የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 3 ገጽ 8-9
  • ሳይንቲስቶች ምን ሊነግሩን አይችሉም?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሳይንቲስቶች ምን ሊነግሩን አይችሉም?
  • ንቁ!—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንድ የፅንስ ጥናት ባለሙያ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?
    ንቁ!—2016
  • ሳይንስ በሕይወትህ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ፈጣሪ ሕይወትህን ትርጉም ያለው ሊያደርግልህ ይችላል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ሕይወት እንዴት ጀመረ?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 3 ገጽ 8-9
አንድ የሳይንስ አስተማሪ ከተማሪዎቹ ጋር ሲወያይ።

ሳይንቲስቶች ምን ሊነግሩን አይችሉም?

ሳይንቲስቶች በሳይንስ የተደረሰበትን ያህል ስለ ጽንፈ ዓለም ብዙ ነገር አውቀዋል። ያም ቢሆን በጣም አስፈላጊ ለሆኑ በርካታ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አልቻሉም።

ሳይንስ ጽንፈ ዓለም እና ሕይወት እንዴት እንደጀመረ ሊነግረን ይችላል? በአጭሩ አይችልም። አንዳንዶች ኮስሞሎጂ የተባለው የሳይንስ ዘርፍ ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደተገኘ ማብራራት እንደሚችል ይሰማቸዋል። ማርሴሎ ግሌይዜር የተባሉት የዳርትማውዝ ኮሌጅ የሥነ ፈለክ ፕሮፌሰር አግኖስቲክ (የአምላክን መኖር በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻል የሚያምኑ) ናቸው፤ ሆኖም እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፦ “‘ጽንፈ ዓለም እንዴት ተገኘ?’ ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ ማግኘት አልቻልንም።”

በተመሳሳይም ‘ሕይወት እንዴት ተገኘ?’ የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ ሳይንስ ኒውስ በተባለው መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ርዕስ እንዲህ ይላል፦ “‘ምድር ላይ ሕይወት እንዴት ጀመረ?’ የሚለውን ጉዳይ በትክክል ማወቅ ጨርሶ የማይቻል ይመስላል፤ መጀመሪያ አካባቢ ምድር ላይ ስለተከናወኑት ነገሮች የሚጠቁሙት አብዛኞቹ ጂኦሎጂያዊ መረጃዎች ከጠፉ ዘመን የላቸውም።” እነዚህ ሐሳቦች እንደሚጠቁሙት ሳይንስ ‘ጽንፈ ዓለም እና ሕይወት እንዴት ጀመረ?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻለም።

ይሁንና ‘ምድር ላይ ያሉት ሕይወት ያላቸው ነገሮች የታሰበበት ንድፍ ካላቸው ንድፋቸውን ያወጣው ማን ነው?’ ብለህ ታስብ ይሆናል። የሚከተሉት ጥያቄዎችም ይፈጠሩብህ ይሆናል፦ ‘ጥበበኛና አፍቃሪ የሆነ ፈጣሪ ካለ ፍጥረታቱ የሆኑት የሰው ልጆች ሲሠቃዩ ዝም የሚለው ለምንድን ነው? እርስ በርስ የሚቃረኑ ብዙ ሃይማኖቶችን እያየ ዝም የሚለው ለምንድን ነው? እሱን እናመልካለን የሚሉ ብዙ ሰዎች በርካታ መጥፎ ነገሮችን ሲፈጽሙ ዝም ብሎ የሚያየው ለምንድን ነው?’

የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ከሳይንስ ማግኘት አይቻልም። ይህ ሲባል ግን እነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ የላቸውም ማለት አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አርኪ መልስ አግኝተዋል።

ጊዜ ወስደው መጽሐፍ ቅዱስን ያጠኑ አንዳንድ ሳይንቲስቶች በፈጣሪ መኖር እንዲያምኑ ያደረጓቸውን ምክንያቶች ማወቅ የምትፈልግ ከሆነ jw.org​ን ጎብኝ። ስለ ሕይወት አመጣጥ የተሰጡ አስተያየቶች የሚለውን የቪዲዮ ዓምድ ፈልግ።

ሳይንስ እና መጽሐፍ ቅዱስ አሳምነዋቸዋል

ጆርጂ ኮይዳን፣ የኬሚስትሪ ሊቅ

“ሥራዬ ብዙ ጊዜ ሞለኪውሎችን ‘መገጣጠም’ ይጠይቃል። ቼዝ ከመጫወት ጋር ይመሳሰላል፤ አስቀድሜ ብዙ እርምጃዎችን ማቀድ አለብኝ። አንዱን እርምጃ ብስት ሞለኪውሉ ሊፈራርስ ይችላል። ሥራዬ ውስብስብነት አለው፤ ሆኖም ሕይወት ባላቸው ሴሎች ውስጥ ውስብስብ የሆኑ ሞለኪውሎችን ለማምረት ከሚከናወኑት በሺዎች የሚቆጠሩ ኬሚካላዊ ሂደቶች አንጻር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አንድ ታላቅ ኬሚስት ወይም ፈጣሪ አለ ብዬ እንዳምን ያደረገኝ ይህ ነው።

“መጽሐፍ ቅዱስን ሳጠና እንዲሁ ተራ መጽሐፍ እንዳልሆነ ገባኝ። መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ካበቃ ወደ 2,000 የሚጠጉ ዓመታት አልፈዋል። በውስጡ ያለው ምክር ግን ዛሬም እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ይሰማኛል። በቤተሰብ ውስጥ፣ በሥራ ቦታ እንዲሁም በጎረቤታሞች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን መፍታት ስለሚቻልበት መንገድ እጅግ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል። እንዲህ ያለ አስተማማኝ ምክር ሊሰጥ የሚችለው ከሰው የላቀ ጥበብ ያለው አካል መሆን አለበት የሚለው መደምደሚያ ላይ ደረስኩ።”

ያን ደር ዙው፣ የሥነ ፅንስ ሊቅ

“ፅንስ እያደገ ሲሄድ ሴሎች ተከፋፍለው ነርቭ፣ ጡንቻ፣ አጥንት፣ ደም እና ሌሎች የአካል ክፍሎች ይሆኑና አንድ ሙሉ አካል ያስገኛሉ። ይህ እንዲሆን ሁሉም ሴሎች ተባብረው መሥራት አለባቸው። የፅንሱን እድገት የሚቆጣጠረው ሂደት ከእኛ የመረዳት ችሎታ በላይ ነው። እንደኔ እንደኔ፣ የላቀ ጥበብ ያለው ንድፍ አውጪ ባይኖር ሕይወት ሊገኝ አይችልም።

“በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመዝሙር 139:15, 16 ላይ ፅንስ በእናቱ ማህፀን ውስጥ እድገት ስለሚያደርግበት መንገድ የተሰጠው መግለጫ ሳይንቲስቶች በቅርብ አሥርተ ዓመታት ውስጥ ከደረሱበት ነገር ጋር እንደሚስማማ ይሰማኛል። የዚህ ሐሳብ ጸሐፊ፣ ፈጣሪ ባይገልጥለት ኖሮ ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በፊት እንዲህ ያለ ትክክለኛ መግለጫ እንዴት ሊያሰፍር ይችላል?”

ሮሲዮ ፒካዶ ሄሬሮ፦ አንዲት የኬሚስትሪ አስተማሪ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። የቪዲዮውን ርዕስ jw.org ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ