በጠቃሚነቱ ተወዳዳሪ የሌለው መጽሐፍ
የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመና በስፋት የተሰራጨ መጽሐፍ የለም። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ከየትኛውም መጽሐፍ የበለጠ በብዙ ሰዎች እጅ መግባትና የብዙ ሰዎችን ሕይወት መቀየር ችሏል። የሚከተሉትን አኃዛዊ መረጃዎች እስቲ እንመልከት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምና ስርጭት
96.5% የሚሆነው የዓለም ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስን ማግኘት ይችላል
በ3,350 ቋንቋዎች ይገኛል (በሙሉ ወይም በከፊል)
5,000,000,000 ገደማ ቅጂዎች እንደተሰራጩ ይገመታል፤ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የዚህን ያህል በስፋት የተሰራጨ መጽሐፍ የለም
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
JW.ORG የተባለውን ድረ ገጻችንን ጎብኝ። በድረ ገጹ ላይ
መጽሐፍ ቅዱስን በኢንተርኔት ማንበብ ትችላለህ (በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ይገኛል)
መጽሐፍ ቅዱስን ማውረድ ትችላለህ
ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ትችላለህ
መጽሐፍ ቅዱስ የብዙዎችን ሕይወት እንዴት እንደለወጠ የሚያሳዩ ርዕሶችን ማንበብ ትችላለህ
መጽሐፍ ቅዱስን በኢንተርኔት ማጥናት ትችላለህa
መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ጥያቄ ማቅረብ ትችላለህ
የይሖዋ ምሥክሮች እና መጽሐፍ ቅዱስ
የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጎሙና በማሰራጨቱ ሥራ በትጋት ይካፈላሉ።
ባለፉት አሥርተ ዓመታት ካሰራጨናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
በ1901 የወጣው አሜሪካን ስታንዳርድ ቨርዥን
በባይንግተን የተዘጋጀው ዘ ባይብል ኢን ሊቪንግ ኢንግሊሽ
ዚ ኢምፋቲክ ዳያግሎት
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን
ሪቫይዝድ ስታንዳርድ ቨርዥን
የቲሸንዶርፍ ኒው ቴስታመንት
አዲስ ዓለም ትርጉም
ከ180 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል (በሙሉ ወይም በከፊል)
ከ1950 ወዲህ የታተሙ የአዲስ ዓለም ትርጉም ቅጂዎች ብዛት—227 ሚሊዮን
a አሁን የሚገኘው በእንግሊዝኛና በፖርቱጋልኛ ብቻ ነው። ወደፊት ሌሎች ቋንቋዎች ይጨመራሉ።