የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 81
  • በአምላክ እርዳታ መተማመን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአምላክ እርዳታ መተማመን
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ሕዝቦች ከባቢሎን ወጡ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የዕዝራ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተነዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ ተማምናችሁ መኖር ትችላላችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ከባቢሎን ምርኮ የኢየሩሳሌም ግንቦች እስከ ተሠሩበት
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 81

ምዕራፍ 81

በአምላክ እርዳታ መተማመን

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከባቢሎን ተነስተው ረጅም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ከተማይቱ ትልቅ የፍርስራሽ ክምር ሆና ነበር። በዚያ የሚኖር አንድም ሰው አልነበረም። እስራኤላውያን ሁሉንም ነገር እንደገና እንደ አዲስ መገንባት ነበረባቸው።

መጀመሪያ ከሠሯቸው ነገሮች መካከል አንዱ መሠዊያ ነበር። ይህ ለይሖዋ የእንስሳት መሥዋዕቶች ወይም ስጦታዎች የሚያቀርቡበት ቦታ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመሩ። ይሁን እንጂ በአቅራቢያቸው በነበሩት አገሮች ውስጥ የሚኖሩት ጠላቶቻቸው እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን እንዲገነቡ አይፈልጉም ነበር። ስለዚህ መሥራታቸውን እንዲያቆሙ ሊያስፈራሯቸው ሞከሩ። በመጨረሻም እነዚህ ጠላቶቻቸው አዲሱ የፋርስ ንጉሥ የግንባታውን ሥራ እንዲያቆሙ የሚያደርግ ሕግ እንዲያወጣ አደረጉ።

ብዙ ዓመታት አለፉ። እስራኤላውያን ከባቢሎን ከተመለሱ 17 ዓመት ሆኗቸው ነበር። ይሖዋ ሕዝቡ ግንባታውን እንደገና እንዲጀምሩ እንዲነግሯቸው ሐጌና ዘካርያስ የተባሉትን ነቢያት ላከ። ሕዝቡ በአምላክ እርዳታ በመተማመን ነቢያቱ ያሏቸውን አደረጉ። ሕጉ እንዳይሠሩ የሚከለክል የነበረ ቢሆንም እንደገና መገንባት ጀመሩ።

ስለዚህ ተንትናይ የተባለ አንድ የፋርስ ባለሥልጣን መጣና እስራኤላውያንን ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ማን እንደፈቀደላቸው ጠየቃቸው። እስራኤላውያንም በባቢሎን ሳሉ ንጉሥ ቂሮስ ‘ወደ ኢየሩሳሌም ሂዱና የአምላካችሁን የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሥሩ’ ብሏቸው እንደነበረ ነገሩት።

ቂሮስ ከመሞቱ በፊት በእርግጥ ይህን ትእዛዝ መስጠት አለመስጠቱን ለማረጋገጥ ተንትናይ ወደ ባቢሎን ደብዳቤ ላከ። ብዙም ሳይቆይ አዲሱ የፋርስ ንጉሥ መልሱን በደብዳቤ ላከ። ደብዳቤው ቂሮስ ይህን ትእዛዝ እንዳወጣ የሚገልጽ ነበር። በተጨማሪም ንጉሡ ‘እስራኤላውያን የአምላካቸውን ቤተ መቅደስ ይሥሩ። አንተም እንድትረዳቸው አዝዤሃለሁ’ ብሎ ጽፎ ነበር። ቤተ መቅደሱ በአራት ዓመት ገደማ ተሠርቶ አለቀ፤ እስራኤላውያንም በጣም ተደሰቱ።

ይህ ከሆነ በኋላ ብዙ ዓመታት አለፉ። ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ካለቀ 48 ዓመታት ያህል ሆኖት ነበር። በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ድሆች ነበሩ፤ ከተማይቱና የአምላክ ቤተ መቅደስም እምብዛም የሚማርኩ አልነበሩም። በዚያ ወቅት በባቢሎን የነበረው እስራኤላዊው ዕዝራ የአምላክን ቤተ መቅደስ ማስዋብ እንደሚያስፈልግ ተገነዘበ። ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?

ዕዝራ የፋርስን ንጉሥ አርጤክስስን ለማነጋገር ሄደ። ይህ ጥሩ ንጉሥ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት የሚሄደው ብዙ ስጦታ ሰጠው። ዕዝራ እነዚህን ስጦታዎች ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ እንዲረዱት በባቢሎን ይኖሩ የነበሩትን እስራኤላውያን ጠየቃቸው። ወደ 6, 000 የሚጠጉ ሰዎች አብረው ለመሄድ ፈቃደኞች ሆኑ። ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት የሚሄዱት ብዙ ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎች ውድ ነገሮች ነበሩ።

በመንገዱ ላይ ክፉ ሰዎች ስለሚያጋጥሙ ዕዝራ በጣም ተጨነቀ። እነዚህ ሰዎች ብራቸውንና ወርቃቸውን ወስደው ሊገድሏቸው ይችላሉ። ስለዚህ ሥዕሉ ላይ እንደምታየው ዕዝራ ሕዝቡን ጠርቶ አንድ ላይ ሰበሰበ። ከዚያም ረጅሙን ጉዞ ተጉዘው ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ከአደጋ እንዲጠብቃቸው ወደ ይሖዋ ጸለዩ።

ይሖዋ ከማንኛውም አደጋ ጠብቋቸዋል። ለአራት ወራት ከተጓዙ በኋላ በሰላም ኢየሩሳሌም ደረሱ። ይህ ሁኔታ ይሖዋ በእሱ እርዳታ የሚተማመኑትን ሰዎች ሊጠብቃቸው እንደሚችል አያሳይም?

ዕዝራ ከምዕራፍ 2 እስከ 8

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ