የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g17 ቁጥር 4 ገጽ 8
  • አስደናቂዋ አርክቲክ ተርን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስደናቂዋ አርክቲክ ተርን
  • ንቁ!—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክሪስማስ ደሴትን የጎበኘንበት ምክንያት
    ንቁ!—2007
  • በደመ ነፍስ የተገኘ አስደናቂ ጥበብ
    ንቁ!—2007
  • የምድርን አናት በመርከብ ማቋረጥ
    ንቁ!—2010
  • የአርክቲኩ የመሬት አደሴ ቁኒ አንጎል
    ንድፍ አውጪ አለው?
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2017
g17 ቁጥር 4 ገጽ 8
አርክቲክ ተርን

አስደናቂዋ አርክቲክ ተርን

አርክቲክ ተርን የተባሉት ወፎች ከአርክቲክ አካባቢ ተነስተው እስከ አንታርክቲካ በሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጉዞ 35,200 ኪሎ ሜትር የሚያህል ርቀት ይበራሉ ተብሎ ይታመን ነበር። በቅርብ በተደረጉ ጥናቶች ግን ወፎቹ ከዚህ የበለጠ ርቀት እንደሚጓዙ ተረጋግጧል።

አርክቲክ ተርኖች አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው የሚጓዙበት መሥመር

ሥዕላዊ መግለጫው ላይ እንደሚታየው ተርኖች የሚበርሩት ጠመዝማዛ የሆነ አቅጣጫ ተከትለው ነው

ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት ጂዮሎኬተር የሚባሉ ትናንሽ መሣሪያዎች በበርካታ ወፎች ላይ ታሰሩ። እነዚህ ከእስክሪብቶ ክዳን ያነሰ ክብደት ያላቸው አስደናቂ መሣሪያዎች እንዳመለከቱት አንዳንድ ተርኖች ከአርክቲክ እስከ አንታርክቲካ ደርሶ መልስ በአማካይ 90,000 ኪሎ ሜትር ይበርራሉ፤ ይህም ማንኛውም እንስሳ ከሚያደርገው የፍልሰት ጉዞ ረጅሙ እንደሆነ ይታመናል። እንዲያውም አንዲት ወፍ 96,000 ኪሎ ሜትር ያህል በርራለች። ለመሆኑ የሚጓዙትን ርቀት በተመለከተ ቀደም ሲል በነበረው ግምታዊ አኃዝ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

እነዚህ ወፎች ጉዟቸውን የሚጀምሩት ከየትኛውም ቦታ ቢሆን የሚበርሩት ጠመዝማዛ የሆነ አቅጣጫ ተከትለው ነው። በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው አብዛኛውን ጊዜ አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው የሚበርሩት የኤስ ቅርጽ ተከትለው ነው። ይህን የሚያደርጉት ለምንድን ነው? ወፎቹ የሚበርሩት የነፋስን አቅጣጫ ተከትለው ስለሆነ ነው።

ተርኖች 30 ዓመት ገደማ በሚሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከ2.4 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛሉ። ይህ ደግሞ ወደ ጨረቃ ሦስት ወይም አራት ጊዜ የደርሶ መልስ ጉዞ የማድረግ ያህል ነው! አንድ ተመራማሪ “ከ100 ግራም የማይበልጥ ክብደት ያላት ወፍ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ መቻሏ በጣም አስደናቂ ነው” ብሏል። ከዚህም በላይ አርክቲክ ተርኖች በሁለቱም ዋልታዎች ላይ የሚያሳልፉት የበጋ ወቅት በመሆኑ ላይፍ ኦን ኧርዝ፣ ኤ ናቹራል ሂስትሪ የተባለው መጽሐፍ “ከማንኛውም ፍጥረት የበለጠ የቀን ብርሃን ያያሉ” ሲል ገልጿል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ