የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g22 ቁጥር 1 ገጽ 4-6
  • 1 | ጤንነትህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1 | ጤንነትህ
  • ንቁ!—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ማወቅ ያለብህ ነገር
  • አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር
  • ጤንነትህን ማሻሻል የምትችልባቸው መንገዶች
    ንቁ!—2015
  • ድንገተኛ የጤና እክል ሲያጋጥም
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ጤናህን መጠበቅ የምትችልበት መንገድ
    ንቁ!—1999
  • አካላዊ ጤንነት
    ንቁ!—2019
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2022
g22 ቁጥር 1 ገጽ 4-6
የተለያዩ ጤናማ ምግቦች ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠው።

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

1 | ጤንነትህ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

አንድ ዓይነት ቀውስ ወይም አደጋ ሲከሰት በሰዎች ጤና ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም።

  • ችግሮች በሰዎች ላይ ውጥረት ይፈጥራሉ፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጭንቀት ደግሞ ለበሽታ ያጋልጣቸዋል።

  • ትላልቅ ችግሮች በጤና ተቋማት ላይ ጫና ይፈጥራሉ፤ በቂ የሕክምና ግብአቶች ማግኘትም አስቸጋሪ ይሆናል።

  • አደጋዎች የሰዎችን ኪስ ይጎዳሉ፤ ይህም የተመጣጠነ ምግብ ወይም ጥሩ ሕክምና ለማግኘት አቅም እንዳይኖራቸው ያደርጋል።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ከባድ የጤና እክልና ጭንቀት አስተሳሰብህን ሊያዛባው ይችላል፤ ይህ ደግሞ ጤንነትህን ለመጠበቅ የሚረዱህን ልማዶች ችላ እንድትል ያደርግሃል። በመሆኑም የጤንነትህ ሁኔታ የባሰ እየከፋ ይሄዳል።

  • አስፈላጊውን ሕክምና ካላገኘህ ያሉብህ የጤና ችግሮች እየተባባሱ ሊሄዱ ይችላሉ፤ አልፎም ለሕይወት የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ይደርሱ ይሆናል።

  • ጤናማ ከሆንክ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የተሻለ አቅም ይኖርሃል።

  • የኑሮ ደረጃህ ምንም ይሁን ምን ጤናህን ለመጠበቅ ማድረግ የምትችላቸው ነገሮች አሉ።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

ጥበበኛ ሰው ሊያጋጥሙት የሚችሉ አደጋዎችን አርቆ ያስባል፤ የሚቻል ከሆነም፣ ራሱን ከአደጋዎች ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል። ይህ ከጤና ጋር በተያያዘም እውነት ነው። ንጽሕናን መጠበቅ የበሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል፤ ወይም በሽታው የከፋ እንዳይሆን ያደርጋል። ታምሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንደሚባለው ነው።

“የራሳችንንም ሆነ የቤታችንን ንጽሕና መጠበቃችን በኋላ ላይ ለሕክምናም ሆነ ለመድኃኒት የሚያስፈልገንን ወጪ እንደሚቀንስልን ምንም ጥያቄ የለውም።”—አንድርያስa

a በዚህ መጽሔት ላይ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

ኑሮን በዘዴ—ጠቃሚ ምክሮች

ቀውስ ባለበት ጊዜ ጤናህን ለመጠበቅ እነዚህን እርምጃዎች ውሰድ

ንጽሕናህን ጠብቅ

አንድ ሰው እጁን በሳሙና እና በውኃ ሲታጠብ።

ንጽሕናህን ጠብቅ

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል።” (ምሳሌ 22:3) ጤንነትህን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ነገሮችን አርቀህ አስብ፤ አስፈላጊውን የቅድመ መከላከል እርምጃም ውሰድ።

  • እጅህን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውኃ ታጠብ፤ በተለይ ምግብ ከመንካትህ በፊት ወይም መጸዳጃ ቤት ከተጠቀምክ በኋላ።

  • ቤትህን አዘውትረህ አጽዳ፤ እንዲሁም ፀረ ጀርም ተጠቀም (በተለይ በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን ወይም ዕቃዎችን)

  • የሚቻል ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ከያዛቸው ሰዎች ጋር ያለህን አካላዊ ርቀት ጠብቅ።

ጤናማ አመጋገብ ይኑርህ

የተለያዩ ጤናማ ምግቦች ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠው።

ጤናማ አመጋገብ ይኑርህ

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “የገዛ አካሉን የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል።” (ኤፌሶን 5:29) የምንበላውንና የምንጠጣውን ነገር በጥንቃቄ በመምረጥ አካላችንን እንደምንወደው እናሳያለን።

  • ብዙ ውኃ ጠጣ።

  • የተለያዩ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን ተመገብ።

  • ቅባት፣ ጨውና ስኳር አታብዛ።

  • ሲጋራ አታጭስ፤ ከልክ በላይ አትጠጣ እንዲሁም ዕፅ አላግባብ አትጠቀም።

“መታመም ስለማንፈልግ ጤናማ አመጋገብ እንዲኖረን ጥረት እናደርጋለን። አለዚያ ያለችንን ገንዘብ በሕክምና መጨረሳችን ነው። ገንዘባችንን ጤናማ ነገር ለመብላት ብናውል እንመርጣለን።”—ካርሎስ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴና በቂ እረፍት አድርግ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚሮጥ ሰው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርግ

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል።” (መክብብ 4:6) ሥራ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ እረፍት ማድረግም አስፈላጊ ነው።

  • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርግ፤ አዘውትረህ ዎክ በማድረግ መጀመር ትችላለህ። በዕድሜ፣ በአካል ጉዳት ወይም በከባድ ሕመም የተነሳ አቅምህ የተገደበ ቢሆንም እንኳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤንነትህን ሊያሻሽልልህ ይችላል።

  • እረፍት ለማድረግ ሸለብ ያደረገች ወጣት ሴት።

    በቂ እረፍት አድርግ

    በቂ እረፍት አግኝ። በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚሰማህ ውጥረት እንዲጨምር ያደርጋል፤ እንዲሁም በአንድ ነገር ላይ የማተኮር ችሎታህ ይቀንሳል። በጊዜ ሂደት ደግሞ ለከባድ የጤና ችግር ሊዳርግህ ይችላል።

  • ወደ አልጋ የምትሄድበትን ቋሚ ሰዓት ወስን፤ የወሰንከውን ሰዓትም አክብር። በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ለመተኛትና ለመነሳት ጥረት አድርግ።

  • አልጋ ውስጥ ሆነህ ቴሌቪዥን አትይ፤ ወይም የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች አትጠቀም።

  • ከመተኛትህ በፊት ከባድ ምግብ አትብላ፤ ቡናና ሻይ ወይም የአልኮል መጠጥም አትጠጣ።

“የእንቅልፍ ልማዴ ጤናዬን በጣም እንደሚነካው አስተውያለሁ። በቂ እንቅልፍ ካልተኛሁ አንዳንድ ጊዜ ራሴን ያመኛል፤ ሰውነቴንም ይጫጫነኛል። በቂ እንቅልፍ ካገኘሁ ግን ማንኛውንም ነገር ማስተናገድ እችላለሁ! ብዙ ኃይል ይኖረኛል፤ ቶሎ ቶሎም አልታመምም።”—ጀስቲን

የቫይረስ ወረርሽኝ—ምን ማድረግ ትችላለህ?” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። አንዲት ሴት የቤቷን በር ከፍታ ቫይረስ ስታስገባ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦ የቫይረስ ወረርሽኝ—ምን ማድረግ ትችላለህ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። በተጨማሪም “ጤንነትህን ማሻሻል የምትችልባቸው መንገዶች” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ