የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 3 ገጽ 12-13
  • እምነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እምነት
  • ንቁ!—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እምነት ምንድን ነው?
  • እምነት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • እምነት ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?
  • ዕብራውያን 11:1—“እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም እርግጠኛ የምንሆንበት” ነው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • በእውነት ላይ የተመሠረተ እምነት አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋ በገባው ቃል ላይ እምነት እንዳላችሁ በተግባር አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • እውነተኛ እምነት ምንድን ነው?
    ንቁ!—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 3 ገጽ 12-13

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

እምነት

አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖተኛ እንደሆኑ ቢናገሩም “እምነት” ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይከብዳቸዋል። ለመሆኑ እምነት ምንድን ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?

እምነት ምንድን ነው?

አንዳንድ ሰዎች ምን ይላሉ?

ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት አንድ ሰው እምነት አለው የሚባለው አንድን ነገር ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የሚቀበል ከሆነ ነው። “በአምላክ አምናለሁ” የሚልን አንድ ሃይማኖተኛ ሰው እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ይህ ሰው “በአምላክ የምታምነው ለምንድን ነው?” ተብሎ ቢጠየቅ “ከልጅነቴ ጀምሮ በአምላክ መኖር አምናለሁ” ወይም “ከልጅነቴ ጀምሮ እንዲህ ተብዬ ነው የተማርኩት” በማለት መልስ ይሰጥ ይሆናል። ይህ ሐሳብ አንድን ነገር በጭፍን በመቀበልና በእምነት መካከል እምብዛም ልዩነት የሌለ እንዲመስል ሊያደርግ ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“እምነት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው፤ በተጨማሪም የምናምንበት ነገር በዓይን የሚታይ ባይሆንም እውን መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።” (ዕብራውያን 11:1) አንድ ሰው አንድን ነገር በእርግጠኝነት ሊጠብቅ የሚችለው ይህን ለማድረግ የሚያበቃ አሳማኝ ምክንያት ካለው ነው። እንዲያውም “በእርግጠኝነት መጠበቅ” የሚለው ሐረግ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ ከስሜት ወይም ከምኞት ያለፈ ትርጉም ያስተላልፋል። ስለዚህ እምነት በማስረጃ ተመሥርቶ ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ መሆንን ያመለክታል።

“[የአምላክ] የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል።”—ሮም 1:20

እምነት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ያለ እምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና።”—ዕብራውያን 11:6

ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ብዙ ሰዎች በአምላክ የሚያምኑት እንዲህ ብለው ማመን እንዳለባቸው ስለተማሩ ነው። ‘ከልጅነቴ ጀምሮ እንዲህ ተብዬ ነው የተማርኩት’ ይሉ ይሆናል። ሆኖም አምላክ የሚፈልገው ሰዎች እሱ መኖሩንና አፍቃሪ አምላክ መሆኑን በራሳቸው አረጋግጠው እንዲያመልኩት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን በትክክል ማወቅ እንድንችል እሱን ከልብ መፈለግ እንዳለብን አጥብቆ የሚናገረው ለዚህ ነው።

“ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።”—ያዕቆብ 4:8

እምነት ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ “እምነት የሚገኘው ቃሉን ከመስማት ነው” ይላል። (ሮም 10:17) ስለዚህ በአምላክ ላይ እምነት ለማዳበር የሚረዳን የመጀመሪያው እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሱ የሚያስተምረውን ነገር “መስማት” ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጨምሮ ለበርካታ አንገብጋቢ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ይረዳሃል፦ አምላክ ማን ነው? አምላክ መኖሩን እንዴት እናውቃለን? አምላክ በእርግጥ ያስብልኛል? አምላክ ለወደፊቱ ጊዜ ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

አንድ ሰው ቢራቢሮ ሲመለከት

አምላክ መኖሩን የሚያሳይ በርካታ ማስረጃ በዙሪያችን አለ

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን እንድትማር ሊረዱህ ዝግጁ ናቸው። jw.org የተባለው ድረ ገጻችን እንደሚገልጸው “የይሖዋ ምሥክሮች ሰዎችን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር በጣም ያስደስታቸዋል፤ ይሁን እንጂ ማንንም ሰው የሃይማኖታቸው አባል እንዲሆን አይጫኑም። ከዚህ ይልቅ ሁሉም ሰው የሚያምንበትን ነገር የመምረጥ መብት እንዳለው ስለምንገነዘብ ለሰዎች የምናስተምረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ትምህርት ብቻ ነው።”

ጉዳዩን ስናጠቃልለው፣ እምነትህ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፤ ይህን ማስረጃ የምታገኘው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምታነበውን ነገር እውነተኝነት በራስህ ስታረጋግጥ ነው። እንዲህ የምታደርግ ከሆነ “የሰሙት ነገር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በየዕለቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጉጉት” የተቀበሉትን በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ምሳሌ መከተል ትችላለህ።—ሥራ 17:11

“የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ አለባቸው።”—ዮሐንስ 17:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ