የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 2 ገጽ 10-12
  • ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በትዳርህ ላይ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በትዳርህ ላይ
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማወቅ የሚኖርብህ ነገር
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ቴክኖሎጂ ሕይወታችንን እንዳይቆጣጠረው ማድረግ
    ለቤተሰብ
  • ሥራን ሥራ ቦታ መተው
    ለቤተሰብ
  • አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ
    ለቤተሰብ
  • ፍቺ በስተርጅና—መከላከያው ምንድን ነው?
    ለቤተሰብ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 2 ገጽ 10-12
አንድ ሰው አየር መንገድ ሆኖ ቤት ካለችው ባለቤቱ ጋር በቪዲዮ ጥሪ ሲያወራ

ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በትዳርህ ላይ

ቴክኖሎጂ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ባለትዳሮች ይበልጥ እንዲቀራረቡ ይረዳል። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ባልና ሚስት የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን ተጠቅመው በቀን ውስጥ በፈለጉት ሰዓት መነጋገር ይችላሉ።

ይሁንና አንዳንድ ባለትዳሮች ቴክኖሎጂን አላግባብ በመጠቀማቸው ምክንያት የሚከተሉት ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፦

  • አብረው የሚያሳልፉት ጊዜ ያጣሉ።

  • የግድ አስፈላጊ ባይሆንም ሥራቸውን ቤት ይዘው ይመጣሉ።

  • እርስ በርስ ያለመተማመን ችግር ያጋጥማቸዋል፤ አንዳንዶቹም ታማኝነታቸውን ያጎድላሉ።

ማወቅ የሚኖርብህ ነገር

በጣም ከመሸ በኋላ አልጋ ላይ ሆነው ሞባይላቸውን እየተጠቀሙ ያሉ ባልና ሚስት

አብራችሁ የምታሳልፉት ጊዜ

ማይክል የተባለ አንድ ባለትዳር እንዲህ ብሏል፦ “አንዳንድ ጊዜ ከባለቤቴ ጋር በአካል አብረን ብንሆንም በመንፈስ አብራኝ አይደለችም። ስልኳን እየጎረጎረች ‘እስካሁን የተላኩልኝን መልእክቶች የማይበት አጋጣሚ አላገኘሁም’ ትላለች።” ጆናታን የተባለ ባል ደግሞ “እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች ሥር ባለትዳሮች በአካል አብረው ቢሆኑም ብዙ ኪሎ ሜትሮች ተራርቀው ያሉ ያህል ነው” በማለት ተናግሯል።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ከትዳር ጓደኛህ ጋር እየተነጋገርክ ሳለህ በስልክ ጥሪ ወይም በሞባይል መልእክቶች ምክንያት በተደጋጋሚ ውይይታችሁን ለማቋረጥ ትገደዳለህ?—ኤፌሶን 5:33

ሥራ

የአንዳንድ ሰዎች የሥራ ባሕርይ በተፈለጉበት ጊዜ ሁሉ መገኘትን ይጠይቃል። ሌሎች ግን እንዲህ ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ባያጋጥማቸውም ከሥራ ሰዓት በኋላ ሥራቸውን ለማቆም ይቸገራሉ። ሊ የተባለ አንድ ባለትዳር እንዲህ ሲል በሐቀኝነት ተናግሯል፦ “ከባለቤቴ ጋር አብሬ ለማሳለፍ በመደብኩት ጊዜ ላይ ከሥራ ጋር የተያያዙ የስልክ ጥሪዎች ወይም መልእክቶች ይደርሱኛል። እነዚህን የስልክ ጥሪዎች ወይም መልእክቶች አለመመለስ ይከብደኛል።” ጆይ የተባለች አንዲት ባለትዳር ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “የምሠራው ከቤት ሆኜ ነው፤ ስለዚህ ሥራዬ ሁሌም አብሮኝ አለ ማለት ይቻላል። በዚህ ረገድ ሚዛናዊ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል።”

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የትዳር ጓደኛህ ስታነጋግርህ ሙሉ ትኩረት ሰጥተህ ታዳምጣታለህ?—ሉቃስ 8:18

ታማኝነት

አንድ ጥናት እንደጠቆመው በባለትዳሮች መካከል ለሚነሳው ግጭት አንዱ የተለመደው ምክንያት በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ረገድ አለመተማመን ነው። በጥናቱ ላይ ከተካፈሉት ሰዎች መካከል አሥር በመቶ የሚሆኑት ኢንተርኔት ላይ የለጠፏቸውን አንዳንድ ነገሮች ከትዳር ጓደኛቸው እንደሚደብቁ ተናግረዋል።

በእርግጥም ማኅበራዊ ሚዲያ “ለባለትዳሮች የፈንጂ ቀጠና” ብሎም “ወደ ምንዝር የሚመራ አመቺ መንገድ” ተብሎ መጠራቱ ተገቢ ነው። ከዚህ አንጻር የፍቺ ጠበቃዎች በዛሬው ጊዜ በባለትዳሮች መካከል ለሚፈጸመው ፍቺ ማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት መግለጻቸው አያስገርምም።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ከተቃራኒ ፆታ ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ከትዳር ጓደኛህ ትደብቃለህ?—ምሳሌ 4:23

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን ነገር ለይ

ምግብ በአግባቡ የማይበላ ሰው ጤናማ ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። በተመሳሳይም ከትዳር ጓደኛው ጋር ጊዜ የማያሳልፍ ሰው ጤናማ ትዳር ይዞ ለመቀጠል ይቸገራል።—ኤፌሶን 5:28, 29

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ [እወቁ]።”—ፊልጵስዩስ 1:10

ቴክኖሎጂ በትዳርህ ላይ ችግር እንዳይፈጥር ከዚህ በታች ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል የትኞቹን ሥራ ላይ ልታውሉ እንደምትችሉ ከትዳር ጓደኛህ ጋር ተወያዩ፤ ወይም የራሳችሁን ሐሳቦች ጻፉ።

  • በቀን ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ አብሮ መመገብ

  • የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችንን የማንጠቀምበት ጊዜ መመደብ

  • አብረን ለየት ያሉ ነገሮችን የምናደርግበት ጊዜ መመደብ

  • ማታ ላይ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችንን መዝጋት ወይም ከመኝታችን ማራቅ

  • በቀን ውስጥ ለ15 ደቂቃ ያህል በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሳንረበሽ አብረን ማውራት

  • ከኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችን ላይ የኢንተርኔት አገልግሎትን የምናጠፋበት የተወሰነ ጊዜ መመደብ

ባለትዳሮች ሊወያዩባቸው የሚችሉ ጥያቄዎች

ከትዳር ጓደኛህ ጋር የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለየብቻችሁ ከመለሳችሁ በኋላ በሰጣችሁት መልስ ላይ አብራችሁ ተወያዩ።

  • ትዳራችሁን ለማጠናከር የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በምን መንገዶች ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ?

  • የቴክኖሎጂ ውጤቶች አብራችሁ የምታሳልፉትን ጊዜ ምን ያህል እንደሚሻሙባችሁ ይሰማችኋል?

  • በዚህ ረገድ ምን ማስተካከያ ብታደርጉ ደስ ይላችኋል?

  • ሥራችሁን ሥራ ቦታችሁ ትታችሁ ለመምጣት ትቸገራላችሁ? የትዳር ጓደኛችሁ በሰጣችሁት መልስ ይስማማል?

  • የትዳር ጓደኛችሁ እንዲሰጣችሁ በምትፈልጉት ጊዜና ትኩረት ረገድ ምክንያታዊ እንደሆናችሁ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ።”—1 ቆሮንቶስ 10:24

ጄሰን እና አሌግዛንድራ

“የምሠራው ከቤት ሆኜ ነው፤ ስለዚህ ከመደብኩት ሰዓት በኋላ ላለመሥራት ጥረት አደርጋለሁ። በተጨማሪም ኢሜይል እንደደረሰኝ የሚገልጹ መልእክቶችን ከሆነ ሰዓት በኋላ እዘጋቸዋለሁ። ይህም በሥራ ጉዳዮች ትኩረቴ ሳይከፋፈል ሰዓት እንደማየት ላሉ አስፈላጊ ነገሮች ብቻ ስልኬን እንድጠቀምበት ያስችለኛል።”​—ጄሰን፣ ከባለቤቱ ከአሌግዛንድራ ጋር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ