የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 23
  • የፈርዖን ሕልሞች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የፈርዖን ሕልሞች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ይሖዋ ዮሴፍን አልረሳውም
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • “ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም”
    በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት
  • እንደ ዮሴፍ ወንድሞች ቅናት አድሮብህ ያውቃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 23

ምዕራፍ 23

የፈርዖን ሕልሞች

ሁለት ዓመታት አለፉ፤ ዮሴፍ አሁንም እስር ቤት ውስጥ ነበር። የወይን ጠጅ አሳላፊው አላስታወሰውም ነበር። ከዚያም አንድ ቀን ሌሊት ፈርዖን በጣም ለየት ያሉ ሁለት ሕልሞች አየ። የእነዚህ ሕልሞች ትርጉም ምን ይሆን ሲል አሰበ። ሥዕሉ ላይ ፈርዖን ተኝቶ አየኸው? በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ፈርዖን ጥበበኞቹን አስጠርቶ በሕልሙ ያያቸውን ነገሮች ነገራቸው። ይሁን እንጂ የሕልሞቹን ትርጉም ሊነግሩት አልቻሉም።

በመጨረሻ የወይን ጠጅ አሳላፊው ዮሴፍን አስታወሰው። ፈርዖንን ‘እስር ቤት ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ የሕልሞችን ትርጉም መናገር የሚችል አንድ ሰው ነበረ’ ሲል ነገረው። ወዲያውኑ ፈርዖን ዮሴፍን ከእስር ቤት አስመጣው።

ፈርዖን ያያቸውን ሕልሞች እንዲህ ሲል ለዮሴፍ ነገረው:- ‘መልካቸው ያማረ ሰባት ወፋፍራም ላሞችን ተመለከትኩ። ከዚያም በጣም ቀጫጭን የሆኑ ሰባት ላሞችን ተመለከትኩ። ቀጫጭኖቹ ላሞች ወፋፍራሞቹን ላሞች በሙሉ በሏቸው።

‘በሁለተኛው ሕልሜ ላይ ደግሞ በአንድ አገዳ ላይ የወጡ ያማሩና የፋፉ የእሸት ዛላዎችን ተመለከትኩ። ከዚያም የቀጨጩና የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎችን ተመለከትኩ። ቀጫጭኖቹ የእሸት ዛላዎች ሰባቱን የፋፉ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው።’

ዮሴፍ ፈርዖንን እንዲህ አለው:- ‘ሁለቱ ሕልሞች ትርጉማቸው አንድ ነው። ሰባቱ ወፍራም ላሞችና ሰባቱ የፋፉ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሰባቱ ቀጫጭን ላሞችና ሰባቱ የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ተጨማሪ ዓመታት ናቸው። በግብፅ ምድር የተትረፈረፈ እህል የሚበቅልባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። ከዚያ በኋላ ደግሞ በጣም አነስተኛ የሆነ እህል የሚበቅልባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ።’

ስለዚህ ዮሴፍ ፈርዖንን እንዲህ አለው:- ‘አንድ ጥበበኛ የሆነ ሰው ምረጥና ብዙ እህል በሚኖርባቸው ሰባት ዓመታት እህል እንዲሰበሰብ ኃላፊ አድርገህ ሹመው። ከዚያ በኋላ በጣም አነስተኛ እህል በሚበቅልባቸው ሰባት አስቸጋሪ ዓመታት ሕዝቡ አይራብም።’

ፈርዖን በዚህ ሐሳብ ተስማማ። እህሉን እንዲሰበስብና እንዲያከማች ዮሴፍን ሾመው። ከፈርዖን ቀጥሎ ዮሴፍ በግብፅ ምድር ላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ሰው ሆነ።

ስምንት ዓመታት ካለፉ በኋላ በረሃቡ ዘመን ዮሴፍ ወደ እርሱ የሚመጡ ሰዎች ተመለከተ። እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? አሥሩ ታላላቅ ወንድሞቹ ነበሩ! በከነዓን ምድር በሚገኘው ቤታቸው የነበራቸው እህል እያለቀ ስለ ነበር አባታቸው ያዕቆብ ወደ ግብፅ ላካቸው። ዮሴፍ ወንድሞቹን አወቃቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁትም ነበር። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ዮሴፍ አድጎ ስለ ነበረና ለየት ያለ ልብስ ለብሶ ስለ ነበረ ነው።

ዮሴፍ ልጅ በነበረበት ጊዜ በሕልሙ ወንድሞቹ መጥተው ሲሰግዱለት አይቶ እንደነበረ አስታወሰ። ይህን የሚገልጸውን ታሪክ አንብበህ እንደነበረ ታስታውሳለህ? ስለዚህ ዮሴፍ ወደ ግብፅ የላከው አምላክ እንደሆነና እርሱን ወደዚህ የላከበት ጥሩ ምክንያት እንደነበረው መረዳት ይችላል። ዮሴፍ ምን ያደረገ ይመስልሃል? እስቲ እንመልከት።

ዘፍጥረት 41:​1-57፤ 42:​1-8፤ 50:​20

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ