የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g23 ቁጥር 1 ገጽ 12-14
  • አየር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አየር
  • ንቁ!—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አየር የተደቀነበት አደጋ
  • ፕላኔታችን የተፈጠረችው ለዘላለም እንድትኖር ነው
  • እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች
  • ተስፋ ለማድረግ የሚያበቁ ምክንያቶች—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ንጹሕ አየርና የፀሐይ ብርሃን—የተፈጥሮ “አንቲባዮቲክ”
    ንቁ!—2015
ንቁ!—2023
g23 ቁጥር 1 ገጽ 12-14
አንድ ባልና ሚስት በበረዶ በተሸፈነ ተራራ ላይ እየተጓዙ ጥርት ባለው ሰማያዊ ሰማይ ሥር በደን በተሞሉ ተራሮች የተከበበውን ሐይቅ ሲመለከቱ።

ፕላኔታችን ትተርፍ ይሆን?

አየር

አየር ያስፈልገናል፤ ሆኖም የሚያስፈልገን ለመተንፈስ ብቻ አይደለም። አየር ፀሐይ ከምታመነጫቸው ከአብዛኞቹ ጎጂ ጨረሮች ፕላኔታችንን ይጠብቃታል። አየር ባይኖር ኖሮ በዓለም ዙሪያ ያለው የሙቀት መጠን ከዜሮ በታች ይወርድ ነበር።

አየር የተደቀነበት አደጋ

በምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት በአየር ብክለት የተነሳ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው መሥፈርት መሠረት ጤናማ የሆነ አየር የሚተነፍሰው ከዓለም ሕዝብ መካከል አንድ በመቶው ብቻ ነው።

የአየር ብክለት ለመተንፈሻ አካላት ሕመም፣ ለሳንባ ካንሰር እንዲሁም ለልብ በሽታ መንስኤ እንደሆነ ይታመናል። በየዓመቱ 7,000,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች በአየር ብክለት የተነሳ ያለዕድሜያቸው ይቀጫሉ።

ፕላኔታችን የተፈጠረችው ለዘላለም እንድትኖር ነው

ፕላኔታችን አየር ለሚተነፍሱ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ በዘላቂነት ጤናማ አየር የማቅረብ አቅም አላት። ይሁንና እነዚህ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ውጤታማ የሚሆኑት የሰው ልጆች የሚያደርሱት ብክለት ቁጥጥር ከተደረገበት ብቻ ነው። አንዳንድ ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት።

  • ደኖች ከአየር ውስጥ ካርቦንዳይኦክሳይድን እንደሚወስዱ በደንብ ይታወቃል። ይሁንና በባሕር ዳርቻ በሚገኙ ረግረጋማ አካባቢዎች የሚበቅሉት ማንግሮቭ የተባሉ ዛፎች ከደኖች ይበልጥ አየርን ማጣራት እንደሚችሉ ብዙ ሰዎች አያውቁም። ማንግሮቮች ከአየር ውስጥ የሚያስወግዱት የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን ከትላልቅ ደኖች በአምስት እጥፍ ይበልጣል።

  • በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ትላልቅ አልጌዎች ካርቦንዳይኦክሳይድን ከአየር ወስደው ወደ ውስጣቸው ማስገባት ብቻ ሳይሆን ይቀብሩታል። ለምሳሌ ኬልፕ የተባለው አልጌ ቅጠሎቹ ረጅም ርቀት ለመንሳፈፍ የሚያስችል በአየር የተሞላ ከረጢት አላቸው። ኬልፑ ከውቅያኖሱ ዳርቻ ከራቀ በኋላ ከረጢቱ ይፈነዳል፤ ከዚያም በካርቦንዳይኦክሳይድ የተሞላው ኬልፕ ወደ ውቅያኖሱ ወለል ይዘቅጣል። በዚያም በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ተቀብሮ ይቆያል።

  • ከባቢ አየራችን ያለው ራሱን ከከባድ ብክለት የማጽዳት ችሎታ በኮቪድ-19 ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት ታይቷል። በ2020 በዓለም ላይ ያሉት ፋብሪካዎችና ተሽከርካሪዎች አየሩን መበከላቸውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባቆሙበት ወቅት የአየሩ ንጽሕና በእጅጉ ተሻሽሎ ነበር። “የ2020 የዓለም የአየር ንጽሕና ሪፖርት” እንደገለጸው በሪፖርቱ ላይ ከተካተቱት አገሮች መካከል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የእንቅስቃሴ ገደቡ በተጣለ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአየሩ ንጽሕና እንደተሻሻለ ገልጸዋል።

    ይህን ታውቅ ነበር?

    የአየር ንጽሕና ሊሻሻል ይችላል

    በኒው ዴልሂ፣ ሕንድ ያለውን የጥቃቅን ብናኞች (PM2.5) መጠን የሚያሳይ ግራፍ። በጥር 2020 ለሁሉም ሰው ጤናማ ያልሆነ መጠን ከነበረው ከ128.1 ተነስቶ በነሐሴ 2020 መጠነኛ ሊባል ወደሚችል መጠን ማለትም ወደ 35.5 ገደማ ወርዷል።

    በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት በኒው ዴልሂ፣ ሕንድ ውስጥ ፋብሪካዎችና ተሽከርካሪዎች የሚያስከትሉት የአየር ብክለት በእጅጉ ቀንሶ ነበር። በአየሩ ውስጥ ያሉት ጥቃቅን ብናኞች (PM2.5) መጠንም ወዲያውኑ አሽቆለቆለ። እነዚህ ጥቃቅን ብናኞች (.0025 ሚሊ ሜትር ወይም ከዚያ በታች) በመተንፈሻ አካላትና በሌሎች የአካል ክፍሎች ላይ ከባድ ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። እርግጥ ይህ ለውጥ በዘላቂነት አልቀጠለም፤ ሆኖም ይህ ሁኔታ ከባቢ አየራችን ከፍተኛ መጠን ካለው ብክለት በፍጥነት ማገገም እንደሚችል አሳይቷል።

    በ2019 መገባደጃ አካባቢ ኒው ዴልሂ፣ ሕንድ፤ የአየር ብክለቱ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አካባቢው ደብዝዞ ይታያል።

    © Amit kg/Shutterstock

    በ2019 መገባደጃ

    ኒው ዴልሂ፣ ሕንድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት፤ የአየር ብክለት በመቀነሱ አካባቢው ጥርት ብሎ ይታያል።

    © Volobotti/Shutterstock

    በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት

እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች

አንድ ሰው ወደ ሥራ ቦታው ከተጓዘ በኋላ ብስክሌቱን ሲያቆም።

በብስክሌት መጓዝ የአየር ብክለትን ለመቀነስ ያግዛል

መንግሥታት፣ ኢንዱስትሪዎች የሚያደርሱትን የአየር ብክለት እንዲቀንሱ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል። በተጨማሪም ሳይንቲስቶች የአየር ብክለት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀልበስ የሚያስችሉ አዳዲስ መንገዶችን ለመፈለግ ጥረት እያደረጉ ነው። ለምሳሌ ባክቴሪያዎችን በመጠቀም በካይ ንጥረ ነገሮችን መርዛማ ወዳልሆኑ ነገሮች መቀየር የሚቻልበት ዘዴ አግኝተዋል። ከዚህም ሌላ ባለሙያዎች፣ ሰዎች መኪና ከመጠቀም ይልቅ በእግራቸው ወይም በብስክሌት እንዲጓዙ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ ኃይል ቆጣቢ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ ያበረታታሉ።

ትንሽ ቤት ውስጥ ያለች አንዲት ሴት መሬት ላይ ቁጭ ብላ ምግብ ስታበስል። የምትጠቀምበት ምድጃ ያን ያህል ዘመናዊ ባይሆንም ብዙ ጭስ የለውም።

አንዳንድ መንግሥታት የአየር ብክለትን የሚቀንሱ ዘመናዊ ምድጃዎችን ለዜጎቻቸው እያቀረቡ ቢሆንም አሁንም እነዚህን ምድጃዎች ማግኘት የማይችሉ ብዙ ሰዎች አሉ

ሆኖም እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች አመርቂ አይደሉም። የዓለም የጤና ድርጅትንና የዓለም ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች በ2022 ያጠናቀሩት ሪፖርት ይህን ያሳያል።

ሪፖርቱ እንደሚገልጸው በ2020 ከዓለም ሕዝብ መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ምግብ ለማብሰል በዋነኝነት የሚጠቀመው የአየር ብክለት የሚያስከትሉ ዘዴዎችንና መሣሪያዎችን ነበር። በብዙ ቦታዎች ውስጥ አብዛኞቹ ሰዎች አዳዲስ ምድጃዎችን ወይም ብክለት የማያስከትሉ የነዳጅ አማራጮችን ለመግዛት አቅማቸው አይፈቅድም።

ተስፋ ለማድረግ የሚያበቁ ምክንያቶች—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣ በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን . . . የሰጠው እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል።”—ኢሳይያስ 42:5

የምንተነፍሰውን አየር እንዲሁም አየርን የሚያጣሩ ተፈጥሯዊ ሂደቶችን የፈጠረው አምላካችን ነው። እሱም ወደር የለሽ ኃይል ያለው ከመሆኑም ሌላ ለሰው ልጆች ጥልቅ ፍቅር አለው። ታዲያ የአየር ብክለትን በተመለከተ እርምጃ ይወስዳል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ አይመስልህም? “አምላክ ፕላኔታችን እንደምትተርፍ ቃል ገብቷል” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ፕላኔታችን ከሕዋ ላይ ስትታይ።

ከባቢ አየራችን የተገኘው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ጽንፈ ዓለም የተገኘው በፍጥረት ነው? የሚለውን ቪዲዮ ከjw.org ላይ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ