የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g22 ቁጥር 1 ገጽ 7-9
  • 2 | መተዳደሪያህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 | መተዳደሪያህ
  • ንቁ!—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ማወቅ ያለብህ ነገር
  • አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር
  • በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ገንዘብህን በጥበብ ተጠቀም
    ንቁ!—2025
  • የገንዘብ አያያዝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ዕዳ በሚኖርባችሁ ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2022
g22 ቁጥር 1 ገጽ 7-9
አንድ አናጺ፣ እንጨት ላይ ሚስማር በመዶሻ ሲመታ።

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

2 | መተዳደሪያህ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች በየቀኑ ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ይላሉ። የሚያሳዝነው ደግሞ በዓለም ላይ የተከሰቱት ቀውሶች ሁኔታው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሆን አድርገዋል። እንዴት?

  • በአንድ አካባቢ ላይ ቀውስ ሲከሰት ኑሮ ይወደዳል፤ ለምሳሌ የምግብ ዋጋና የቤት ኪራይ ይጨምራል።

  • ቀውስ ባለባቸው አካባቢዎች ሥራ አጥነት ይጨምራል፤ ወይም ሰዎች የሚያገኙት ደሞዝ ይቀንሳል።

  • አደጋዎች የንግድ ቦታዎችን፣ መኖሪያ ቤቶችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን ያበላሻሉ ወይም ያወድማሉ፤ ይህም ብዙዎችን ለድህነት ይዳርጋል።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ገንዘብህን በአግባቡ የምትይዝ ከሆነ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት የተሻለ ዝግጁነት ይኖርሃል።

  • ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው፤ ዛሬ ያለህ ገቢ፣ የቆጠብከው ገንዘብ ወይም ንብረትህ ነገ ዋጋውን ሊያጣ ይችላል።

  • ገንዘብ የማይገዛቸው ነገሮች አሉ፤ ለምሳሌ ደስታ ወይም ሰላማዊ የቤተሰብ ሕይወት በገንዘብ ሊገዛ አይችልም።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ምግብና ልብስ ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል።”—1 ጢሞቴዎስ 6:8

ባለን ነገር መርካት ሲባል ያማረን ነገር ሁሉ ይኑረን አለማለት ነው፤ ለዕለት የሚያስፈልገን ነገር ከተሟላልን በዚያ እንረካለን። በተለይ መተዳደሪያችንን የሚነካ ችግር ሲያጋጥም ይህ አመለካከት አስፈላጊ ነው።

ባለህ ነገር መርካት በአኗኗርህ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ሊጠይቅብህ ይችላል። ከአቅምህ በላይ የምትኖር ከሆነ ያለብህ የገንዘብ ችግር እየባሰ መሄዱ አይቀርም።

ኑሮን በዘዴ—ጠቃሚ ምክሮች

ቀውስ ባለበት ጊዜ ገንዘብህን በአግባቡ ለመጠቀም እነዚህን እርምጃዎች ውሰድ

ወጪ ቀንስ

  • አንዲት አረጋዊት ከጓሮ አትክልቷ ውስጥ ካሮት ስትሰበስብ።

    ወጪ ቀንስ

    የግድ ካላስፈለገህ በቀር የቤት ዕቃ ወይም ልብስ አትግዛ። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘አንዳንድ ጊዜ፣ መኪና ከመጠቀም ይልቅ በእግሬ መሄድ እችላለሁ? ጓሮዬ አትክልት መትከል እችል ይሆን?’

  • አንድ ነገር ከመግዛትህ በፊት ‘ይህ ዕቃ የግድ ያስፈልገኛል? አቅሜስ ይፈቅዳል?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ።

  • ከተቻለ የመንግሥት ወይም የእርዳታ ድርጅቶችን ድጎማ ለማግኘት አመልክት።

“በቤተሰብ ቁጭ ብለን ኑሯችንን ገመገምን። ገንዘብ የሚያስወጡ መዝናኛዎችን አንዳንዶቹን ሰረዝን፤ በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ማስተካከያ አደረግን። ብዙ ወጪ የማይጠይቁ ምግቦች መሥራትም ጀመርን።”—ጊፍት

በጀት አውጣ

አንዲት ሴት ደረሰኞችን ሰብስባ ስትመዘግብ፤ በሒሳብ ማሽን እየተጠቀመች ነው።

በጀት አውጣ

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል፤ ችኩሎች ሁሉ ግን ለድህነት ይዳረጋሉ።” (ምሳሌ 21:5) በጀት ማውጣትህ፣ ወጪህ ከገቢህ እንዳይበልጥ ይረዳሃል።

  • በመጀመሪያ የወር ገቢህን ጻፍ።

  • ከዚያም የወሩን ወጪዎችህን በዝርዝር ጻፍ፤ እንዲሁም የገንዘብ አወጣጥህን ገምግም።

  • በመጨረሻም ገቢህን ከወጪህ ጋር አነጻጽር፤ አስፈላጊ ከሆነም ማስተካከያ ልታደርግባቸው ወይም ጨርሶ ልታስቀራቸው የምትችላቸውን ወጪዎች ለይ።

“በየወሩ ገቢና ወጪያችንን በዝርዝር እንጽፋለን። ለአደጋ ጊዜ የሚሆን መጠባበቂያ ገንዘብ እናስቀምጣለን። እንዲሁም ወደፊት ለምናደርጋቸው ወጪዎች የሚሆን ገንዘብ እናጠራቅማለን። ይህም ጭንቀት ቀንሶልናል፤ ምክንያቱም ገቢያችንን እንዴት እንደምንጠቀም አስቀድመን እናውቃለን።”—ካርሎስ

ዕዳ ውስጥ አትግባ / ገንዘብ ቆጥብ

  • አንዲት እናት ልጇን ገንዘብ እንድታጠራቅም ስትረዳት።

    ዕዳ ውስጥ አትግባ/ ገንዘብ ቆጥብ

    ዕዳህን ለመክፈል የሚያስችል ጥሩ ዕቅድ አውጣ። የሚቻል ከሆነ ምንም ገንዘብ አትበደር። መግዛት የሚያስፈልግህ ነገር ካለ አጠራቅመህ ግዛ።

  • ወደፊት የምትጠብቃቸውም ሆነ የማትጠብቃቸው ወጪዎች ሊያጋጥሙህ ስለሚችሉ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ አስቀምጥ።

ታታሪ ሁን / ሥራህ ላይ ጽና

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል።”—ምሳሌ 14:23

  • አንድ አናጺ፣ እንጨት ላይ ሚስማር በመዶሻ ሲመታ።

    ታታሪ ሁን/ ሥራህ ላይ ጽና

    ለሥራህ ጥሩ አመለካከት ይኑርህ። ሥራህ የምትመኘው ዓይነት ባይሆንም እንኳ ገቢ እያስገኘልህ እንደሆነ አትርሳ።

  • ታታሪና እምነት የሚጣልብህ ሁን። ይህ ከሥራ እንዳትባረር ሊረዳህ ይችላል፤ ሌላው ቢቀር ወደፊት ሥራ የማግኘት አጋጣሚህ ሰፊ እንዲሆን ያደርጋል።

“ሥራ አላማርጥም፤ ሥራው የምመኘው ዓይነት ባይሆንም ወይም ደሞዙ ያሰብኩትን ያህል ባይሆንም እንኳ ለመሥራት ፈቃደኛ ነኝ። ምንጊዜም ሥራዬን በኃላፊነት አከናውናለሁ፤ ለራሴ ቢሆን የማደርገውን ያህል ጥራት ያለው ሥራ ለመሥራት እጥራለሁ።”—ዲሚትሪ

ሥራ እየፈለግህ ነው?

  • ሥራ እስኪመጣ አትጠብቅ። ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ባያወጡም እንኳ በአንተ የሥራ መደብ ሰው ሊቀጥሩ የሚችሉ ድርጅቶችን አነጋግር። ሥራ እየፈለግህ እንደሆነ ለወዳጅ ዘመዶችህ ንገራቸው።

  • እንደ ሁኔታው ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኛ ሁን። አንተ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሥራ ማግኘት አስቸጋሪ ነው።

አንድ ባልና ሚስት ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ፤ ልጆቻቸው ደጅ ሲጫወቱ ይታያል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦ “በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ