የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 5 ገጽ 10-11
  • አስደናቂው ንጥረ ነገር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስደናቂው ንጥረ ነገር
  • ንቁ!—2016
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ካርቦን ሞኖክሳይድ—ድምፅ አልባው ገዳይ
    ንቁ!—2001
  • ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ዑደቶች
    ንቁ!—2009
  • ደኖች የሚሰጡት አገልግሎት—ዋጋው ምን ያህል ነው?
    ንቁ!—2004
  • እርሳስ ያለው አለ?
    ንቁ!—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 5 ገጽ 10-11

አስደናቂው ንጥረ ነገር

የካርቦን አቶሞች

“የካርቦንን ያህል ለሕይወት አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር የለም” በማለት ኔቸርስ ቢልዲንግ ብሎክስ የተባለው መጽሐፍ ይናገራል። ካርቦን ብቻ ያሉት አንዳንድ ባሕርያት፣ ከሌሎች የካርቦን አቶሞች እንዲሁም ከተለያዩ ንጥረ ነገሮች ጋር በመጣመር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ውህዶችን ለመፍጠር ያስችላሉ፤ በመሆኑም በየጊዜው አዳዲስ የካርቦን ውህዶች እየተገኙ እንዲሁም በቤተ ሙከራ እየተሠሩ ነው።

ቀጥሎ የቀረቡት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት የካርቦን አቶሞች እርስ በርስ ተጣምረው የተለያዩ ዓይነት ቅርጾችን ሊፈጥሩም ይችላሉ፤ ለምሳሌ የሰንሰለት፣ የፒራሚድ፣ የቀለበት፣ የቱቦ እንዲሁም ዝርግ የሆነ ቅርጽ ሊፈጥሩ ይችላሉ። በእርግጥም ካርቦን አስደናቂ ንጥረ ነገር ነው!

አልማዝ

አልማዝ

የካርቦን አቶሞች ቴትራሄድሮን በመባል የሚጠሩ ፒራሚዶችን በመሥራት በጣም ጠንካራ የሆነ ቅርጽ ይፈጥራሉ፤ አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮች መካከል በጥንካሬው ተወዳዳሪ የሌለው የሆነው በዚህ ምክንያት ነው። ምርጥ የሚባለው አልማዝ ከካርቦን አቶሞች የተሠራ አንድ ሞለኪውል ነው።

ግራፋይት

እርሳስ

እርስ በርስ ከፍተኛ ትስስር ያላቸው የካርቦን አቶሞች እንደ ዝርግ ወረቀት ያለ ቅርጽ በመሥራት ተነባብረው ይቀመጣሉ፤ በእነዚህ የተነባበሩ ንጣፎች መካከል ጠንካራ ትስስር ስለሌለ ተደራርበው እንደተቀመጡ ወረቀቶች አንዱ ንጣፍ ከሌላው ላይ ሊንሸራተት ይችላል። በዚህ የተነሳ ግራፋይት እንደ ማለስለሻ የሚያገለግል ከመሆኑም ሌላ እርሳስ ለመሥራት ከሚያስፈልጉት ንጥረ ነገሮች ዋነኛው ነው።a

ግራፊን

በእርሳስ የተሠራ መስመር

ግራፊን፣ የስድስት ማዕዘን ቅርጽ በመሥራት እርስ በርስ የተያያዙ በርካታ የካርቦን አቶሞች ንጣፍ ነው። ግራፊን ጫና የመቋቋም አቅሙ ከብረት በብዙ እጥፍ ይበልጣል። በእርሳስ የተሠራ አንድ መስመር አነስተኛ መጠን ያለው ግራፊን ሊኖረው የሚችል ሲሆን ይህም በአንድ ወይም በበርካታ ንጣፎች የተቀመጠ ሊሆን ይችላል።

ፉለሪኖች

ፉለሪኖች

ውስጣቸው ባዶ የሆነው እነዚህ የካርቦን ሞለኪውሎች የተለያየ ቅርጽ ሊኖራቸው ይችላል፤ በማይክሮስኮፕ ብቻ ከሚታዩት ከእነዚህ ሞለኪውሎች አንዳንዶቹ የኳስ አሊያም ደግሞ የቱቦ ዓይነት ቅርጽ (ናኖቲዩብ ይባላሉ) አላቸው። የፉለሪኖች መጠን የሚለካው በናኖሜትር (የአንድ ሜትር አንድ ቢሊዮንኛ) ነው።

ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት

ካርቦን ያላቸው ሕያዋን ፍጥረታት

ዕፀዋት፣ እንስሳት እንዲሁም ሰዎች የተዋቀሩባቸው ሴሎች ከካርቦን የተሠሩ ናቸው፤ ምክንያቱም ካርቦን በካርቦሃይድሬት፣ በስብና በአሚኖ አሲድ ውስጥ ይገኛል።

‘የማይታዩትን የአምላክ ባሕርያት ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል።’—ሮም 1:20

a በሐምሌ 2007 ንቁ! ላይ የወጣውን “እርሳስ ያለው አለ?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

አንድ ኮከብ

ካርቦን—በከዋክብት ውስጥ የሚካሄድ አስደናቂ ቅንብር ውጤት

ካርቦን የሚፈጠረው ሦስት የሂሊየም ኒውክሊየሶች ሲዋሃዱ ነው፤ ሳይንቲስቶች ይህ ውህድ የሚፈጠረው ሬድ ጃየንትስ ተብለው በሚጠሩ ከዋክብት ውስጥ እንደሆነ ያምናሉ። እነዚህ የሂሊየም ኒውክሊየሶች እንዲቀላቀሉ ግን የግድ መሟላት ያለባቸው የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ። ፖል ዴቪስ የተባሉ የፊዚክስ ሊቅ “[በተፈጥሮ ሕጎች] ላይ ትንሽ ሌላው ቀርቶ ከቁጥር የማይገባ ለውጥ እንኳ ቢደረግ ጽንፈ ዓለምና ሕይወት ሊኖሩ አይችሉም፤ የሰው ልጆች መኖርማ ጨርሶ የማይታሰብ ነው” ብለዋል። ነገሮች እንዲህ በሚያስደንቅ መንገድ ሊቀናበሩ የቻሉት እንዴት ነው? አንዳንዶች እንዲሁ በአጋጣሚ እንደሆነ ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ ይህ ቅንብር ጥበበኛ ፈጣሪ መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ የትኛው አመለካከት ይበልጥ አሳማኝ ይመስልሃል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ