የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/15 ገጽ 12-13
  • ነፍስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ነፍስ
  • ንቁ!—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ነፍስ ትሞታለች?
  • ነፍስ ከሥጋ የተለየች ናት?
  • ሰው ሲሞት ነፍሱ ምን ትሆናለች?
  • የማትሞት ነፍስ አለችህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍስ ምን ይላል?
    ስንሞት ምን እንሆናለን?
  • ነፍስ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ከሞት በኋላ ሕይወት —መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 12/15 ገጽ 12-13

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ነፍስ

ሃይማኖቶች ስለ ነፍስ እንዲሁም ሰው ሲሞት ነፍሱ ምን እንደምትሆን የሚያስተምሩት ነገር የተለያየ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ይህንን አስመልክቶ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ይሰጣል።

ነፍስ ትሞታለች?

ሰዎች ምን ይላሉ?

ብዙ ሰዎች ‘ነፍስ አትሞትም’ ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ነፍስ፣ የነበረችበት አካል ሲሞት ሌላ አካል ለብሳ እንደምትወለድና ይህ ሂደት የማያቋርጥ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ነፍስ ወደ ሌላ ዓለም ማለትም ወደ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነም እንደምትሄድ የሚያምኑም አሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ነፍስ ዘላለማዊ እንደሆነች አይናገርም። ከዚህ ይልቅ ብዙ ቦታዎች ላይ፣ ነፍስ እንደምትሞት የሚገልጽ ሐሳብ እናገኛለን። በአምላክ መንፈስ በመመራት አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የጻፈው ነቢዩ ሕዝቅኤል፣ ነፍስ እንደምትሞት ገልጿል። በሌላ ቦታ ላይ ደግሞ አስከሬን ‘የሞተ ነፍስ’ ተብሎ ተገልጿል። (ዘሌዋውያን 21:11 የግርጌ ማስታወሻ) በግልጽ መመልከት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ ነፍስ እንደማትሞት አያስተምርም።

“ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።”—ሕዝቅኤል 18:20

ነፍስ ከሥጋ የተለየች ናት?

ሰዎች ምን ይላሉ?

አንድን ሰው በሕይወት እንዲንቀሳቀስ የምታደርገው ነፍሱ ናት፤ ሰውየው ሲሞት ግን ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ትሄዳለች።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት እናት “16 ነፍስ” እንደወለደች ይገልጻል፤ ይህ ሐሳብ፣ እናትየው ሕይወትና እስትንፋስ ያላቸው ሰዎችን እንደወለደች የሚጠቁም ነው። (ዘፍጥረት 46:18 የግርጌ ማስታወሻ) እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ነፍስ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “የሚተነፍስ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ይህ ቃል እንስሳትንም እንኳ ለማመልከት ተሠርቶበታል። ከዚህም በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ነፍስ ምግብ እንደሚያስፈልጋት ይናገራል። (ዘዳግም 12:20 የግርጌ ማስታወሻ) ነፍስ ከሥጋ የተለየች ነገር ብትሆን ኖሮ መተንፈስ ወይም መብላት ያስፈልጋት ነበር? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ “ነፍስ” የሚለው ቃል የተሠራበት በሕይወት ያለን ሰው ለማመልከት ነው፤ ይህም የሰውየውን አካል፣ ስሜትና ማንነት የሚያጠቃልል ነው።

“እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ 16 [“ነፍስ፣” የግርጌ ማስታወሻ] ነበሩ።”—ዘፍጥረት 46:18

ሰው ሲሞት ነፍሱ ምን ትሆናለች?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ስንሞት ሥጋችን እንደሚበሰብስ ሁሉ በመቃብርም ውስጥ “ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለም።” (መክብብ 9:10) መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ እንደሚገልጸው አንድ ሰው ሲሞት “ወደ መሬት ይመለሳል፤ በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።” (መዝሙር 146:4) ነፍስ ስትሞት ከማንኛውም እንቅስቃሴ ውጭ ትሆናለች፤ በመሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ፣ የሞቱ ሰዎች ‘እንደተኙ’ ተደርገው ተገልጸዋል።—ማቴዎስ 9:24

ሐዘን የደረሰባቸው ባልና ሚስት በአንድ የሬሳ ሣጥን ፊት ቆመው

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

የምትወዳቸውን ሰዎች በሞት ስታጣ የሚከተሉት ጥያቄዎች በአእምሮህ ይፈጠሩ ይሆናል፦ የት ናቸው? በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ? እየተሠቃዩ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሞቱ ሰዎች ምንም እንደማያውቁ ስለሚናገር በሞት የተለዩን ሰዎች እየተሠቃዩ እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ይህ ደግሞ ያጽናናናል። ይሖዋ የሞቱ ነፍሶችን ወደፊት መልሶ ሕያው እንደሚያደርጋቸው የገባውን ቃል ማወቃችንም መጽናኛ ይሰጠናል።—ኢሳይያስ 26:19

“ሙታን . . . ምንም አያውቁም።”—መክብብ 9:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ