የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g18 ቁጥር 2 ገጽ 9
  • 6 ተግሣጽ መስጠት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 6 ተግሣጽ መስጠት
  • ንቁ!—2018
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
  • ጠቃሚ የሆነ ተግሣጽ
    ንቁ!—2015
  • ተግሣጽን የምትመለከተው እንዴት ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ለልጆቻችሁ ተግሣጽ መስጠት የሚኖርባችሁ እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የተግሣጽን ዓላማ መረዳት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2018
g18 ቁጥር 2 ገጽ 9
አንድ ቤተሰብ የሚጓዝበትን ጀልባ አቅጣጫ በመቅዘፊያ ሲያስተካክል

መቅዘፊያ የአንድን ጀልባ አቅጣጫ ለማስተካከል እንደሚረዳ ሁሉ ተግሣጽም አንድን ልጅ በትክክለኛው መንገድ እንዲጓዝ ይረዳዋል

ለወላጆች

6 ተግሣጽ መስጠት

ምን ማለት ነው?

ተግሣጽ መስጠት የሚለው ሐረግ መምራት ወይም ማስተማር ተብሎ ሊተረጎምም ይችላል። ይህም የልጆችን መጥፎ ባሕርይ ማስተካከልን የሚጠይቅበት ጊዜ አለ። በአብዛኛው ግን አንድ ልጅ በሕይወቱ ውስጥ ጥሩ ምርጫ ማድረግ እንዲችል የሚረዳ ሥነ ምግባራዊ ሥልጠና መስጠትን ያመለክታል።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ ወላጆች ለልጃቸው እርማት መስጠት አቁመዋል ሊባል ይችላል፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ ልጁ ለራሱ ያለው ግምት ዝቅ እንዲል ያደርጋል ብለው ይፈራሉ። ይሁን እንጂ ጥበበኛ ወላጆች ለልጆቻቸው ምክንያታዊ የሆኑ መመሪያዎችን በመስጠት ልጆቹ እነዚህን መመሪያዎች እንዲታዘዙ ያሠለጥኗቸዋል።

“ልጆች ሲያድጉ ብስለት ያለው ሰው እንዲሆኑ ከተፈለገ አንዳንድ ገደቦች ሊቀመጡላቸው ይገባል። ልጆች ተግሣጽ የማይሰጣቸው ከሆነ መሪ እንደሌለው መርከብ ሊሆኑ ይችላሉ፤ እንዲህ ያለው መርከብ ቀስ በቀስ አቅጣጫውን ሊስት አልፎ ተርፎም ሊሰምጥ ይችላል።”—ፓምላ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

የማይለዋወጥ አቋም ይኑራችሁ። ልጃችሁ ያወጣችሁትን መመሪያ የማይታዘዝ ከሆነ ተገቢውን ቅጣት ከመስጠት ወደኋላ አትበሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ልጃችሁ ያወጣችሁትን መመሪያ ሲታዘዝ አመስግኑት።

“ታዛዥነት በጠፋበት ዓለም ውስጥ ታዛዦች በመሆናቸው ልጆቼን ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ። ልጆቻችንን የምናመሰግናቸው ከሆነ የምንሰጣቸውን እርማት መቀበል አይከብዳቸውም።”—ክሪስቲን

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል።”—ገላትያ 6:7

ምክንያታዊ ሁኑ። ለልጃችሁ የምትሰጡት ተግሣጽ ከፈጸመው ጥፋትና ከዕድሜው ጋር የሚመጣጠን መሆን ይኖርበታል። አብዛኛውን ጊዜ አንድ ቅጣት ውጤታማ የሚሆነው ቅጣቱ ካጠፋው ነገር ጋር የተያያዘ ሲሆን ነው፤ ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ልጅ በስልኩ አላግባብ ከተጠቀመ ለተወሰነ ጊዜ በስልኩ እንዳይጠቀም መከልከል ጥሩ ውጤት ሊያስገኝ ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥቃቅን ጥፋቶችን በጣም አጋንናችሁ ላለማየት ተጠንቀቁ።

“ልጄ ያልታዘዘው ሆን ብሎ ነው ወይስ ባለማወቅ? የሚለውን ለመለየት ጥረት አደርጋለሁ። መታረም ባለበት ሥር የሰደደ መጥፎ ባሕርይና ትክክለኛው አቅጣጫ የቱ እንደሆነ በመጠቆም ሊስተካከል በሚችል ጥፋት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።”—ዌንደል

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አባቶች ሆይ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው።”—ቆላስይስ 3:21 የግርጌ ማስታወሻ

አፍቃሪ ሁኑ። ልጆች ወላጆቻቸው የሚቀጧቸው ለእነሱ ባላቸው ፍቅር ተነሳስተው እንደሆነ ሲያውቁ ተግሣጹን ተቀብለው ማስተካከያ ማድረግ ቀላል ይሆንላቸዋል።

“ልጃችን ስህተት ሲሠራ ከዚህ በፊት ባደረጋቸው ጥሩ ውሳኔዎች እንደምንኮራበት እናረጋግጥለታለን። አስፈላጊውን ማስተካከያ እስካደረገ ድረስ አሁን የሠራው ስህተት ከዚህ በፊት ያደረጋቸውን መልካም ነገሮች ከንቱ እንደማያደርግበትና እኛም እሱን ለመርዳት ከጎኑ እንደሆንን እንገልጽለታለን።”—ዳንኤል

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው።”—1 ቆሮንቶስ 13:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ