የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 5 ገጽ 8-9
  • ልጃችሁን ስለ ፆታ ማስተማር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ልጃችሁን ስለ ፆታ ማስተማር
  • ንቁ!—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተፈታታኙ ነገር
  • ማወቅ የሚኖርባችሁ ነገር
  • ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
  • ከልጆቻችሁ ጋር ስለ ፆታ አውሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • በልጆቻችሁ ልብ ውስጥ የሥነ ምግባር እሴቶችን ትከሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የፆታ ግንኙነት እንድፈጽም የሚደረግብኝን ተጽዕኖ መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 5 ገጽ 8-9
አንዲት እናት ልብስ እያሰጣች ከሴት ልጇ ጋር ስታወራ

ለቤተሰብ | የወላጅ ሚና

ልጃችሁን ስለ ፆታ ማስተማር

ተፈታታኙ ነገር

አንድ ልጅ መረጃ ማግኘት የሚችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስን፣ ሌላ መጽሐፍንና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ሲመለከት

ከጥቂት አሥርተ ዓመታት በፊት ወላጆች፣ ልጆቻቸው ስለ ፆታ ግንኙነት ከሌላ ሰው ከመስማታቸው በፊት ቀድመው የማስተማር አጋጣሚያቸው ሰፊ ነበር። እንዲሁም የልጃቸውን ዕድሜና ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ጉዳዩን በጊዜ ሂደት ማብራራት ይችሉ ነበር።

አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። ዘ ሎሊታ ኢፌክት የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ብሏል፦ “ልጆች ከትንሽነታቸው ጀምሮ ከፆታ ግንኙነት ጋር ለተያያዙ መልእክቶች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፤ እንዲሁም ለልጆች ተብለው በሚዘጋጁ የመገናኛ ብዙኃን ፕሮግራሞች ላይ የሚታዩት ስለ ፆታ የሚያወሱ ነገሮች እየጨመሩ መጥተዋል።” ይህ ታዲያ ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ?

ማወቅ የሚኖርባችሁ ነገር

ከፆታ ጋር የተያያዙ ነገሮች በየቦታው ይገኛሉ። ዴብራ ሮፍማን ቶክ ቱ ሚ ፈርስት በተባለው መጽሐፏ ላይ እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ጭውውቶች፣ ማስታወቂያዎች፣ ፊልሞች፣ መጻሕፍት፣ የዘፈን ግጥሞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ መልእክቶች፣ ጌሞች፣ ፖስተሮች እንዲሁም የሞባይልና የኮምፒውተር ስክሪኖች በፆታዊ ምስሎች፣ ወሬዎችና በተዘዋዋሪ በሚነገሩ እንዲህ ያሉ ሐሳቦች የተሞሉ ናቸው፤ ይህም [በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ በርካታ ልጆችና ትናንሽ ልጆችም ጭምር] ሳይታወቃቸውም ቢሆን በሕይወት ውስጥ ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆነው ነገር . . . የፆታ ግንኙነት እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል።”

የንግዱ ዓለም በከፊል ተጠያቂ ነው። ምርቶችን የሚያስተዋውቁና የሚሸጡ ድርጅቶች ተቃራኒ ፆታን የሚማርኩ ልብሶችን ለልጆች በመሸጥ፣ ከትንሽነታቸው ጀምሮ ለመልካቸው ከተገቢው በላይ ትኩረት መስጠትን እንዲማሩ ያደርጓቸዋል። ሶ ሴክሲ ሶ ሱን የተባለው መጽሐፍ “የንግድ አስተዋዋቂዎች ትናንሽ ልጆች በእኩዮቻቸው ዘንድ ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት እንዳላቸው ስለሚያውቁ ይህን ፍላጎታቸውን ያገናዘበ ምርት ያቀርባሉ” ይላል። አክሎም “ሰዎቹ ከፆታ ጋር የተያያዙ ምስሎችንና ምርቶችን የሚያዘጋጁበት ዓላማ ልጆቹ የፆታ ግንኙነት እንዲፈጽሙ ለማበረታታት ሳይሆን ሸቀጣቸውን ለመሸጥ ነው” ብሏል።

እውቀት ብቻውን በቂ አይደለም። አንድ ሰው መኪና እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ማወቁ ብቻ ኃላፊነት የሚሰማው አሽከርካሪ እንዲሆን አያደርገውም፤ በተመሳሳይም ልጆች ስለ ፆታ ግንኙነት እውቀት ስላላቸው ብቻ ይህን እውቀት ተጠቅመው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ያደርጋሉ ማለት አይደለም።

ዋናው ነጥብ፦ ልጆቻችሁ “ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን” እንዲያሠለጥኑ መርዳታችሁ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አሁን አስፈላጊ ነው።—ዕብራውያን 5:14

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

እናንተ ራሳችሁ ንገሯቸው። ስለ ፆታ ግንኙነት ከልጆቻችሁ ጋር ማውራት ሊከብዳችሁ ቢችልም ይህን ማድረግ የእናንተ ኃላፊነት ነው። ይህን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባችሁ አስታውሱ።—የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ምሳሌ 22:6

ቀስ በቀስ ንገሯቸው። በአንድ ጊዜ ረዘም ያለ ሰዓት ወስዳችሁ ስለ ፆታ ግንኙነት ከልጆቻችሁ ጋር ከማውራት ይልቅ ዘና የምትሉባቸውን የተለያዩ አጋጣሚዎች ተጠቀሙ፤ ምናልባትም አብራችሁ በመኪና ስትጓዙ ወይም ቤት ውስጥ ሥራ ስትሠሩ እንዲህ ማድረግ ትችላላችሁ። ልጃችሁ ሐሳቡን አውጥቶ እንዲነግራችሁ ለማበረታታት የአመለካከት ጥያቄዎችን ተጠቀሙ። ለምሳሌ “እንዲህ ዓይነት ማስታወቂያዎች ደስ ይሉሃል?” ከማለት ይልቅ “ማስታወቂያ የሚያዘጋጁ ሰዎች ምርቶቻቸውን ለመሸጥ እንዲህ ያሉ ምስሎችን የሚጠቀሙት ለምን ይመስልሃል?” ብላችሁ ልትጠይቁት ትችላላችሁ። ልጃችሁ መልስ ከሰጠ በኋላ “አንተስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማሃል?” ልትሉት ትችላላችሁ። —የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ዘዳግም 6:6, 7

ዕድሜያቸውን ያገናዘበ መረጃ ስጧቸው። ትምህርት ቤት ላልገቡ ሕፃናት፣ የፆታ ብልቶችን ትክክለኛ ስሞች እንዲሁም ፆታዊ ጥቃት ከሚያደርሱ ሰዎች ራሳቸውን መጠበቅ ስለሚችሉበት መንገድ ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ። እያደጉ ሲሄዱ ደግሞ ልጆች ስለሚወለዱበት መንገድ አንዳንድ መሠረታዊ መረጃዎችን ልትነግሯቸው ትችላላችሁ። የጉርምስና ዕድሜ ላይ ሲደርሱ፣ ከፆታ ግንኙነት ጋር የተያያዙ አካላዊና ሥነ ምግባራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይበልጥ የተሟላ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል።

የሥነ ምግባር እሴቶችን አስተምሯቸው። ልጃችሁን ከሕፃንነቱ አንስቶ ስለ ሐቀኝነት፣ ስለ ታማኝነት እንዲሁም አክብሮት ስለ ማሳየት አስተምሩት። ከዚያም ስለ ፆታ ግንኙነት ሲነሳ ቀደም ሲል በነገራችሁት ነገር ላይ ተመሥርታችሁ ልታስተምሩት ትችላላችሁ። በተጨማሪም ለልጆቻችሁ የምትመሩባቸውን የሥነ ምግባር እሴቶች በግልጽ ንገሯቸው። ለምሳሌ ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸም ተገቢ እንዳልሆነ የምታምኑ ከሆነ ይህንን አሳውቋቸው። እንዲሁም ይህን ማድረግ ስህተት ብሎም ጎጂ የሆነው ለምን እንደሆነ አብራሩላቸው። ቢዮንድ ዘ ቢግ ቶክ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆች፣ የፆታ ግንኙነት መፈጸማቸው ተገቢ እንዳልሆነ ወላጆቻቸው የሚነግሯቸው ከሆነ በዚያ ዕድሜ የፆታ ግንኙነት ከመፈጸም የመቆጠብ አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው።”

ምሳሌ ሁኑ። ለልጆቻችሁ በምታስተምሩት የሥነ ምግባር እሴት ተመሩ። እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቡባቸው፦ የብልግና ቀልዶች ሲነገሩ ትስቃላችሁ? አለባበሳችሁ የፆታ ስሜት የሚቀሰቅስ ነው? ታሽኮረምማላችሁ? እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ልጆቻችሁ ስለ ሥነ ምግባር እሴቶች የምታስተምሯቸውን ነገር አክብደው ላያዩት ይችላሉ።—የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ሮም 2:21

አዎንታዊ ሁኑ። የፆታ ግንኙነት የአምላክ ስጦታ ነው፤ እንዲሁም በትክክለኛው ሁኔታ ሥር ማለትም በጋብቻ ውስጥ ከተፈጸመ የደስታ ምንጭ ሊሆን ይችላል። (ምሳሌ 5:18, 19) ልጃችሁም ትዳር እስኪመሠርት ድረስ ከታገሠ፣ ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸም ከሚያስከትለው የስሜት ሥቃይና ጭንቀት ነፃ ሆኖ ይህንን ስጦታ ማጣጣም እንደሚችል ንገሩት።—1 ጢሞቴዎስ 1:18, 19

ቁልፍ ጥቅሶች

  • “ልጅን [ወይም “ሕፃንን፤ ወጣትን፣” የግርጌ ማስታወሻ] ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤ በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።”—ምሳሌ 22:6

  • ‘የአምላክን ትእዛዛት ለልጆችህ ደጋግመህ ንገራቸው።’—ዘዳግም 6:6, 7 የግርጌ ማስታወሻ

  • “ታዲያ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርም?”—ሮም 2:21

የወላጅ ሚና

ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት በተለየ መልኩ በልጆች ላይ (በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙትን ጨምሮ) ከእኩዮቻቸው የበለጠ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት ወላጆቻቸው ናቸው። “ምንጊዜም ቢሆን ልጆች፣ መመሪያ እንዲሁም በዙሪያቸው ስላለው ዓለም መረጃ ለማግኘት መጀመሪያ የሚሄዱት በሕይወታቸው ውስጥ በቅርበት ወደሚያገኟቸው አዋቂዎች ነው። ይህን መረጃ ከሌላ ምንጭ ለማግኘት የሚሞክሩት እኛ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ እንዳልሆንን ወይም ሊያነጋግሩን እንደማይችሉ ሲያውቁ አሊያም እንደዚህ ሲሰማቸው ብቻ ነው። . . . ለአሥርተ ዓመታት የተደረገ ጥናት የሚያሳየው ውጤት ሊያስገርመን አይገባም፦ ወላጆች እንደ ፆታ ስለመሳሰሉት ጉዳዮች ከልጆቻቸው ጋር የሚያወሩ ከሆነ ልጆቻቸው ይበልጥ ጤናማና ጥሩ ውሳኔ የማድረግ ችሎታ ያላቸው ብሎም ለድርጊታቸው ኃላፊነት የሚወስዱ ይሆናሉ፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ አደገኛ ከሆኑ ባህርያት ይርቃሉ።”—ቶክ ቱ ሚ ፈርስት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ