የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 36
  • ከወርቅ የተሠራው ጥጃ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከወርቅ የተሠራው ጥጃ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቃላቸውን አልጠበቁም
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃ ሠሩ
    ሥዕላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 36

ምዕራፍ 36

ከወርቅ የተሠራው ጥጃ

እንዴ! እንዴ! ሰዎቹ ምን እያደረጉ ነው? ለአንድ ጥጃ እየጸለዩ ነው! ይህን እያደረጉ ያሉት ለምንድን ነው?

ሙሴ ተራራው ላይ ወጥቶ ረጅም ጊዜ ሲቆይ ሕዝቡ ‘ሙሴ ምን እንደደረሰበት አናውቅም። ስለዚህ ከዚህ ምድር የሚያወጣን አምላክ እንሥራ’ አሉ።

የሙሴ ወንድም የሆነው አሮን ‘እሺ፣ የወርቅ ጉትቻዎቻችሁን አውልቃችሁ ስጡኝ’ አላቸው። ሕዝቡ ጉትቻዎቻቸውን አውልቀው ሲሰጡት አሮን ጉትቻዎቹን አቀለጣቸውና አንድ የወርቅ ጥጃ ሠራ። ሕዝቡም ‘ከግብፅ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!’ አሉ። ከዚያም እስራኤላውያን ትልቅ ድግስ አዘጋጁና ከወርቅ የተሠራውን ጥጃ አመለኩ።

ይሖዋ ይህን ሲመለከት በጣም ተቆጣ። ስለዚህም ሙሴን ‘ፈጥነህ ውረድ። ሕዝቡ ኃጢአት ሠርተዋል። ሕጎቼን ችላ ብለው ለአንድ የወርቅ ጥጃ እየሰገዱ ነው’ አለው።

ሙሴ ከተራራው ፈጥኖ ወረደ። ሕዝቡ ወዳሉበት ቦታ ሲደርስ የተመለከተው ይህን ነበር። ሕዝቡ ከወርቅ በተሠራው ጥጃ ዙሪያ እየዘፈኑ ይጨፍሩ ነበር! ሙሴ በጣም ስለተናደደ ሕጎቹ ተጽፎባቸው የነበሩትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሲወረውራቸው ተሰባበሩ። ከዚያም ከወርቅ የተሠራውን ጥጃ ወስዶ አቀለጠው። ከዚያ በኋላም ዱቄት እስኪሆን ድረስ ፈጨው።

ሕዝቡ በጣም መጥፎ የሆነ ድርጊት ፈጽመው ነበር። ስለዚህ ሙሴ የተወሰኑ ሰዎች ሰይፋቸውን እንዲታጠቁ ነገራቸው። ‘ከወርቅ የተሠራውን ጥጃ ያመለኩ ክፉ ሰዎች መሞት አለባቸው’ ሲል ሙሴ ተናገረ። ስለዚህ ሰይፋቸውን የታጠቁት ሰዎች 3, 000 ሰዎች ገደሉ! ይህ ሁኔታ ማንኛውንም ዓይነት የሐሰት አማልክት ማምለክ እንደሌለብንና ይሖዋን ብቻ ማምለክ እንዳለብን አያሳይምን?

ዘጸአት 32:​1-35

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ