የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
  • መልሱን ማወቅህ ለውጥ የሚያመጣው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መልሱን ማወቅህ ለውጥ የሚያመጣው ለምንድን ነው?
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለህ
  • ለዕለት ተዕለት ሕይወትህ የሚጠቅም አስተማማኝ መመሪያ ታገኛለህ
  • ለጥያቄዎችህ መልስ ታገኛለህ
  • ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ይኖርሃል
  • አምላክ አለ? ይህን ማወቅ ምን ለውጥ ያመጣል?
    ንቁ!—2015
  • አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማስተዋወቂያ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
ጓደኛሞች ዛፍ ሥር ሆነው ወፎች እያዩ ሲያደንቁ።

መልሱን ማወቅህ ለውጥ የሚያመጣው ለምንድን ነው?

የፈጣሪ መኖር ለውጥ የሚያመጣው ለምንድን ነው? ሁሉን ቻይ አምላክ እንዳለ የቀረበልህ ማስረጃ ካሳመነህ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈውም እሱ መሆኑን የሚያሳየውን ማስረጃ መመርመር ትፈልግ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ሐሳብ ከተማመንክ ደግሞ የሚከተሉትን ጥቅሞች ታገኛለህ።

በሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለህ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “[አምላክ] ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።”—የሐዋርያት ሥራ 14:17

ይህ ለአንተ ምን ትርጉም አለው? ከተፈጥሮ የምትደሰትባቸው ነገሮች ሁሉ ከፈጣሪ የተገኙ ስጦታዎች ናቸው። እነዚህን ስጦታዎች የሰጠህ ፈጣሪ ምን ያህል እንደሚወድህ ስታውቅ ለስጦታዎቹ ያለህ አድናቆት ይጨምራል።

ለዕለት ተዕለት ሕይወትህ የሚጠቅም አስተማማኝ መመሪያ ታገኛለህ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገር ይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።”—ምሳሌ 2:9

ይህ ለአንተ ምን ትርጉም አለው? አምላክ ፈጣሪህ ስለሆነ ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልግህን ነገር ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስን መመርመርህ ለአሁኑ ሕይወትህ የሚጠቅምህ ትምህርት ለማግኘት ይረዳሃል።

ለጥያቄዎችህ መልስ ታገኛለህ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።”—ምሳሌ 2:5

ይህ ለአንተ ምን ትርጉም አለው? ፈጣሪ እንዳለ ማወቅህ እንደሚከተሉት ላሉ መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ይረዳሃል፦ የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው? መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? ስንሞት ምን እንሆናለን? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጥሃል።

ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ይኖርሃል

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው።’”—ኤርምያስ 29:11

መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? እና የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው? የሚሉትን ቪዲዮዎች jw.org ላይ ተመልከት። “መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ” ወይም “የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት” የሚሉትን ሐረጎች የፍለጋ ሣጥኑ ላይ በማስገባት እነዚህን ቪዲዮዎች ማግኘት ትችላለህ።

ይህ ለአንተ ምን ትርጉም አለው? አምላክ ወደፊት ክፋትን፣ መከራን ሌላው ቀርቶ ሞትን እንኳ እንደሚያስወግድ ቃል ገብቷል። አምላክ በገባው ቃል ላይ ስትተማመን ይህ ብሩህ ተስፋ ዛሬ የሚያጋጥሙህን ችግሮች በድፍረት ለመወጣት ያስችልሃል።

አንዳንዶች በፈጣሪ ማመናቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

ሲንዲ።

“አምላክ በሕይወታችን ውስጥ በብዙ አቅጣጫዎች እንደሚረዳን ሳይ ሁሌም እደነቃለሁ። በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ ልንሰጣቸው የሚገቡ ነገሮችን እንድንለይም ሆነ አለመግባባቶችን እንድንፈታ ወይም የእሱ ወዳጆች እንድንሆን እንዲሁም በሌሎች መንገዶች ይረዳናል።”—ሲንዲ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ኤሊስ።

“በፈጣሪ ማመኔ ሕይወቴ አስደሳችና አርኪ እንዲሆንልኝ አድርጓል። አእምሮዬን እንዳሠራ ያደርገኛል፤ ምክንያቱም ስለ እሱ፣ ስለ ፍጥረታቱ እንዲሁም ስለ ቃሉ ገና ልናውቃቸው የምንችላቸው በጣም ብዙ ግሩም ነገሮች አሉ።”—ኤሊስ፣ ፈረንሳይ

ፒተር።

“ፈጣሪያችን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚያስተምረንን ነገር ተግባራዊ ማድረጌ ይበልጥ ደስተኛ እንድሆን ረድቶኛል። አሁን እንደ ቀድሞው ነጭናጫ አይደለሁም፤ ባሉኝ ነገሮች ረክቼ እኖራለሁ። ጥሩ አባት መሆን እንድችልም ረድቶኛል።”—ፒተር፣ ኔዘርላንድስ

ሊዝ።

“ከዚህ ቀደም ሕይወቴ አሰልቺ ዑደት ነበር፤ እበላለሁ፣ እተኛለሁ ከዚያ ደግሞ ተነስቼ ወደ ሥራ እሮጣለሁ። እንዲያው ዝም ብዬ ብቻ ነበር የምኖረው። አሁን ግን ሕይወት ላጣጥመውና ልንከባከበው የሚገባ በጣም ልዩ ስጦታ እንደሆነ ይሰማኛል።”—ሊዝ፣ ኢስቶኒያ

አድሪያን።

“በተፈጥሮዬ ጭንቀታም ነኝ። ክፋት፣ ግፍና መከራ እንደሚወገዱ ማወቄ ግን ጭንቀቴን እንድቋቋም ረድቶኛል።”—አድሪያን፣ ፈረንሳይ

መጽሐፍ ቅዱስ በአእምሯችን ውስጥ ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጠን እንዴት ነው? የሚከተለውን ቪዲዮ ተመልከት፦ መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?—ሙሉው ቪዲዮ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ