የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 4 ገጽ 4
  • 1 ምክንያታዊ ሁን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1 ምክንያታዊ ሁን
  • ንቁ!—2016
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልማድ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለበጎ ተጠቀሙበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ማስተዋወቂያ
    ንቁ!—2016
  • መጥፎ ልማዶችን ማሸነፍ ይቻላል?
    ንቁ!—2004
  • 2 አመቺ ሁኔታዎችን ፍጠር
    ንቁ!—2016
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 4 ገጽ 4
አንዲት ሴት ስትጽፍ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ልማዶችህን መቆጣጠር የምትችለው እንዴት ነው?

1 ምክንያታዊ ሁን

በሕይወትህ ውስጥ ማድረግ የምትፈልጋቸውን ለውጦች በሙሉ ወዲያውኑ ለማድረግ ትጓጓ ይሆናል። “በዚህ ሳምንት ማጨስ አቆማለሁ፣ መሳደብ እተዋለሁ፣ በጊዜ መተኛት እጀምራለሁ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እጀምራለሁ፣ አመጋገቤን አስተካክላለሁ እንዲሁም ለአያቶቼ ስልክ እደውላለሁ” ብለህ ታስብ ይሆናል። ይሁን እንጂ ግቦችህን ሁሉ በአንድ ጊዜ ለማሳካት የምትሞክር ከሆነ አንዱም ላይ ሳትደርስ ትቀራለህ!

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ . . . ጥበብ ትገኛለች።”—ምሳሌ 11:2

ልኩን የሚያውቅ ሰው ምክንያታዊ ነው። ጊዜውም ሆነ ጉልበቱ እንዲሁም ያሉት ቁሳዊ ነገሮች ውስን እንደሆኑ ይገነዘባል። በመሆኑም ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለመቀየር ከመሞከር ይልቅ ቀስ በቀስ ማሻሻያ ለማድረግ ይጥራል።

ግቦችህን ሁሉ በአንድ ጊዜ ለማሳካት የምትሞክር ከሆነ አንዱም ላይ ሳትደርስ ትቀራለህ!

ምን ማድረግ ትችላለህ?

በአንድ ጊዜ፣ አንድ ወይም ሁለት ልማዶችን ለማዳበር አሊያም ለማስወገድ ጥረት አድርግ። በዚህ ረገድ ቀጥሎ የቀረቡት ነጥቦች ሊረዱህ ይችላሉ፦

  1. ልታዳብራቸው የምትፈልጋቸውን ጥሩ ልማዶችም ሆነ ልታስወግዳቸው የምትፈልጋቸውን መጥፎ ልማዶች በሁለት ረድፍ ዘርዝረህ ጻፋቸው። የተወሰኑ ልማዶችን ብቻ መጻፍ እንዳለብህ አይሰማህ፤ በእያንዳንዱ ዝርዝር ላይ ወደ አእምሮህ የመጣውን ልማድ ሁሉ ጻፍ።

  2. በጻፍከው ዝርዝር ላይ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ለይ፤ ትልቅ ቦታ ከምትሰጣቸው ጀምረህ በቅደም ተከተል አስፍራቸው።

  3. በእያንዳንዱ ረድፍ ላይ ካሰፈርካቸው ልማዶች መካከል አንድ ወይም ሁለቱን ምረጥና በእነዚህ ላይ ለመሥራት ጥረት አድርግ። ከዚያ በኋላ በዝርዝርህ ላይ ባሰፈርካቸው ሌሎች ልማዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ትችላለህ።

መጥፎ ልማዶችህን በጥሩ ልማዶች መተካትህ፣ ልማዶችህን ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካልህ ሊረዳህ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ ቴሌቪዥን በመመልከት ብዙ ጊዜ የማጥፋት ልማድህን ማስወገድ እንዲሁም ቤተሰብህን አዘውትረህ የመጠየቅ ልማድ ማዳበር ትፈልግ ይሆናል፤ ‘በየዕለቱ ከሥራ ወደ ቤቴ እንደገባሁ ቴሌቪዥን ከመክፈት ይልቅ አንድ ጓደኛዬ ወይም የቤተሰቤ አባል ጋ ደውዬ አዋራቸዋለሁ’ የሚል ቁርጥ ውሳኔ አድርግ።

ተዛማጅ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች

“ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ [እወቁ]።”—ፊልጵስዩስ 1:10

“የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል።”—መክብብ 7:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ