የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gt ምዕ. 90
  • የትንሣኤ ተስፋ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የትንሣኤ ተስፋ
  • እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ትንሣኤና ሕይወት”
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • “አምናለሁ”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • “አምናለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ለማርታ የተሰጠ ምክርና ስለ ጸሎት የተሰጠ ትምህርት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
gt ምዕ. 90

ምዕራፍ 90

የትንሣኤ ተስፋ

በመጨረሻ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ወደ ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ ወደምትገኘው ቢታንያ ወደምትባለው መንደር ዳርቻ ደረሰ። አልዓዛር ሞቶ የተቀበረው ከጥቂት ቀናት በፊት ነው። እህቶቹ ማርያምና ማርታ አሁንም ሐዘን ላይ ናቸው። እነርሱን ለማጽናናትም ብዙ ሰዎች ወደ ቤታቸው መጥተው ነበር።

ሐዘን ላይ እያሉ አንድ ሰው ኢየሱስ እየመጣ መሆኑን ለማርታ ነገራት። ስለዚህ እሱን ለመቀበል ከቤት ወጥታ በፍጥነት ሄደች፤ ለእህቷም የነገረቻት አይመስልም። ማርታ ኢየሱስ ጋር ስትደርስ “አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው፤ ባለፉት አራት ቀናት እሷና እህቷ ይህን ቃል ብዙ ጊዜ ደጋግመው ሳይናገሩት አይቀሩም።

ይሁን እንጂ ማርታ አሁንም ቢሆን ኢየሱስ ለወንድሟ አንድ ነገር ሊያደርግለት እንደሚችል የሚጠቁም ነገር በመናገር ያላትን ተስፋ ገልጻለች። “ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ” አለችው።

ኢየሱስ “ወንድምሽ ይነሣል” ሲል ቃል ገባላት።

ማርታ ኢየሱስ የተናገረው አብርሃምና ሌሎች የአምላክ አገልጋዮችም ሲጠባበቁት ስለነበረውና ወደፊት ስለሚከናወነው ምድራዊ ትንሣኤ እንደሆነ አድርጋ ተረድታ ነበር። ስለዚህ “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ” ብላ መለሰችለት።

ይሁን እንጂ ኢየሱስ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ” ብሎ በመመለስ ያኔውኑ ከኀዘኗ የሚያሳርፍ ተስፋ ሰጣት። “የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም” በማለት አምላክ በሞት ላይ ሥልጣን እንደሰጠው ማርታ እንድታስታውስ አደረጋት።

ኢየሱስ ማርታን እንዲህ ሲላት በዚያን ጊዜ የነበሩ የታመኑ አገልጋዮች ፈጽሞ አይሞቱም ማለቱ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ በእሱ ማመን ወደ ዘላለም ሕይወት ሊመራ እንደሚችል ለመናገር ፈልጎ ነው። በመጨረሻው ቀን አብዛኞቹ ሰዎች ከሞት በመነሣት ይህን ሕይወት ያገኛሉ። ሆኖም ሌሎች የታመኑ ሆነው የተገኙ ሰዎች በምድር ላይ የዚህን የነገሮች ሥርዓት ፍጻሜ በሕይወት ስለሚያልፉ የኢየሱስ ቃላት በእነዚህ ሰዎች ላይ ቃል በቃል ፍጻሜውን ያገኛል። ፈጽሞ አይሞቱም! ኢየሱስ ይህን አስደናቂ ቃል ከተናገረ በኋላ “ይህን ታምኚያለሽን?” ሲል ማርታን ጠየቃት።

“አዎን ጌታ ሆይ፤” ስትል መለሰችለት። “አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ።”

ከዚያም ማርታ በፍጥነት ወደ እህቷ ሄደችና በምሥጢር “መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል” አለቻት። ወዲያውኑ ማርያም ከቤት ወጣች። ሰዎቹ ማርያም ስትሄድ ሲያዩ ወደ መታሰቢያው መቃብር የምትሄድ መስሏቸው ተከተሏት።

ማርያም፣ ኢየሱስ ጋር ስትደርስ እግሩ ላይ ወድቃ አለቀሰች። “ጌታ ሆይ፣ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው። ኢየሱስ ማርያምና የተከተሏት ሰዎች ሲያለቅሱ ሲያይ ሆዱ ተንሰፈሰፈ። “ወዴት አኖራችሁት?” ሲል ጠየቃቸው።

“ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት።

ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ፤ በዚህ ጊዜ አይሁዶች “እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ” ሲሉ ተናገሩ።

አንዳንዶቹ ኢየሱስ ከጥቂት ወራት በፊት የዳስ በዓል ሲከበር ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ወጣት እንደፈወሰ አስታወሱና “የዕውሩን ዐይኖች ያበራ ይህ ሰው እንዳይሞት ሊያደርግ አይችልም ነበርን?” አሉ።​—የ1980 ትርጉም ዮሐንስ 5:​21፤ 6:​40፤ 9:​1-7፤ 11:​17-37

▪ ኢየሱስ በመጨረሻ ቢታንያ አቅራቢያ የደረሰው መቼ ነው? እዚያስ የነበረው ሁኔታ ምንድን ነው?

▪ ማርታ በትንሣኤ ለማመን ምን መሠረት ነበራት?

▪ ኢየሱስ በአልዓዛር ሞት ምን ተሰማው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ