የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g18 ቁጥር 2 ገጽ 4
  • 1 ቃል ኪዳንን ማክበር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1 ቃል ኪዳንን ማክበር
  • ንቁ!—2018
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • 2ኛው ቁልፍ፦ ቃል ኪዳንን ማክበር
    ንቁ!—2009
  • የጋብቻን ቃለ መሐላ ጠብቆ መኖር የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2015
  • የጋብቻን ሰንሰለት ማጠናከር የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የጋብቻ ቃል ኪዳንን አክብሮ መኖር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2018
g18 ቁጥር 2 ገጽ 4
መልሕቅ፣ ኃይለኛ ማዕበል በሚነሳበት ወቅት አንድ መርከብ ቀጥ ብሎ እንዲቆም ያደርጋል

ቃል ኪዳንን ማክበር ልክ እንደ መልሕቅ ትዳራችሁ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቀጥ ብሎ እንዲቆም ያደርጋል

ለባለትዳሮች

1 ቃል ኪዳንን ማክበር

ምን ማለት ነው?

ቃል ኪዳናቸውን የሚያከብሩ ባልና ሚስቶች ትዳራቸውን የሚመለከቱት ዘላቂ ጥምረት እንደሆነ አድርገው ሲሆን ይህም በመካከላቸው የመተማመን ስሜት ይፈጥራል። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳ የትዳር ጓደኛቸው እንደማይከዳቸው እርግጠኛ ናቸው።

አንዳንድ ባለትዳሮች አብረው ለመኖር የሚገደዱት ማኅበረሰቡ ወይም ዘመዶቻቸው ፍቺውን ስለሚቃወሙ ነው። ሆኖም አብረው ለመኖር የሚያነሳሳቸው በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተመሠረተውን ቃል ኪዳናቸውን ለመጠበቅ ያላቸው ፍላጎት መሆን አለበት።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ባልም ሚስቱን መተው የለበትም።”—1 ቆሮንቶስ 7:11

“የጋብቻ ቃል ኪዳንህን የምታከብር ከሆነ ሊያናድድ የሚችል ነገር ቢያጋጥምህም በቀላሉ አትናደድም። ይቅር ለማለትም ሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ አትዘገይም። ችግሮችን እንደ ጊዜያዊ መሰናክል እንጂ ለፍቺ እንደሚያበቃ ምክንያት አድርገህ አትመለከታቸውም።”—ማይካ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ቃል ኪዳናቸውን የማያከብሩ ባለትዳሮች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ‘በቃ ልንጣጣም አልቻልንም’ ብለው ያስባሉ፤ ከዚያም ከትዳሩ መገላገል የሚችሉባቸውን መንገዶች ይፈልጋሉ።

“ብዙ ሰዎች ትዳር ውስጥ የሚገቡት ‘ካልሆነ እንፋታለን’ ብለው ነው። ሰዎች ትዳር የሚመሠርቱት ስለመፋታት እያሰቡ ከሆነ መጀመሪያውኑ እውነተኛ ቃል ኪዳን ገብተዋል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል።”—ጂን

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ራስህን ፈትሽ

በመካከላችሁ አለመግባባት በሚፈጠርበት ጊዜ . . .

  • የትዳር ጓደኛህን በማግባትህ ትቆጫለህ?

  • ሌላ ሴት ብታገባ ኖሮ ሕይወትህ ምን ሊመስል እንደሚችል ታስባለህ?

  • “የአንቺስ ነገር በቃኝ” ወይም “ለእኔ የምትሆነኝን አላጣም” እንደሚሉት ያሉ ሐሳቦችን ትሰነዝራለህ?

ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል ለአንዱ እንኳ አዎ የሚል መልስ ከሰጠህ ይህ የገባኸውን ቃል ኪዳን በቁም ነገር መመልከት እንዳለብህ የሚጠቁም ነው።

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ተወያዩባቸው

  • የጋብቻ ቃል ኪዳናችንን ችላ ማለት ጀምረን ይሆን? ከሆነ ለምን?

  • ቃል ኪዳናችንን አክብረን ለመኖር የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?

ጠቃሚ ምክሮች

  • አልፎ አልፎ፣ ለትዳር ጓደኛህ ያለህን ፍቅር የሚገልጽ አጭር ነገር ጽፈህ ላክላት

  • በሥራ ቦታህ የትዳር ጓደኛህን ፎቶግራፍ ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ ቃል ኪዳንህን ከፍ አድርገህ እንደምትመለከት አሳይ

  • በየቀኑ፣ አብራችሁ በማትሆኑበት አጋጣሚ ሁሉ ለትዳር ጓደኛህ ስልክ ደውልላት

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው።”—ማቴዎስ 19:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ