የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
  • መከራ የሚደርስብን፣ የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መከራ የሚደርስብን፣ የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለመከራ የዳረጉን የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ናቸው
  • ለሚደርስብን መከራ ሌሎቹ ተጠያቂዎች ክፉ መናፍስት ናቸው
  • አንዳንድ ጊዜ ራሳችንን ለመከራ የምንዳርገው እኛ ራሳችን ነን
  • የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ነው
  • ሰዎች ችግርና መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን መጽናኛ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • መከራ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
ባገኟቸው ጥቂት መሠረታዊ ነገሮች ብቻ ለመኖር የሚታገሉ በድህነት አረንቋ ውስጥ ያሉ ሰዎች።

መከራ የሚደርስብን፣ የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?

ፈጣሪያችን የሚመለከተን እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው። ስለዚህ ችግር እንዲደርስብን አይፈልግም። ሆኖም ሕይወት በችግር የተሞላ ነው። ይህ የሆነው ለምን ድን ነው?

ለመከራ የዳረጉን የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ናቸው

“በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ . . . ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”—ሮም 5:12

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን አዳምንና ሔዋንን ሲፈጥራቸው ፍጹም አእምሮና ፍጹም አካል ነበራቸው። በተጨማሪም አምላክ፣ ምድር ላይ ኤደን በተባለ ውብ ገነት ውስጥ እንዲኖሩ አደረገ። ከአንዱ በስተቀር በገነት ውስጥ ካሉት ዛፎች ሁሉ መብላት እንደሚችሉ ነገራቸው። አዳምና ሔዋን ግን ከዚያ ከተከለከሉት ዛፍ ፍሬ በሉ፤ በዚህ መንገድ ኃጢአት ሠሩ። (ዘፍጥረት 2:15-17፤ 3:1-19) አምላክ በእሱ ላይ በማመፃቸው ባልና ሚስቱን ከገነት አባረራቸው፤ ከዚያ በኋላ ሕይወታቸው በመከራ የተሞላ ሆነ። ከጊዜ በኋላ ልጆች ወለዱ፤ ሕይወት ለልጆቻቸውም ከባድ ነበር። ሁሉም አርጅተው ሞቱ። (ዘፍጥረት 3:23፤ 5:5) የምንታመመው፣ የምናረጀውና የምንሞተው ከእነዚህ ወላጆቻችን ስለተገኘን ነው።

ለሚደርስብን መከራ ሌሎቹ ተጠያቂዎች ክፉ መናፍስት ናቸው

“መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።”—1 ዮሐንስ 5:19

እዚህ ላይ “ክፉው” የተባለው ሰይጣን ነው። ሰይጣን፣ በአምላክ ላይ ያመፀ በዓይን የማይታይ መንፈሳዊ ፍጡር ነው። (ዮሐንስ 8:44፤ ራእይ 12:9) ከጊዜ በኋላ፣ ሌሎች መንፈሳዊ ፍጥረታትም ከሰይጣን ጋር ተባብረዋል። እነዚህ መንፈሳዊ ፍጥረታት፣ አጋንንት ተብለው ተጠርተዋል። ክፉ መናፍስት ኃይላቸውን የሚጠቀሙት ሰዎችን ለማሳሳትና ከፈጣሪ ለማራቅ ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎችን መጥፎ ድርጊት እንዲፈጽሙ የሚገፋፉት እነሱ ናቸው። (መዝሙር 106:35-38፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:1) ሰይጣንና አጋንንቱ ሰዎችን ማሠቃየትና በእነሱ ላይ መከራ ማምጣት ያስደስታቸዋል።

አንዳንድ ጊዜ ራሳችንን ለመከራ የምንዳርገው እኛ ራሳችን ነን

“አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል።”—ገላትያ 6:7

ብዙውን ጊዜ መከራ የሚደርስብን፣ በወረስነው ኃጢአትና ሰይጣን በዓለም ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ የተነሳ ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች በገዛ እጃቸው በራሳቸው ላይ መከራ ያመጣሉ። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? መጥፎ ነገር ያደርጉና ወይም የሞኝነት ውሳኔ ይወስኑና የሚያስከትለውን መዘዝ ለማጨድ ይገደዳሉ። በሌላ በኩል ግን፣ ሰዎች ጥሩ ነገር ሲያደርጉ ጥሩ ነገር ያጭዳሉ። ለምሳሌ ሐቀኛ፣ ትጉ ሠራተኛና አፍቃሪ የሆነ ባልና አባት ብዙ መልካም ነገሮችን ያጭዳል፤ ቤተሰቡም ደስተኛ ይሆናል። ቁማርተኛ፣ ሰካራም ወይም ሰነፍ ከሆነ ግን ራሱንም ሆነ ቤተሰቡን ለድህነት ይዳርጋል። ስለዚህ ፈጣሪያችን የሚለንን መስማታችን ጠቃሚ ነው። እሱ ‘ሰላማችን እንዲበዛልንና’ ሌሎች ብዙ መልካም ነገሮችን እንድናጭድ ይፈልጋል።—መዝሙር 119:165

የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ነው

“በመጨረሻዎቹ ቀናት . . . ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ . . . ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ . . . ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ . . . ይሆናሉ።”—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

በዛሬው ጊዜ የብዙ ሰዎች ባሕርይ ልክ በዚህ ትንቢት ላይ እንደተነገረው ነው። የሰዎች ባሕርይ መለወጡ፣ በዚህ ዓለም ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ውስጥ እንደምንኖር የሚያሳይ አንዱ ማስረጃ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ባለንበት ዘመን ጦርነት፣ ረሃብ፣ ታላላቅ የምድር ነውጦችና በሽታዎች እንደሚከሰቱም ይናገራል። (ማቴዎስ 24:3, 7, 8፤ ሉቃስ 21:10, 11) ብዙዎችን ለመከራና ለሞት እየዳረጉ ያሉት እነዚህ ነገሮች ናቸው።

የአእምሮ ሰላም አገኘሁ

“በ19 ዓመቴ ሽባ ሆንኩ፤ ይህ የደረሰብኝ ከመወለዴ በፊት በሠራሁት መጥፎ ነገር የተነሳ እንደሆነም ተነገረኝ። ይህም በሐዘንና በጭንቀት እንድዋጥ አደረገኝ። በሰው ልጆች ላይ መከራ የሚያመጣው አምላክ እንደሆነ ተምሬ ነበር። አምላክ ጨካኝ ነው ብዬ ስላሰብኩ እሱን መውደድ ከበደኝ። በኋላ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብ ግን ፈጣሪ እንደሚያስብልን ተማርኩ፤ በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ በዋነኝነት ተጠያቂ የሚሆነውም ሰይጣን የተባለ ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር እንደሆነ ተረዳሁ። በተጨማሪም አምላክ በቅርቡ ሰይጣንን እንደሚያጠፋውና እሱ ያስከተለውን ጉዳት ሁሉ እንደሚያስተካክል አወቅኩ። አምላክ እንዲህ ዓይነት ግሩም ባሕርያት እንዳሉት ስለተረዳሁ ለእሱ ያለኝ ፍቅር ጨመረ። እንዲሁም የአእምሮ ሰላም አገኘሁ።”—ሳንጄይ

ሳንጄይ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦

ስለሚደርስብን መከራ እንዲሁም መከራ ሲደርስብን ለመቋቋም ምን እንደሚረዳን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትፈልጋለህ? jw.org የተባለው ድረ ገጽ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው > መከራ በሚለው ሥር ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ