የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 1 ገጽ 5-7
  • ውጥረት ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውጥረት ምንድን ነው?
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውጥረት ጠቃሚ ወይም ጎጂ ሊሆን ይችላል
  • ውጥረት በእኛ ላይ የሚያስከትለው ውጤት
    ንቁ!—2010
  • ጥሩና መጥፎ ውጥረት
    ንቁ!—1998
  • ውጥረት—መንስኤዎቹና የሚያስከትላቸው ችግሮች
    ንቁ!—2005
  • ውጥረትን መቆጣጠር የምንችልበት መንገድ
    ንቁ!—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 1 ገጽ 5-7
በከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ የቢሮ ሠራተኛ ወደሚሠራበት ሕንፃ ለመግባት እየሮጠ ደረጃ ሲወጣ።

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

ውጥረት ምንድን ነው?

አስቸጋሪ ወይም አደገኛ ሁኔታ ሲያጋጥመን ሰውነታችን ውጥረት ውስጥ ይገባል። በዚህ ወቅት አንጎላችን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሆርሞኖች ይረጫል። እነዚህ ሆርሞኖች ደግሞ የልብ ምትን ይጨምራሉ፤ የደም ግፊትን ይቆጣጠራሉ፤ ብሎም ሳንባችን እንዲሰፋ ወይም እንዲጠብብ እንዲሁም ጡንቻዎቻችን እንዲገታተሩ ያደርጋሉ። እኛ ሳይታወቀን ሰውነታችን በራሱ እርምጃ ለመውሰድ ይዘጋጃል። ውጥረት የፈጠረብን ነገር ካለፈ በኋላ ግን ሰውነታችን ይረጋጋና ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመለሳል።

ውጥረት ጠቃሚ ወይም ጎጂ ሊሆን ይችላል

ውጥረት ተፈጥሯዊ ነገር ነው፤ ሰውነትህ ውጥረት ውስጥ መግባቱ አስቸጋሪ ወይም አደገኛ ሁኔታዎችን ለማለፍ ይረዳሃል። ውጥረት የሚጀምረው ከአንጎል ነው። ጠቃሚ የሆነ ውጥረት ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ ያስችልሃል። በተወሰነ መጠን ውጥረት ውስጥ መሆንህ ግብህ ላይ ለመድረስ እንዲሁም በፈተና፣ በሥራ ቃለ መጠይቅ ወይም በስፖርታዊ ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሊረዳህ ይችላል።

ይሁንና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ከልክ ያለፈ ወይም ሥር የሰደደ ውጥረት ጎጂ ነው። ሰውነትህ ሁልጊዜ ውጥረት ውስጥ ከሆነ አካላዊ፣ ስሜታዊ እና አእምሯዊ ጉዳት ሊደርስብህ ይችላል። ባሕርይህ እንዲሁም ሌሎችን የምትይዝበት መንገድ ይቀየር ይሆናል። ከዚህም ሌላ አንዳንዶች ሥር የሰደደ ውጥረትን ለመቋቋም ሲሉ ለሱሶች ወይም ለሌሎች መጥፎ ልማዶች ይጋለጣሉ። አልፎ ተርፎም ውጥረት በመንፈስ ጭንቀት እንድትዋጥ፣ ሁሉ ነገር እንዲታክትህ እንዲሁም ራስህን ለማጥፋት እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።

ውጥረት በተለያዩ ሰዎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ሊለያይ ይችላል፤ ያም ቢሆን በጥቅሉ ሲታይ ውጥረት ለብዙ ዓይነት በሽታዎች መንስኤ ይሆናል። አብዛኞቹን የሰውነት ክፍሎችም ይነካል።

ውጥረት በሰውነትህ ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ

የነርቭ ሥርዓት

አንድ ሰው በውጥረት ምክንያት ጭንቅላቱን ይዞ።

የነርቭ ሥርዓትህ እንደ አድሬናሊንና ኮርቲሶል ያሉ ሆርሞኖች እንዲመነጩ ያደርጋል። እነዚህ ሆርሞኖች የልብ ምትህ፣ የደም ግፊትህና በደምህ ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርጋሉ፤ ይህም ላጋጠመህ አደጋ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጥ ይረዳሃል። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ብስጩነት፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ ራስ ምታት፣ የእንቅልፍ እጦት

የጡንቻና የአጥንት ሥርዓት

ሰውነትህን ከጉዳት ለመጠበቅ ሲሉ ጡንቻዎችህ ይገታተራሉ። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ቁርጥማት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ መኮማተር

የመተንፈስ ሥርዓት

ተጨማሪ ኦክስጅን ለማስገባት ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ትጀምራለህ። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ቁና ቁና መተንፈስ፣ የትንፋሽ ማጠር እንዲሁም በአንዳንዶች ላይ ድንገተኛ የመሸበር ስሜት (ፓኒክ አታክ)

የደም ዝውውር ሥርዓት

ልብህ ለመላው ሰውነትህ ደም ለማዳረስ ሲል በፍጥነትና በኃይል ይመታል። የደም ሥሮችህ ደግሞ ይበልጥ ወደሚያስፈልግበት ቦታ ለምሳሌ ወደ ጡንቻዎችህ ደም እንዲሄድ ለማድረግ ሲሉ ይጠብባሉ ወይም ይሰፋሉ። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም፣ አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ

የዕጢና የሆርሞን ሥርዓት

ሰውነትህ ውጥረቱን ለፈጠረው ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት እንዲዘጋጅ ዕጢዎችህ አድሬናሊንና ኮርቲሶል የተባሉትን ሆርሞኖች ያመነጫሉ። ተጨማሪ ጉልበት እንዲኖርህ ጉበትህ በደምህ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይጨምረዋል። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • የስኳር በሽታ፣ በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስና በተደጋጋሚ መታመም፣ የስሜት መለዋወጥ፣ ውፍረት መጨመር

የምግብ መፈጨት ሥርዓት

ሰውነትህ ምግብ የሚፈጭበት ሥርዓት ይዛባል። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ድርቀት

የመራባት ሥርዓት

ውጥረት በፆታ ግንኙነትና በፆታ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ከመጠን ያለፈ ውጥረት ለሚከተሉት ነገሮች ሊዳርግ ይችላል፦

  • ስንፈተ ወሲብ፣ የወር አበባ መዛባት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ