁንና ይህን ለማድረግ የሚያስችል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የገንዘብ ድጋፍ በመታጣቱ የኢኳዶር መንግሥት የያዘውን ዕቅድ ትቶታል። ይህ የአማዞን ደን ክፍል በዓለም ላይ ብዙ የእንስሳት እና የዕፀዋት ዝርያዎች ከሚገኙባቸው ክልሎች አንዱ ነው።

ጃፓን

አንድ የሕክምና ባለሙያ የተቀዳ ደም ይዞ

ዘ ጃፓን ኒውስ እንደተናገረው አንድ የተቀዳ ደም የተበከለ መሆን አለመሆኑን በምርመራ ማረጋገጥ በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህ ዘገባ የወጣው በ60ዎቹ ዕድሜ የሚገኙ አንድ ሰው በተሰጣቸው ደም ምክንያት የኤች አይ ቪ ቫይረስ እንደያዛቸው በ2013 የተላለፈውን ዜና ተከትሎ ነው። ከለጋሾች የሚወሰደው ደም የኤች አይ ቪ ቫይረስ ያለበት ቢሆንም እንኳ ደሙ በሚመረመርበት ጊዜ የቫይረሱ መኖር ላይታወቅ ይችላል፤ ምክንያቱም ቫይረሱ በምርመራ ሊገኝ የማይችልበት ዊንዶው ፔሬድ የሚባል ወቅት አለ።

ዚምባብዌ

በዚምባብዌ በተቀበሩ ፈንጂዎች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰበት ሰው

በዚምባብዌና በሞዛምቢክ ድንበር ላይ ይደረግ የነበረው የደፈጣ ውጊያ ካቆመ ከ30 ዓመታት በላይ ቢያልፉም በዚህ አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎች አሁንም ድረስ ሰዎችን ለአካል ጉዳተኝነትና ለሞት እየዳረጉ ነው። ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እንደዘገበው “ከ1980 ወዲህ በዚህ አካባቢ ባለው የዚምባብዌ ግዛት ውስጥ በፈንጂዎች ምክንያት ከ1,500 የሚበልጡ ሰዎችና 120,000 የቀንድ ከብቶች የሞቱ ሲሆን 2,000 የሚያህሉ ሰዎች ደግሞ አካል ጉዳተኞች ሆነዋል።”

አውስትራሊያ

ፍቺ በፈጸሙ አንድ ባልና ሚስት መሃል የተቀመጠ ውሻ

እንደ ውሻና ድመት ባሉ የቤት እንስሳት የባለቤትነት ጥያቄ የተነሳ ክርክር ውስጥ የሚገቡ የተፋቱ ባለትዳሮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አንድ ጥናት አመልክቷል። ፍቺ በፈጸሙ ባልና ሚስት መካከል ለክርክር መንስኤ ከሆኑት የጋራ ንብረቶች መካከል ቤት፣ ገንዘብና አንዳንድ የግል ዕቃዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፤ የቤት እንስሳት ደግሞ ቀጥሎ ያለውን ደረጃ ይይዛሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ