የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g18 ቁጥር 2 ገጽ 13
  • 10 እምነት የሚጣልበት መሆን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 10 እምነት የሚጣልበት መሆን
  • ንቁ!—2018
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ወላጆቼ እምነት እንዲጥሉብኝ ምን ላድርግ?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ወላጆቼ እምነት የማይጥሉብኝ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
  • ደስተኛ ሕይወት ለመምራት መተማመን አስፈላጊ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የበለጠ ነፃነት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2018
g18 ቁጥር 2 ገጽ 13
አንዲት ሴት የባንክ ቤት ዕዳዋን ስትከፍል

ወላጆችህን መታዘዝ የባንክ ዕዳን ከመክፈል ጋር ይመሳሰላል። እምነት የሚጣልብህ በሆንክ መጠን ተጨማሪ ብድር ታገኛለህ፤ በሌላ አባባል የበለጠ አመኔታ ታተርፋለህ

ለወጣቶች

10 አመኔታ ማትረፍ

ምን ማለት ነው?

እምነት የሚጣልባቸው ሰዎች የወላጆቻቸውን፣ የጓደኞቻቸውንና የአሠሪዎቻቸውን አመኔታ ያተርፋሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎች ሕግ ያከብራሉ፤ ቃላቸውን ይጠብቃሉ እንዲሁም ምንጊዜም እውነት ይናገራሉ።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የምታገኘው ነፃነት በአብዛኛው የተመካው ከዚህ በፊት ባተረፍከው አመኔታ ላይ ነው፤ ይህ ሐቅ ከብዙ ነገሮች ጋር በተያያዘ ይሠራል።

“የወላጆችህን አመኔታ ለማትረፍ ከሁሉ የተሻለው መንገድ በሳልና ኃላፊነት የሚሰማህ ሰው መሆንህን በተግባር ማሳየት ነው፤ ይህን ማድረግ ያለብህ ግን ከእነሱ ጋር ስትሆን ብቻ ሳይሆን እነሱ አጠገብህ በማይኖሩበት ጊዜም ጭምር ነው።”—ሴራኤ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “መልካም ምግባር ይኑራችሁ።”—1 ጴጥሮስ 2:12

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነጥቦች በሌሎች ዘንድ ይበልጥ አመኔታ ለማትረፍም ሆነ ሰዎች እንደገና አመኔታ እንዲጥሉብህ ለማድረግ ሊረዱህ ይችላሉ።

ሐቀኛ ሁን። የውሸትን ያህል ሰዎች ባንተ ላይ አመኔታ እንዲያጡ የሚያደርግ ነገር የለም። በተቃራኒው ደግሞ በተለይ የሠራሃቸውን ስህተቶች በተመለከተ ግልጽና ሐቀኛ ከሆንክ የሌሎችን አመኔታ ማትረፍ ትችላለህ።

“ችግር ከማያስከትሉ ነገሮች ጋር በተያያዘ ሐቀኛ መሆን ቀላል ነው። በሰዎች ዘንድ መጥፎ ስም ሊያሰጡህ በሚችሉ ጉዳዮችም ጭምር ሐቀኛ መሆንህ ግን ይበልጥ አመኔታ የሚጣልብህ እንድትሆን ያደርጋል።”—ካይማን

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።”—ዕብራውያን 13:18

ኃላፊነት የሚሰማህ ሰው ሁን። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው በሠራተኛ አስተዳደር ክፍሎች ከሚሠሩ ባለሙያዎች መካከል 78 በመቶ የሚያህሉት “ሥራ ለመቀጠር እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ሦስት ችሎታዎች አንዱ” ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ሆኖ መገኘት እንደሆነ ተናግረዋል። ወጣት እያለህ ኃላፊነት የሚሰማህ ሰው ሆነህ ለመገኘት ጥረት ማድረግህ ትልቅ ሰው ስትሆንም ይጠቅምሃል።

“ወላጆቼ በራሴ ተነሳስቼ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ሳከናውን ያደረግኩትን ነገር ማስተዋላቸው አይቀርም። በራሴ ተነሳሽነት የማደርጋቸው ነገሮች እየጨመሩ ሲሄዱ እነሱ የሚጥሉብኝ አመኔታም እየጨመረ ይሄዳል።”—ሣራ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ይህን የምጽፍልህ በዚህ እንደምትስማማ በመተማመንና ከምጠይቅህም በላይ እንደምታደርግ በማወቅ ነው።”—ፊልሞና 21

ታጋሽ ሁን። አካላዊ እድገት በሌሎች ዘንድ በቀላሉ ሊስተዋል ይችላል፤ ብስለት ያለውና ኃላፊነት የሚሰማው ሰው እየሆንክ መምጣትህን ለማሳየት ግን የተወሰነ ጊዜ ማለፍ ሊኖርበት ይችላል።

“አንድ ጊዜ ያደረግከው ነገር ብቻ የወላጆችህንና የሌሎችን አመኔታ እንድታተርፍ አያደርግም። ይህን ማድረግ የምትችለው ኃላፊነት የሚሰማው ሰው መሆንህን ማሳየትህን ከቀጠልክ ነው።”—ብራንደን

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ትዕግሥትን ልበሱ።”—ቆላስይስ 3:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ