የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g22 ቁጥር 1 ገጽ 13-15
  • 4 | ተስፋህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 4 | ተስፋህ
  • ንቁ!—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ማወቅ ያለብህ ነገር
  • አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር
  • መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ተስፋ ይሰጣል
  • ተስፋ የሚሰጥ ነገር ከየት ማግኘት እችላለሁ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማስተዋወቂያ
  • 2024ን በተስፋ መጀመር—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2022
g22 ቁጥር 1 ገጽ 13-15
ተገልጦ የተቀመጠ መጽሐፍ ቅዱስ፤ አጠገቡ በአበባ ማስቀመጫ ውስጥ አበባ አለ።

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

4 | ተስፋህ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የዓለም ቀውስ የሚፈጥረው ጭንቀት በሰዎች ጤንነትም ሆነ ስሜት ላይ ትልቅ ጫና ያሳድራል። እነዚህ ነገሮች ተጽዕኖ ያሳደሩባቸው ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ አይኖራቸውም። ታዲያ ለችግራቸው ምን ምላሽ ይሰጣሉ?

  • አንዳንዶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ጨርሶ ማሰብ አይፈልጉም።

  • ሌሎች በመጠጥ ወይም በዕፆች ከችግራቸው ለመደበቅ ይሞክራሉ።

  • ጥቂቶች በሕይወት መኖር ምንም ጥቅም የለውም ብለው ይደመድማሉ። ‘ሞቼ ብገላገልስ?’ ብለው ያስባሉ።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ዛሬ ያሉብህ አንዳንድ ችግሮች ጊዜያዊ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ባልጠበቅኸው መንገድ ነገሮች ይሻሻሉ ይሆናል።

  • ያለህበት ሁኔታ ባይቀየርም እንኳ ችግርህን ለመቋቋም ማድረግ የምትችላቸው ነገሮች አሉ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ተስፋ ይሰጣል፤ ይህ ተስፋ የሰው ልጆች ችግሮች ለዘለቄታው እንደሚወገዱ ይገልጻል።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ስለ ነገ ፈጽሞ አትጨነቁ፤ ምክንያቱም ነገ የራሱ የሆኑ የሚያስጨንቁ ነገሮች አሉት። እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለው።”—ማቴዎስ 6:34

ስለ ነገ አትጨነቅ። እንዲህ ማድረግ የዛሬውን ኃላፊነትህን በአግባቡ እንዳትወጣ እንቅፋት ይሆንብሃል።

እንዲህ ቢሆንስ እያሉ መጥፎ መጥፎውን ማሰብ ውጥረት ከመጨመርና ተስፋን ከማጨለም ውጭ ሌላ ጥቅም የለውም።

ኑሮን በዘዴ—ጠቃሚ ምክሮች

በጎ በጎውን አስብ

አንዲት ሴት በመስኮት አሻግራ እየተመለከተች፤ ፊቷ ላይ መረጋጋት ይታያል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ጎስቋላ ሰው ዘመኑ ሁሉ አስከፊ ነው፤ ደስተኛ ልብ ያለው ሰው ግን ሁልጊዜ ግብዣ ላይ ያለ ያህል ነው።” (ምሳሌ 15:15) ሁልጊዜ መጥፎ መጥፎው የሚታየው ሰው እጁ ላይ ያሉት መፍትሔዎች እንኳ አይታዩትም። በተቃራኒው አዎንታዊ አመለካከት ለችግራችን መፍትሔ የሚሆኑ ሐሳቦች እንዲመጡልን ሊያደርግ ይችላል።

  • ዜና የምታይበትንና የምትሰማበትን ጊዜ ቀንስ።

  • በቀኑ መጨረሻ፣ አመስጋኝ እንድትሆን የሚያደርጉህን ሁለት ወይም ሦስት ነገሮች አስብ።

  • የዕለት ፕሮግራም አውጣ፤ በቀኑ ውስጥ ማከናወን የምትችላቸውን ነገሮች ብቻ አካትት። ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስዱ ሥራዎችን በትንሽ በትንሹ ከፋፍል፤ ይህም በቀኑ መጨረሻ የሥራህን ውጤት ለማየት ያስችልሃል።

የሌሎችን እርዳታ ጠይቅ

አንድ አረጋዊ ሰው በዕድሜ ከእሱ የሚያንስን ሰው ሲያበረታታ።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ራሱን የሚያገል ሰው . . . [ጥበብን] ሁሉ ይቃወማል።” (ምሳሌ 18:1) ጥልቅ ከሆነ ጉድጓድ ውስጥ በራስህ ቧጥጠህ መውጣት አትችልም፤ ከላይ የሚጎትትህ ሰው ካለ ግን ይሳካልሃል።

  • የቤተሰብህን አባላት ወይም ጓደኞችህን እንዲረዱህ ጠይቅ።

  • አንተም እነሱን መርዳት የምትችልባቸውን መንገዶች አስብ። ሌሎችን መርዳት የራስህን ችግር አግዝፈህ እንዳትመለከት ይረዳሃል።

  • ሁሉ ነገር ከጨለመብህና ‘ሞቼ ብገላገልስ?’ የሚለው ስሜት የሚመጣብህ ከሆነ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ሊያስፈልግህ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ያለው ስሜት እንደ መንፈስ ጭንቀት ያለ የጤና እክል እንዳለብህ የሚጠቁም ሊሆን ይችላል። ብዙዎች የሕክምና እርዳታ ማግኘታቸው ሁኔታቸውን አሻሽሎታል።a

a ንቁ! አንድን የሕክምና ዘዴ ለይቶ በመጥቀስ የተሻለ እንደሆነ የሚገልጽ ሐሳብ አያቀርብም።

መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ተስፋ ይሰጣል

አንድ ጥንታዊ ዘማሪ ወደ አምላክ ሲጸልይ እንዲህ ብሏል፦ “ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።” (መዝሙር 119:105) ታዲያ የአምላክ ቃል ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያበራልን እንዴት ነው?

ጨለማ ውስጥ ስንጓዝ መብራት መያዛችን የት መርገጥ እንዳለብን ለማወቅ ይረዳናል። መጽሐፍ ቅዱስም እንደዚህ መብራት ነው፤ ከባድ ውሳኔ ማድረግ ሲያስፈልገን አቅጣጫችንን እንድናውቅ ይመራናል።

ብርሃን በመንገዳችን ላይ በርቀት ያለውን ነገርም አሻግረን እንድናይ ይረዳናል። መጽሐፍ ቅዱስም በተመሳሳይ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን ይረዳናል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ዘር ታሪክ ከመነሻው አንስቶ ከመተረክ ባለፈ ስለ ወደፊቱ ጊዜም ብሩህ ተስፋ ይሰጣል። የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ይነግረናል፦

እንዴት?

በሰው ልጆች ላይ መከራ የመጣው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”—ሮም 5:12

ለምን?

የሰው ልጆች ያቋቋሟቸው መንግሥታት ችግሮቻችንን መፍታት የተሳናቸው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ “አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት [እንደማይችል]” ይናገራል። (ኤርምያስ 10:23) ዛሬ በዓለም ላይ ያለውን ሁኔታ ማየት ብቻ እንኳ ለዚህ ማስረጃ ይሆነናል።

ምን?

አምላክ መፍትሔ ለመስጠት ምን ያደርጋል? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:4

“መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። አንዲት ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያነበበችውን ነገር ለባሏ ስታሳየው።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦ መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ