የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rs ገጽ 117-ገጽ 121
  • ማበረታቻ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማበረታቻ
  • ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መንግሥት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • እውነተኛው ሃይማኖት የሚሰጠው ተስፋ
    ንቁ!—1999
  • ተመልሳ በምትቋቋመው ገነት የሚኖረው ሕይወት
    ንቁ!—2008
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
rs ገጽ 117-ገጽ 121

ማበረታቻ

ፍቺ:- ድፍረት የሚሰጥ ወይም ተስፋ የሚያሳድር ነገር ማበረታቻ ይባላል። ማንም ሰው ማበረታቻ ያስፈልገዋል። በግል ቀርቦ በመርዳት ወይም አድናቆትና ምስጋና በመግለጽ ማበረታታት ይቻላል። ይህም ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥመው ችግሩን እንዴት መወጣት እንደሚችል መርዳትን ወይም የወደፊቱ ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ለመጠበቅ በሚረዱ ምክንያቶች ላይ መወያየትን ይጨምራል። ተወዳዳሪ የሌለው ማበረታቻ የሚገኘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከዚህ በታች የቀረቡት ጥቅሶች የተለያዩ ሁኔታዎች ያጋጠሟቸውን ሰዎች ለመርዳት ሊጠቅሙ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ የሐዘኔታ መንፈስ ማሳየት ብቻ የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ ይችላል።—ሮሜ 12:15

በሕመም ለሚሰቃዩ:-

ራእይ 21:4, 5:- “[አምላክ] እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። በዙፋንም የተቀመጠው:- እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም:- እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።”

ማቴ. 9:35:- “ኢየሱስም . . . የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፣ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፣ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።” (ያደርግ የነበረውን ፈውስ ከመንግሥቱ ስብከት ጋር በማያያዝ በሺህ ዓመት ግዛቱ ለሚያደርገው ነገር አስደናቂ የሆነ ጥላነት ያለው ምሳሌ አሳይቷል።)

2 ቆሮ. 4:13, 16:- “እኛ ደግሞ እናምናለን . . . ስለዚህም አንታክትም፣ ነገር ግን የውጪው ሰውነታችን [ሥጋዊው አካላችን] ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል [አዲስ ጉልበት ያገኛል]።” (በሥጋዊ ሁኔታ እየሟሸሽን ልንሆን እንችላለን። ነገር ግን የአምላክን ውድ ተስፋዎች መመገባችንን ስንቀጥል እንታደሳለን።)

በተጨማሪ ሉቃስ 7:20–23⁠ን ተመልከት።

የሚወዷቸውን ዘመዶች በሞት ላጡ ሰዎች:-

ኢሳ. 25:8, 9:- “ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ . . . በዚያም ቀን:- እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፣ ያድነንማል፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን ይባላል።”

ዮሐ. 5:28, 29:- “በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።”

ዮሐ. 11:25, 26:- “ኢየሱስም:- ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።”

መዝ. 146:5, 9:- “ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን [“ደስተኛ” አዓት] ነው፤ . . . ድሀ አደጎችንና [“አባት የሌለውን ልጅና” አዓት] ባልቴቶችን ይቀበላል።” (አሁንም እንኳ ለሟች ቤተሰቦች አምላክ እንዲህ የመሰለ ፍቅራዊ አሳቢነት አሳይቷል።)

በተጨማሪ ሉቃስ 7:11–16፤ 8:49–56⁠ን ተመልከት።

የአምላክን ፈቃድ በማድረጋቸው ስደት ለደረሰባቸው ሰዎች:-

መዝ. 27:10:- “አባቴና እናቴ ትተውኛልና፣ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።”

1 ጴጥ. 4:16:- “ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።”

ምሳሌ 27:11:- “ልጄ ሆይ፣ ጠቢብ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኘው፣ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።” (የታመንን ሆነን በመገኘት ማንም ሰው ከባድ ችግር ሲያጋጥመው አምላክን ማገልገሉን ያቆማል በማለት ሰይጣን ላቀረበው የሐሰት ክስ መልስ ለመስጠት እንችላለን።)

ማቴ. 5:10–12:- “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን [“ደስተኞች” አዓት] ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን [“ደስተኞች” አዓት] ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”

ሥራ 5:41, 42:- “[ሐዋርያት] ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቆጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።”

ፊልጵ. 1:27–29:- “ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ። በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፣ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፣ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም።”

በፍትሕ መጓደል ምክንያት ለሚተክዙ:-

መዝ. 37:10, 11:- “ገና ጥቂት፣ ኃጢአተኛም አይኖርም፤ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።”

ኢሳ. 9:6, 7:- “ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም [“መስፍናዊ አገዛዝ” አዓት ] በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። [“የሠራዊት ጌታ” አዓት ] የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።”—ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።

ዳን. 2:44:- “በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፣ ለዘላለምም ትቆማለች።”

በተጨማሪ ኢሳይያስ 32:1, 2፤ 2 ጴጥሮስ 3:13⁠ን ተመልከት።

በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ለተጨነቁ:-

ኢሳ. 65:21, 22:- “ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተክሉም፤ . . . እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።”

መዝ. 72:8, 16 አዓት:- “[መሲሐዊው ንጉሥ] ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል። በምድር ላይ ብዙ እህል ይኖራል፣ በተራሮችም ጫፍ ይትረፈረፋል።”

ማቴ. 6:33:- “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ [ለሕይወት የሚያስፈልጉት ቁሣዊ ነገሮች] ይጨመርላችኋል።”

ሮሜ 8:35, 38, 39:- “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፣ ወይስ ጭንቀት፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ራብ፣ ወይስ ራቁትነት፣ ወይስ ፍርሃት፣ ወይስ ሰይፍ ነውን? ሞት ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ ግዛትም ቢሆን፣ ያለውም ቢሆን፣ የሚመጣውም ቢሆን፣ ኃይላትም ቢሆኑ፣ ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።”

በተጨማሪ ዕብራውያን 13:5, 6⁠ን ተመልከት።

በጉድለቶቻቸው ምክንያት ቅስማቸው ለተሰበረ ግለሰቦች:-

መዝ. 34:18:- “እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፣ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።”

መዝ. 103:13, 14:- “አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፣ እኛ አፈር እንደሆንን አስብ። [“አፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።” አዓት ]”

ነህ. 9:17:- “አንተ ግን ይቅር ባይ፣ ቸርና መሐሪ አምላክ፣ ለቁጣም የምትዘገይ፣ ምሕረትንም የምታበዛ ነህ።”

2 ጴጥ. 3:9, 15:- “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፣ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። የጌታችንንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደሆነ ቁጠሩ።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ